>

የወለጋው ሳምሪ .... !! (ዘመድኩን በቀለ)

የወለጋው ሳምሪ …. !!

ዘመድኩን በቀለ

… ባንክ እየዘረፈ፣ ደምወዙን እየበላ፣ ስንቅና ትጥቅ እየቀረበለት፣ ከመኖሪያው ከጫካው እየወጣ በየጊዜው ምስኪን የዐማራ ነገድ አባላት የሆኑ ገበሬዎችን በእንዲህ ዓይነት መልኩ የሚረግጠው፣ የሚያሰቃየው፣ የሚያርደው እና የሚረሽነው ደግሞ የኦሮሚያው ሳምሪ ኦነግ ሸኔ የተባለው የኦሮሚያው አልሸባብ ነው። ቦኮሃራም፣ አልቃይዳው ኦነግ ሸኔ ነው። ስለዙ ጠቅላዩም አይተነፍሱም። ሚዲያዎችም አይዘግቡትም። ገጽታ ያበላሻል።
… ትግራይ ድረስ ሄዳ ከመቀሌ ሸሽተው ሃገረ ሰላም ዋሻ ውስጥ ተደበቁ የተባሉትን የህወሓት አመራሮች የሚያወሩትን ወሬ ሁሉ ጭምር እየቀዳች 4ኪሎ ሚኒልክ ቤተ መንግሥት ድረስ በቀጥታ ስርጭት እንከታተለው ዘንድ መረጃ ትልክልናለች ተብሎ ትናንት በፓርላማ በየዓሰሎጠሚዶኮ ዐቢይ አሕመድ ጭምር የተመሰከረላት ተአምረኛዋ ድሮንና፣ ሳታላይቷም ጭምር እነዚህን የወለጋ ሳምሪዎች አይቀርጿቸውም። ድሮኗ ዓይኗ የሚገለጠው ለህወሓት እንጂ ለኦነግን ይጨልምባታል። ዳፍንታም ናት አታይም።  አትቀርጽምም።
… በማይካድራም የተራዱት፣ የተጨፈጨፉት፣ የተገደሉት ዐማሮች ናቸው። ገዳዮቹ ትግርኛ ከመናገራቸው በቀር ያው ገዳዮቹም ፀረ ዐማራ ናቸው። በወለጋም እየታረዱ፣ እየተጨፈጨፉ ያሉት ያው ዐማሮች ናቸው። ገዳዮቹ ኦሮምኛ ከመናገራቸው በቀር ያው ገዳዮች ፀረ ዐማራ ናቸው። ሁለቱም ዐማራን በመግደል በኩል ስምም ናቸው። ይሄን ስንቃወም ደግሞ ወዶ ገብ ተደማሪዎች ዘረኛ ይሉናል። አቦ ዘራችሁን ያጥፋው ልል እፈልግና ደግሞ ቀዝቀዝ እላለሁ። ቶርቶራ ሁላ አለ ጃዋር  !!
… ደስ የሚለው በዐማራ ክልል ያለ ትግሬም ሆነ ኦሮሞ ሰላማዊ ህይወቱን ይመራል። ዐማራ ሰው ነው። ከምር ሙሉ ሰው ነው። እስከ አሁን በዐማራ ወገን የተዘረፈ ባንክም ድርጅትም፣ ግለሰብም የለም። ሌባ ይዞ የሚያስረክብ እንጂ የሚዘርፍ የለም። የሰውነት ውኃ ልክ የሚሉት ነገር ሃቅ አለው። የሽመልስ አብዲሳዋ ኦሮሚያ ግን ለዐማራ ነገድ አባላት ሌላኛዋ ማይካድራ ናት። ደብረ ጽዮንን የሚጠይቀው፣ የሚቆጣው መንግሥታችን ደግሞ በሽመልስ አብዲሳ ላይ የሚጨክን አንጀት የለውም። ኦሮሞ ኦሮሞን አይጠይቀውማ  !  ኣ
… እንዲህ መከራውን የሚያየው ዜጋ የእሱ አባት፣ ወንድም፣ እህትና እናት ቢሆኑ አፉን የማይከፍተው ልቅ አፍ ወዶገብ ተደማሪ ሁላ ይሄ ለምን ይሆናል? ብለህ፣ መንግሥት የዜጎችን በህይወት የመቆየት መብት ያስጠብቅ፣ ያስከብርም ብለህ በመጠየቅህ ብቻ ሲንበጫበጭብህ ይውላል። እኔ ግን መስሚያዬ ጥጥ ነው። የኦነግ ተንከባካቢው ራሱ ዐቢይ አሕመድና ሽመልስ አብዲሳ ናቸው። የኦሮሚያ ፖሊስም ሚኒሻም በኦነግ ሸኔ የተዋጠ ነው። እንግዲህ ዐማራ የራሱ የሆነ የሚቆረቆርለት መንግሥት እስኪያገኝ ድረስ በዚሁ መልክ እየታረደ፣ እና እየተዘረፈ፣ ንብረቱም እየወደመበት በመከራና በጭንቅ ዘመኑን ይገፋል።
…  እናሳ ተደማሪዎች ሆዬ ስለዚህ ነገርስ ምን ትላላችሁ?  እስቲ ተንፒሱ  !!
 አሸባሪው ኦነግ-ሸኔ 
ወያኔን አጥቅቶ ኦነግ-ሸኔን መተው አይቻልም። ወያኔ በትጥቅና በገንዘብ እየደገፈች አገር እንዲያሸብር ያሰማራችው አሸባሪው ኦነግ-ሸኔ መወገድ ይኖርበታል። መንግስት በጀመረው ህግን የማስከበር እርምጃ ላይ ሳይቀር በአንዳንድ አካባቢዎች የኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች ከወያኔ ልዩ ኃይል ጋር በመሆን ከመከላከያ ሰራዊታችን ጋር ተዋግተዋል። በእርግጥ ፍላጎቱ ካለ ለኦነግ-ሸኔ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል ከበቂ በላይ ነው። የአማራ ልዩ ኃይል ወያኔን እንዴት አድርጎ እንደገረፋት አይተናል። ከአሁን በኃላ ግን መንግስት በአገር ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች የሚከሰቱ ግጭቶችን በተመለከተ በኦነግ-ሸኔና በወያኔ ላይ ማሳበብ አይችልም፤ ሰሚም አያገኝም። ወያኔ ላይ የሰራው ህግን የማስከበር ተግባር ኦነግ-ሸኔም ላይ ተግባራዊ ይሁን።
Filed in: Amharic