>

አዲስ አበባን ለመሰልቀጥ ያሰፈሰፈው ኦህዴድ የስውር ጦሩንም የግላጩንም በስፋት እያመረተው ነው !!! (ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው)

አዲስ አበባን ለመሰልቀጥ ያሰፈሰፈው ኦህዴድ የስውር ጦሩንም የግላጩንም በስፋት እያመረተው ነው !!!

ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው

*… አስረዱኝ….
 መንግስት በተለያዩ ቦታዎች በተለይ ወለጋ ለፈሰሰው የንፁሃን ደም ተጠያቂ ነው የሚለው ኦነግ ሸኔ ነጭ ድንኳን ዘርግት ፣ተረጋግቶ ወታደሮች ማስመረቁ በሃገራችን መንግስት የሚባል አካል ከመኖሩ ጋር ያለውን ግንኙነት የሚያስረዳኝ እሻለሁ። At any cost የመንግስትን defend የሚያደርጉ ግብረ-በላዎች  ይበረታታሉ….
 
ኦነግ ሸኔ ንፁሃንን እየጨፈጨፈ ነው። ከዚህ ጨካኝ ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሰዎች ቢሯቸው ቁጭ ብለው መግለጫ ይሰጣሉ። ስልጣን ላይ ያሉት አንገራግረው ይተዋቸዋል።  ጫካ ያለው የኦነግ ኀይልም የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል  አሰለጠንኩ ባለ ቁጥር በምስል ያሰለጠናቸውን ያሳያል።  የዚህ ድርጅት ተባባሪ መዋቅር የኦሮሚያ ክልል መዋቅር ነው።  ይህ ሁሉ እያለ ግን ታሳሪው ንፁሁ እስክንድር ነጋና ጓዶቹ ናቸው።
ከትህነግ ጋር ተባብሮ፣ ከኦነግ ጋር ተመሳጥሮ ክልልና ሀገሩን ለማበጣበጥ ሰራ የተባለ የኦሮሚያ ከፍተኛ ባለስልጣን ከመታገድ ውጭ ምንም አልሆነም። ጭራሽ አሁን ይመልሷቸዋል ተብሏል። እነዚህ ሰዎች ከሁከትና ብጥብጥ ጀርባ ነበሩ እየተባለ በሚዲያ ተነግሮባቸዋል። ግን የታሰሩት ንፁሆቹ እነ እስክንድር ናቸው!
በዐቃቤ ሕግ፣ ደህንነት መስርያ ቤቱና ሌሎች ቁልፍ ተቋማት ውስጥ ሆነው ከአሸባሪዎቹ ጋር ተመሳጥረው ሲሰሩ የነበሩ ምንም አልሆኑም። የስልጣን ቦታ ለውጥ ይደረግላቸዋል። ይህ በሆነበት ግን የታሰሩት እስክንድርና ጓዶቹ ናቸው።
መንግስት ለሀገርና ሕዝብ ቢያስብ ኖሮ አዲስ አበባ በእነ ታከለ ኡማ ስትዘረፍ ለምን ያሉት እነ እስክንድር መሸለም ነበረባቸው። ባይሆን እንኳ ይህ እስር በምንም ተአምር አይገባቸውም!
እነ እስክንድር አዲስ አበባን መዋጥ በሚፈልጉት ጥላቻ ነው የታሰሩት። ሌላ ጥፋት የለባቸውም።
ለሕዝብና ለሀገር የሚያስብ መንግስት ቢኖር እስክንድር የአዲስ አበባ ከንቲባ ነበር መሆን የነበረበት!
የእስክንድር ብቸኛው ወንጀል ለአዲስ አበባ ድምፅ መሆኑ ነው። የእነ እስክንድር ወንጀል ወንጀለኞችን ማጋለጣቸው ነው!
Filed in: Amharic