>

“ ዓይኖችህም ከሚያዩት ጆሮዎችህም ከሚሰሙት የተነሣ ዕብድ ትሆናለህ...!!!” ዘዳ 28፥34 (ዘመድኩን በቀለ)

 
“ ዓይኖችህም ከሚያዩት ጆሮዎችህም ከሚሰሙት የተነሣ ዕብድ ትሆናለህ…!!!” ዘዳ 28፥34
ዘመድኩን በቀለ

የወንድ ልጅ ብልት ቆርጠ በአፋቸው ያንጠለጥሉታል፤ የሴትን ልጅ ብልት እንደ ቋንጣ ዘልዝለው በእግር ላይ ይሰቅሉታል  !!
 
★ እናቱ ያዝለችው ህፃን አንገት ማረድ ወግ አለው ወገቡ ላይ ለሁለት ቆርጠውት ሲጥሉት ያየ ሰው ጤነኛ አይምሮ ይኖረዋል???
 
★ አምስት ግዜ በቀስት ወግተውት አልሞት ሲላቸው በካራ አንገቱን አረዱት!!!
ሰለባዎች ይናገራሉ ቪድዮውን እስከ ፍጻሜው ይመልከቱት….
 
… ጣሊያን ጀምሮት፣ ደርግ አተራምሶት ከዘመነ ህወሓት የቀጠለው እና አሁን በዘመነ ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ እየተፈፀመ ያለው አረመኔያዊ የጭካኔ ድርጊት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ በዓይነቱ ለየት ያለ ዘግናኝ ተግባር በሰው ልጆች ላይ እየተፈጸመ ይገኛል። ይሄ ዘግናኝ ወንጀል በጀርመን ከተፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ጋር የሚነጻጻርም አይደለም። በጀርመን የሰው ልጆች አይሁዶች ቢገደሉም አልተበሉም። በኢትዮጵያ ግን የሰው ልጅ እየተበላ ይገኛል። በ21 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በየትኛውም የዓለማችን ክፍል የማይፈጸም አረመኔያዊ የወንጀል ድርጊት ነው በሃገራችን እየተፈጸመ የሚገኘው።
… መጀመሪያ በሶማሊያ ክልል፣ ቀጥሎ በደቡብ፣ ኦሮሚያና አዲስ አበባ፣ ከዚያም ሰሜን ሸዋ፣ አፋር፣ ቅማንትና ዐማራ፣ የአረመኔዎች ተግባር ታየም፣ ተፈጸመም። ጥቅምትና ሰኔ በኦሮሚያ በቢልዮን የሚቆጠር የዐማሮችና የኦርቶዶክሳውያን ንብረት ወደመ። ኦርቶዶክሳውያኑ፣ ታረዱ፣ በእንጨት ላይ ተሰቀሉ። በመኪና እና በሞተር ሳይክል አስከሬናቸው ተጎተተ። ሰውነታቸው ተቆራርጦ ተጣለ። ይህ ሁሉ ሲሆን መከላከያ ሠራዊቱና ፖሊሱ ዝም ብሎ ቆሞ ያይ ነበር። እስከ አሁን በወንጀሉ የተጠየቀም፣ የሚጠየቅም የለም። ሽመልስ አብዲሳ አሁንም በወለጋ ዐማራን እያጸዳ ነው። በፊት በፊት በህወሓት ነበር ወንጀሉን ሁሉ ዐቢይ አሕመድ የሚያሳብበው። የጦስ ዶሮ አሁን ጠፍቷል።
… የመተከሉ ጉዳይ የሃገር ውስጡ የእነ ዐቢይ አሕመዱ ገዳይ ቡድን ፍላጎት ብቻ ያለበት አይመስልም። የውጭ ወዳጆቹ ጭምር በመተከል ጆፌ ሳይጥሉ አልቀረም። የግብፅ እጅ፣ የሱዳንና የዓረቦቹም እጅ ብቻ አይመስለኝም። የሃያላኑ የምዕራባውያኑ እጅም ሳይኖርበት አይቀርም ባይ ነኝ። ከገዳዮቹ መሃከል፣ የተሸፋፈኑ ዓረቦችና ነጮችንም አይተናል የሚሉ ሰዎችን ስታይ ነገሩ ከፍ ያለ መሆኑ ይገባሃል። የዐማራ ልዩ ኃይል እንዳይገባ የሚደረገውም ለዚሁ ነው። ምክንያቱም ውጊያው ከጉምዝና ከኦነግ ጋር ብቻም አይሆንም እና ነው።
