>
5:26 pm - Saturday September 15, 5038

“እስክንድር ነጋ ይፈታ!” የሚል ዓለም አቀፋዊ ዘመቻ ይፋ ተደረገ...!!!

“እስክንድር ነጋ ይፈታ!” የሚል ዓለም አቀፋዊ ዘመቻ ይፋ ተደረገ…!!!

የህሊና እስረኛ የሆነውን እስክንድር ነጋ በአስቸኳይና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከእስር እንዲፈታ ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡን ለማሳሰብና ለመጠየቅ ገለልተኛና የፓርቲ ልሳን ያልሆነ ዓለም አቀፍ ዘመቻ ተጀምሯል። በአብይ አህመድ አገዛዝ በግፍና በማን አለብኝነት በህገወጥ ሁኔታ በፖለቲካ ጥላቻና ቁማር ምክንያት እስር ቤት እየተሰቃዩ የሚገኙትን እስክንድር ነጋንና ባልደረቦቹን ለማስፈታት የተጀመረውን ዓለም አቀፋዊ ጥረት እንድትቀላቀሉ ትጠየቃላችሁ።
በትዊተር @FreeEskinderN
በInstagram ላይ @freeeskindernega ላይ ይከተሉን
እንዴት እስክንድር ነጋን የሚያክል የሰላምና የዲሞክራሲ ሐዋርያና ዋርካ በትህነግ ዘመን የተሰቃየው ሳያንሰው አሁን ደግሞ በአብይ አህመድ አገዛዝ በግፍ እስር ቤት ሲጣል ኢትዮጵያዊያን ዝም ብለን እናያለን? አባዱላ ገመዳ፣ ወርቅነህ ገበየሁና የመሳሰሉት ነፍሰ ገዳዮችና ዘራፊዎች በድሎትና በምቾት አየተንቀባረሩ ሲኖሩ እድሜ ልኩን ለኢትዮጵያ ህዝብ ዋጋ እየከፈለ የሚገኘው እስክንድር ነጋ በእስር ይማቅቃል? እስክንድር ነጋ እስር ቤት እየተሰቃየ ለአብይ አህመድ ማሸርገድና ከገዳዮችና አሳሪዎች ጎን መቆም ኢትዮጵያዊያን ለሆኑ በሙሉ ትልቅ ውርደትና የቁም ሞት ስለሆነ እስክንድር ነጋ በአስቸኳይ እንዲፈታ ጥረትና እርብርቦሽ መደረግ አለበት።
ለዓለም አቀፍ ድርጅቶች የሚላኩ በቅድሚያ የተጻፉ ኢሜሎች አዘጋጅተናል። በአሜሪካ ሴኔትና በተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ የሚያገለግሉትን ተወካዮች በኢሜል፣ በደብዳቤና በስልክ እያነጋገሩ ከዚህ የተቀደሰ ዓላማ የበኩልዎን አስተዋጽኦ ያበርክቱ። ስለ እስክንድር ነጋ ጉዳይ ወቅታዊ የዜና ዘገባዎችንና ሌሎች መረጃዎች ስለሚለቀቁ የኢሜል አድራሻዎትን ይስጡ።
Filed in: Amharic