ደጀኔ አሰፋ
መከላከያ ሰራዊታችን በየደረሰባቸው ቦታዎች (በተለይ ቆላ ተንቤን ዙሪያ) ባደረጋቸው ጥልቅ አሰሳዎች እንዲሁም በትግራይ ገበሬዎች ጥቆማ አማካኝነት የተገኙት የጁንታው ባለስልጣናት እና ወታደራዊ አመራሮች የቀበር ጉድጏዶች ውስጥ አብዛኞቹ አስከሬኖች ከአንገት በታች የተቀበሩ በመሆኑ እና በዚያ ላይ ለሶስት እና ከዚያ በላይ ቀናት ተቀብረው የቆዩ በመሆናቸው ሳቢያ ማንነታቸውን የመለየት ስራውን የበለጠ ውስብስብ አድርጎት ቆይቷል::
በዚህም ሳቢያ ከአንገት በታች ሆነው በተገኙት አስከሬኖች ላይ መንግስት #የDNA ምርመራ ለማድረግ ጭምር እንደተገደደ እና ከዚህ ጋር ተያያዞ ያለው አብዛኛው ስራ አሁን ላይ እየተገባደደ መሆኑም ተጠቁሟል:: ብቻ ግን ዋናው ኦፕሬሽን ካለቀ የቆየ ቢሆንም ሪፖርት ለማዘጋጀት ግን ፈተናው ቀላል አልሆነም ነበር:: ይህም ለጁንታው ደጋፊዎች: ለተቀጣሪ የውጭ ጋዜጠኞች እና ለቴድሮስ አድሃኖም ዓይነት ከሃዲ ባንዳዎች የአለምአቀፉን ማህበረሰብ ለማወናበድ ትንሽ እድል ሰጥቷቸው ነበር ማለት ይቻላል – ባይሳካላቸውም!!!
ያም ተባለ ይህ ዋናው ኦፕሬሽን በተሳካ ሁኔታ ተደምድሟል!!!! ትህነግ ታሪክ ሆኗል!!! ትህነግ እንደ ድርጅት ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል!!!! የጁንታው ተላላኪዎች እና የጥቅም ተጋሪዎች ተራ አልቧልታ እና ቀረርቶ እንዲያው የቀን ቅዠት ሆኖ ቀርቷል!!! ጁንታው ቢኖር ኖሮ ድምፁ በተሰማ ነበር:: ድምፁ ከጠፋ ቆየ!!!
መለስ ዜናዊ በትጥቅ ትግል ወቅት “…ድምፁ ዘርሓቀ ተጋዳላይ ከምትዝሰወአ ቁፀርዎ” (ድምፁ ያልተሰማ ታጋይ እንደተሰዋ ቁጠሩት) ብሏል አሉ::
አዎ! ልክ ነው! ጁንታው በህይወት ቢኖር እስከዛሬ ድምፁ በተሰማ ነበር!!! ሮይተርስ እንኳን ከደብረፅዬን መስማት ካቆመ ቆየ:: ብቻ ትህነግ እንደ ተቋም የለም!!!አሁን ትህነግ የሚባል ድርጅት ጠፍቷል!!! ዳግም ሊነሳና ሊያንሰራራም ከቶ አይችልም!!! ‘ተዛዚሙ’!!! አልቋል!!! ዋና ጉዳይ ተጠናቋል!!!
አይደለም በኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ጭምር ሲፈራ የኖረው የማፊያዎች ስብስብ ተደምስሶ ርዝራዦቹ እንደ አይጥ እና እንደ እንሽላሊት ጉድጓድ ለጉድጓድ እየተሽሎኮሎኩ አለያም በባህታዊ ልብስ እና በገበሬዎች ቡሃቃ ስር ሲደበቁ ከማየት በላይ ሌላ ምን የቁም ሞት ሊኖር ይችላል?? እርስ በርስ አንገት እንደተቆራረጡ ከመስማት በላይስ ምን የሞት ሞት አለ??? እጅግ ጥቂቶቹ በደመነብስ ሮጠው የትእንዳሉ ራሳቸው እንኳን አያውቁትም!! ገሚሶቹ በጅብ ተበልተዋል:: ገሚሶቹ የአሞራ ሲሳይ ሆነዋል:: …ሲያልቅ አያምር! ስለዚህ ጁንታውን ተስፋ ያደረጋችሁ ምስኪኖች ብትኖሩ እርማችሁን አውጡ!!! በቃ ሌላ አልልም!!! እርማችሁን አውጡ!!!! አዲዮስ!!!
ይህን መረጃ ልጨምርላችሁ….
ጁንታው ወደ ቆላ ተንቤን ሸሽቶ በአራት እና በአምስት ቡድን ሆኖ በተለያዩ ዋሻዎች እንደተሸሸገ በዚያ ሰሞን ፈትለወርቅ ከደብረፅዬን ጋር በመገናኛ ራዲዮ ባደረገችው ንግግር “…አብይ በልጦናል : አሁን ልንጠፋ ነው : ስለዚህ እግሩ ስር ወድቀንም ቢሆን ለምን ይቅርታ አንጠይቀውም?”… በማለት በከፍተኛ ተስፋ መቁረጥ እንደወተወተችው እና ደብረፅዬንም በበኩሉ “አሁን ጊዜው ረፍዷል: ይህንን ማድረግ በፍፁም አንችልም: አሁን ከቻልን ነፍሳችንን ብቻ ለማዳን ባለን እድል ሁሉ ተጠቅመን እንሞክር እንጅ ጊዜው አልፏል….” በማለት እንደመለሰላት ከተጠለፈው የመገናኛ ራዲዮ መስመር መገኘቱ ይታወቃል:: ይህም ማለት የነፍስ አድን ጭንቅ ውስጥ እንደነበሩ መረዳታ ይቻላል:: ጭራሽ ይህንን ከተባባሉ ትንሽ ቆየ:: ሳምንታት አለፉ:: ከዚያ በኃላ ደግሞ የዘነበባቸውን ጥቃት ፈጣሪ ይወቀው:: አሁን ድምፃቸው ፈፅሞ የለም!!!!