… አሁን ከሰው ማረዱም በላይ አስከፊው ነገር ከፊታችን የቆመው ችግር ነው። ከመተከል፣ ከወለጋ የተፈናቀሉት፣ የሺናሻ፣ የዐማራና አገው ነገድ አባላት ያለ ምግብ፣ ያለመጠለያ ሜዳ ላይ ፈስሰዋል። መድኃኒት የለም። ምግብ የለም። መንግሥት ተፈናቃዮቹ አንዳችም ነገር እንዳይደርሳቸው አድርጎ አስሮ አስቀምጧቸዋል። በመተከል ታርደው ከሞቱት ይልቅ አሁን በመድኃኒት እጦትና በረሃብ የሚረግፉት ይልቃሉ። ዐቢይ አሕመድ ዝም፣ ጭጭ፣ ጮጋ፣ ባላየ ባልሰማ ለሽሽ ብሏል። ሌሎች ነገዶችም ዝም፣ ጭጭ ብለዋል። ሚዲያዎች አይተነፍሱም። ለጊዜው ለእነ ታዬ ደንደአም ዐማራን የማጽዳቱ ሥራ የተሰካ መስሏል።
… በዐማሮቹ ላይ የሚፈጸመውን የዘር ማጥፋትና የጭካኔ ተግባር ስንመለከት ወንጀሉን የሚፈጽሙት ሰዎች ወንጀሉን የሚፈጽሙት በህይወት የተረፉት ሰዎች ከርስታቸው ነቅለው እንዲወጡና ወደ ሥፍራው በድንጋጤ እንዳይመለሱ ለማድረግ ነው። የሚገርመው ነገር ግን ዐማራ ሲሰደድ ሃገሩ ውስጥ ነው እንጂ ዐማራ ኢትዮጵያን ለቅቆ የሚሄድበት ትርፍ ሃገር የለውም። ሱዳንም ቢሆን ማለቴ ነው። ይሄኛው በዐማሮች ላይ እየደረሰ ያለ ግፍ ነው። የግፍ ጽዋው ሞልቶም እየፈሰሰ ነው። ለማንኛውም ይሄን ለማናችንም የማይቀረውንና በተራ የምንጎበኝበትን የተሻገር ጣሰውን ዘገባ ጨከን ብላችሁ እዩት፣ ተመልከቱት። https://youtu.be/kFhKFEAwQuE
… እንደ ሃገር ስንመለከት ደግሞ አብዛኛውን የደረሰ ሰብል አንበጣ እና የግሪሳ ወፍ አውድሞታል። ሱዳን ወርራ የዘረፈችው፣ ኦነግ በወለጋ ያቃጠለው፣ በቤኒሻንጉል እና በጉማይድሌ፣ በደቡብ ኢትዮጵያም የወደመው፣ በረዶም ያጠፋው እህል ተደማምሮ ቀላል የማይባል የምግብ እጥረት ከፊታችን እንደሚጠብቀን ለመናገር ነቢይ መሆንን አይጠይቅም። የዳር ሃገሩ ህዝብ ጭንቅ ላይ ነው። ትርፍ አምራች የሆነው የመተከልና የወለጋ ገበሬም ገሚሱ ታርዷል። ማሳውም ጎተራውም ተቃጥሏል። ሱዳን እንኳ በአቅሟ ድንበር ተሻግራ እህል ዘርፋ፣ ማሳ አውድማ፣ የግብርና ማሽኖች አቃጥላለች። የሚደርሱኝ መረጃዎች የሚያሳዩኝ የሃገር ውስጥ ስደተኛው የትየለሌ መሆኑ ነው። በቀጣይ ከዐቢይ አሕመዱ የሸገር ፓርክ እና የእንጦጦ ፓርክ ቤተሰቦች በቀር በመላዋ ኢትዮጵያችን የረሃቡ ነገር አስጊ ነው።
