አቶ ሙስጠፌ መሐመድ የሱማሌ ክልል ፕሬዚደንት
” ትህነጎች ከአማራ ክልል መሬት ቆርሰው ለራሳቸው መውሰዳቸው ሳያንስ ለራሳቸው ወሰዱ ተብለው ላለመታማት ቆርሰው ለአጎራባች ክልሎች ሠጡ።
የሚገርመው ግና ይህ አይደለም! ከዚሁ ክልል ቆርሰው ለጎረቤት ሱዳን ሸጡ!!
ነገር ግን የህዝቡ አስደናቂ ታሪክ የተጻፈው እነርሱ ከ1990 ዓም ጀምሮ አማራ ክልል ለክተው ቆርሰው ለሱዳን ሽጠውት ተመልሰው አዲስ አበባ ደርሰው
ከቻርተር አውሮፕላናቸው ሳይወርዱ የአማራ ሚሊሻ (ፋኖ) የሸጡትን መሬት በነፍጣቸው ያስመልሱና የኢትዮዽያን ዳር ድንበር ያስከብራሉ።
በዚህ ድርጊት የሚበሳጩት የወያኔ አመራሮች በተለያዬ መንገድ የሀሰት ስም ለአማራ ፋኖ ኃይል እየሰጡ በኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት እርምጃ ለመውሰድ ይሞክሩ ነበር። ይሁን እንጂ አንድም ቀን ተሳክቶላቸው አያውቅም ነበር።
የአማራ ፋኖኮ የኢትዮዽያን ዳር ድንበር ለማስከበር ከሱዳን ጦር ጋር ብቻ ሳይሆን ከትህነግ ታዛዦች ጋር እየተዋጋ ብዙ ዋጋ እየከፈለ ሉአላዊነቷን ሳያስደፍር የኖረ ክቡር ሀይል ነው።
የአማራ ፋኖ ከለውጡ በኋላም ቢሆን በመንግስት ደረጃ በከባድ መሳርያ ተደራጅቶ ለመውረር የሚመጣውን የሱዳን ኃይል ልክ እንደ ቀድሞው ዓላማው አርሶ ያመረተውን እህል ሽጦ በግሉ ጥይት እየገዛ በትክሻው በሚይዘው የግሉ ክላሽ ና ሚኒሽር እየገረፈ በመጣበት እግሩ መልሶ እያባረረ የአባቶቹን ታሪክ በመድገም የሀገሩን ዳር ድንበር እያስከበረ የሚገኝ የመላው ኢትዮዽያውያን ተምሳሌት ና ኩራት የሆነ የጀግና ስብስብ ነው።
የአማራ ኃይል ለውጡን ደጋፊ መሆኑን ያሳየበት አቋም ደግሞ በቅርቡ መንግስታችን በትግራይ ክልል እየሰራ በአለው የህግ ማስከበር ኦፕሬሽን
የኦፕሬሽኑ አንድ አካል መሆኑን ጠብቆ የሱዳን ጦር ወረራ ሲፈጽም፤ ከመንግስት ትእዛዝ በመጠበቅ ወረራውን ዝም ብሎ ተመለከተ። ይህ የአማራ ፋኖ(ሚሊሻ) አስተሳሰብ እጅግ የሚደንቀውም ለለውጡ መንግስት ያለውን ክብርና የመንግስትን ትእዛዝ ለመጠበቅ ያሳየው ልዩ አክብሮት ነው።
መንግስት ድንበራችን እንዲከበር ትእዛዝ ቢሰጥስ? ከዚያ በኋላ የሚፈጠረውን ለማየት ያጓጓል። የኢፌዴሪ መከላከያ ኃይል እገዛ ሳይኖርበት የአማራ ፋኖ ኃይል ብቻውን ድሉን በአጭር ቀን እንደሚያበስረን ቅንጣት ያክል ጥርጥር የለኝም!!”
ከአልአይን ጋር ካደረጉት ምልልስ