አሁን ያለው የሊይሊቲ እና የገሬ እጅግ አስቂኝ “የደምስሰናቸዋል” ዜና ብቻ ነው:: አሁን ያለው የአሉላ ሰለሞን እና የማርቲን ፕላውት የቅዠት ወሬ ብቻ ነው:: ቀልደኞች ናቸው! እውነት ግን ጅንታው ቢኖር ድምፁ አይሰማምን?? …መቼም አዛውንቶቹ ለሽምቅ ውጊያ እየተዘጋጁ ስለሆነ ትንፋሽ እየሰበሰቡ ነው አይባልም:: እንኳን በ1960ዎቹ ፋሽኑ ያለፈበት ሽምቅ ውጊያ ሊያደርጉ ይቅርና የአዛውንቶቹ ትንፋሻቸው ቢኖር እስካሁን በተሰማ!!! ብቻ ግን ትግራይ የወራሪዎች መቀበሪያ ትሆናለች ሲሉ የነበረው ያ ሁሉ ድንፋታ እና ጉራ ውሃ በላው!!! ከደደቢት ተነስተው መጨረሻቸው ደደቢት ሆነ!!! የትህነግ ጅማሮ እና ፍፃሜ በበርሃ ሆነ!!! ትህነግ ወደ “ነበርነት” ታሪክ ተሸጋግሯል!!! ወደ ተረትነት ተቀይሯል!!!
አሁን የመንግስት ቀሪ ስራ ሪፖርት ማቅረብ ብቻ ነው:: ኦፕሬሽኑ እንዳለቀ ሪፖርቱ ወዲያው ያልቀረበበት ብዙ ምክንያቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ ቢገመትም አንደኛው ምክንያት ግን ጁንታው የራሱን ጏዶች አንገት እየቆረጠ አንገታቸውን ሌላ ቦታ ከአንገት በታች ያለውን አስከሬን ደግሞ ሌላ ቦታ በመቅበሩ ማንነት የመለየቱን ስራ ከባድ ስላደረገው ነበር::
ሌላኛው ምክንያት ደግሞ በየ ገዳማቱ እና በየ ገበሬው ቤት ራሳቸውን የቀየሩ የጁንታው አመራሮች ስለነበሩ ነው:: አሁን ግን ሁሉም ፍፃሜውን እያገኘ ይመስላል:: በተለይ ባለፉት ጥቂት ቀናት አሰሳው እና የመጨረሻው የተቀናጀ ከባድ ጥቃት በሚገባ ተካሂዷል::የሚገርማችሁ አንድ የጁንታው ከፍተኛ ጀነራል አንገቱ ተቆርጦ እንደተገኘም ሰምቻለሁ:: አስደንጋጭ ነው:: ብቻ ብዙ ብዙ ጉድ ገና እንሰማለን:: የክፋታቸውን ጥግም የበለጠ እንረዳለን!!!
በአጠቃላይ መንግስት በአጭር ቀናት ውስጥ በፓርላማ አለያም በሚዲያዎች በኩል የሞቱትን : የተያዙትን : የጠፉትን ያልተገኙትን ወዘተ የጁንታው አመራሮች በሚመለከት ዝርዝር ሪፖርት ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል:: ዋናው ጉዳይ ትህነግ ታሪክ መሆኑ ነው!!!! ትልቅ ድል ነው!!! ይህ ድል ትርጉሙ የሚገባን በጊዜ ሂደት ሊሆን ይችላል!!! ትህነግ እንዲህ በአጭር ጊዜ ይጠፋል ብሎ ከቶ ማን ሊገምት ይችላል?? ድሉ በአጭር ጊዜ ተረጋገጠ ማለት ግን የድሉን ትርጉም አነስተኛ አያደርገውም!!! ትህነግ ከደደቢት አዲስ አበባ ለመድረስ 17 አመት ፈጅቶበታል!!! ለመጥፋት ግን 17 ቀናት ብቻ ወሰዱ!!! የሰራዊታችን ብቃት የት እንደደረሰ ማሳያ ነው!!! አንድነታችንም ዳግም የተረጋገጠበት ኩነት ነው!!! ዘላለም የሚዘከር አስደማሚ ታሪክ ሆኖም ተመዝግቧል!!!
ለዚህም ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን : የአየር ኃይላችን : የሪፐብሊካን ጥበቃ ስፔሻል ኮማንዶዎች : የፌደራል ፖሊስ : ብሄራዊ መረጃና ደህንነት : የአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ እንዲሁም የአፋር ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ በሙሉ ትልቅ ክብር እና ምስጋና ይገባቸዋል!!!! መላው የኢትዮጵያ ህዝብም እስከመጨረሻዋ ሰዓት ከሰራዊታችን እና ከመንግስት ጎን በመሆኑ ድሉን ፈጣን እና ህዝባዊ ድል አድርጎታል!!!! የጠቅላይ ሚኒስትሩ ወታደራዊ የአመራር ብቃትም እፁብ ድንቅ ነበር!!! የፍትህ አምላክም አግዞናል ቢባል ትልቅ ሃቅ ነው!!! አሁን የቀረው ትንሽ አቧራ ብቻ ነው!!! አቧራ ደግሞ በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ይረጋል!!! እየረጋም ነው!!! ለኢትዮጵያም ብሩህ ዘመን እየሆነ ይሄዳል!!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!!