…አሁን የዳር ሃገሩ የተፈታ ይመስላል። በትግራይ ምን እየተካሄደ እንዳለ የሚያውቅ የለም። መቀሌ ላይ ካሜራ ፊት ተመርጠው የሚቆሙ ግለሰቦችን ሁኔታ እያየን የገጠሩን የትግራይ ነዋሪ ህይወት ልንረዳ አልቻልንም። ድፍን ሁለት ወር ሙሉ ቤተሰቦቻችን ናፈቁን የሚሉ አቤቱታዎች እየሰማን ነው። በሴፍቲኔት ህይወቱን የሚገፋው የትግራይ ገበሬ አሁን ምን ላይ ደርሶ እንደሆነ የሚያውቀው ፈጣሪ ብቻ ነው። ብዙዎች በኤርትራ ወታደሮች ሴቶቹ እየተደረፈሩ፣ ሃብት ንብረታቸውንም እየተዘረፉ እነደደሆነ ነው እየተነገረ ያለው። በተለይ የኤርትራ ወታደሮች የሚማርኳቸውን የህወሓት ባለሥልጣናት አፍታም ሳያቆዩ ነው የሚረሽኑት እየተባለ ነው። ቂማቸውን በሰፊው እንዲወጡ ዐቢይ አሕመድ ለሸአቢያ ፈቃድ የሰጠ ይመስላል።
… እናም መጪዎቹ ወራቶች ደስስ አይሉም። የራበው ህዝብ ይበዛል። በዚህ ላይ ብዙ የሆድ ብሶት ያለበት ህዝብ ነው ያለው። ይሄም አልበቃ ብሎት በላዩ ላይ ሌላ መከራ ተጨምሮበታል። እሳት አደጋው ሌላው አደገኛ መጥፎ ምልክት ነው። ምሽት እየጠበቀ ደቡብና ሰሜን የሚንቦገቦገው እሳት በጊዜ ካልቆመ መጪውን ጊዜ ደሃ በርከት ብሎ የጦዘ ችግርና አስፈሪ ጊዜ የሚከሰት ይመስላል።
… ሥራ ፈላጊው የትየለሌ ነው። ሥራ ግን የለም። በኦሮሚያ ፋቢሪካዎች በኦነግና በብልጽግና ቄሮዎች እንዲወድሙ፣ በጎንደር በሱዳን ወራሪ የእርሻ ማሳዎች እንዲወድሙ፣ በደቡብና በምዕራብ ኢትዮጵያ ገበሬዎች፣ አርሶአደሮች ታርደው እንዲጠፉ ስለተደረገ አሁን ሁሉም ሰው ወደ ከተሞች በመፍለሱ ከተሞች በሥራ አጥ ወጣቶች ተጨናንቀዋል። እናም ሥራ የለም። ረሃብ ደግሞ በየቤቱ ከተማ ድረስ ገብቷል።
… የውጭ ምንዛሪ ንሯል። ነጋዴ ሁለት ዶላር አንድ መቶ ስምንት ብር እየመነዘረም ቢሆን ለመንቀሳቀስ ቢፈልግም እንደልቡ እንዳይንቀሳቀስ ዓለምአቀፍ ወረርሽኙ አንቆ ይዞታል። ብዙ ሰው ገንዘብ ተሸክሞ ዓይን ዓይኑን እያየው ተቀምጧል። አይዝናና መዝናኛው ዝግ ነው። አይጓዝ አውሮጳም አማሪካም ወፍ የለም። ገንዘቡን ተሸክሞ የቁም እስረኛ ሆኗል። የበረኸኞቹ ገንዘብ ከወረቀት እኩል ይመደባል። ተራና ርካሽም ይሆናል ያሉት ነገር ቀስ እያለ እየመጣ ነው። በዚምቧቤ፣ በሱማሌ ላይ ስንስቅ እኛው ዓይናችን እያየ ብር በጆንያ ተሸክመን ዳቦ ልንገዛ መሰለፋችን ነው። ይሄም ያስፈራል።
… ሀገሪቷ በፍንዳታ የእኔ ቢጤ ወጠጤዎች ስለምትመራ ከፊቷ አደጋ ተጋርጧል። ነገን ታሳቢ የሚያደርግ ፖሊሲ የሌለው በስብከት ሃገር የሚመሩ አውርቶ አደሮች ቦታውን ስለያዙት መጪው ጊዜ የከፋ ነው። ቤተሰቡን በቅጡ መምራት የማይችል፣ ትምህርቱን በቅጡ ያልጨረሰ፣ ለእረፍት እንደወጣ ወደ ትምህርት ቤት ያልተመለሰ ሁላ አሁን ባለ ሥልጣን ሆኖ የኢኮኖሚ ተንታኝ ቀማሪ ሆኖ በአፍጢማችን ሊደፋን ሩብ ጉዳይ ላይ ደርሰናል። የሲቪል ሰርቪስን ዲግሪ የገበሬ ድግር ይበልጠዋል በሚባልበት ሃገር መሃይሞች ሜካፕ እየተቀቡ፣ ሱፍ ለብሰው በየሚዲያው እየወጡ በመተወን ሃገር በረሃብ እና በእርስ በእርስ ጦርነት ሊፈጁ ነው።
… አሁን በጎጃም በቻግኒ አካባቢ መድኃኒት የሚባል የለም እየተባለ ነው። ምግብማ አስፈሪ ነው። የህክምና መሣሪያዎችና ግብአቶች ያልተሟሉላቸው ጤና ጣቢያዎች ውስጥ የሚሞተው ዜጋም የትየለሌ ነው። ሃኪሞች በጸሎት ህሙማንን እንዲፈውሱ የተፈረደባቸው ይመስላል። መድኃኒት ኢንጅሩ። እናም ደስስ አይልም።
… አንዳንዶች ቤተመንግሥት አካባቢ የተሠሩ መናፈሻዎችን፣ በከተማው ውስጥ የቆሙ ፎቆቹን፣ ቪላዎችንና ውድ ውድ መኪኖችን በማየት፣ የኢትዮጵያ ሚዲያዎችም ለገጽታ ግንባታ ብለው የሚያሳዩአቸውን ቪድዮዎች ብቻ በማየት ነውራችንን በግርግር፣ በሆያ ሆዬና በካድሬ ዲስኩር ለማሳለፍ ይላላጣሉ። ይሄ ግን አያዋጣም። አያዛልቅምም። ምን ብንደብቀው፣ ምን ብንሸሽገው ቦርጭም ከሆነ ይጠፋል፣ ሽልም ከሆነ ይገፋል። ብቻ ጊዜ ደጉ የሚፈታውን ጉዳይ በፕሮፓጋንዳ ጋጋታ ብቻ ልንሸፍነው አንችልም።
… መጪው ጊዜ ለዚያው ካደረሰን የምርጫ ጊዜም ነው ተብሏል። ምርጫው ቅርጫ እንዳይሆን ያሰጋል። ኦሮሚያ እንዴት ተብሎ ሊመረጥ ነው? ትግራይስ? በደቡብ ምርጫ ነው ሪፈረንደም? ስለየቱ ያስብ? ቤኒሻንጉል ቀስቱ በየት በኩል ያስመርጣል? አዲስ አበባ ሁለት ጊዜ በሚመርጡ መራጮች ልትታመስ ነው የሚሉም አሉ። መጀመሪያ ኦሮሚያ ሄደው በክልላቸው ይመርጣሉ፣ ቀጥሎ በታደሉት መታወቂያ መሠረት በሳምንቱ ይመርጣሉ ስለሚባለው ነገር ቡርቱካን ሚደቅሳ ምን እንደምታስብ ለማወቅ የጓጉም አሉ። ጃዋር በኦሮሚያ፣ እስክንድር በአዲስአበባ ሌላው የመንግሥት ተብዬዎቹ ፈተና ናቸው።
… ምስቅልቅል ያለ ነገር … እንዲያም ሆኖ ግን ኢትዮጵያ ግን ትነሣለች። ይሄ ሁሉ ውጥንቅጥ የሚጠርገውን ጠርጎ፣ ጥቂቶችን አስተርፎ ማለፉ አይቀርም። ለትንሣኤው ዘመን ለመብቃት ግን ንሥሀ እንግባ፣ ሥጋወደሙ እንቀበል። በምኞት፣ ከተማ ነኝ፣ ከችግሩ ሥፍራ የራቀ ሥፍራ ነው ያለሁት ብለው ተዘልለው አይቀመጡ።
… የትም ይሁኑ የትም መከራ ፈተናው ሁሉ በሁሉም የዓለም ክፍል ነው። እዚህ እኔ ያለሁበት ሃገር ያለሁበት ከተማ ሁሉ ነገር ከተዘጋጋ ወራቶች ተቆጠሩ። ታላላቅ ሞሎች እቃቸውን አውጥተው ዘግተዋል። ሆቴሎች፣ መዝናኛ ስፍራዎች፣ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ከተዘጉ ቆዩ። ትምህርት ቤቶች ዝግ ናቸው። በሽታው የሌለ አሽመድምዶአቸዋል። እንግሊዝ የሆነ ክፍለሃገሯ፣ በጎርፍ ተጥለቅልቋል። አርመኒያና አዘርባጃን በጦርነት ደም እየተፋሰሱ ነው። ሁሉም በሩን ዘግቶ ከቤቱ ተቀምጧል። ነገ ምን እንደሚከሰት አንድዬ ብቻ ነው የሚያውቀው። በአጠቃላይ ኢትዮጵያ በጽኑ ታማለች። ዓለምም ተደቁሳ ተኝታለች።

… ፈጣሪ ምህረቱን ይላክልን  !!

Filed in: Amharic