ታላቁ እስክንድር ነጋ ማነው ?
የአዲስ አበቤ ጨዋዎች ግሩፕ
ሩትጋር ዩንቨርሲቲ ከሚሰራው አባቱና የአሜሪካን ዩንቨርሲቲ ኦፍ ቤሩት አስተማሪ ከሆነችው
እናቱ በ1960 ዓ.ም ተወለደ።
በሳንፎርድ ት/ቤት የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን ከተከታተለ በኋላ ወደ አሜሪካ በማቅናት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን እዛው ጨርሶ ዋሽንግተን በሚገኘው አሜሪካን ዩንቨርሲቲ ተቀላቀለ ። እዛም ፖለቲካል ሳይንስና ኢኮኖሚክስ ተምሯል ።
ዘወትር ሰለአገሩ ማሰብ የማይታክተው እስክንድር ከደርግ ውድቀት በኋላ ለጉብኝት ወደ አገር
ቤት የመጣው እስክንድር መንግስት የሰጠውን ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት ተመርኩዞ የመጀመሪያ ጋዜጣውን ኢትዮጲስን በ1985 ዓ.ም ማሳተም ጀመረ ። ነገር ግን ቃሉን የበላው መንግስት ጋዜጣውን አገደው ።
ከባለቤቱ ሰርካለም ጋር በመጣመር የ”ሰርካለም አሳታሚ ድርጅትን” በመመስረት እርሱ በዋና ስራአስኪያጅነት እንዲሁም ባለቤ ሰርካለም በአዘጋጅነት ይሰሩባቸው የነበሩትን ” አስኳል ፣ ሳተናው ፣ ምኒሊክ የተሰኙ ጋዜጦችን የወያኔ ቀለብተኞች በህግ ሽፋን በማገድ ሁለቱንም ወደ ቃሊቲ ባጋዟቸው ጊዜ ባለቤቱ የመጀመሪያ ልጃቸውን በእስር ቤት እንድትወልደው ተገዳለች ።
በወቅቱ ሰርካለም ነፍሰጡር የነበረች ሲሆን በማረሚያ ቤት በደረሰባት ስቃይ ምጥ ያለቀኑ
ቢመጣባትም ሰብዓዊነት የሚጎድላቸው የማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎችና ባለስልጣናት ምንም
ሊረዷት ስላልቻሉ ያለጊዜው ለመገላገል በቅታለች ።
ጨቅላውንም ማሞቂያ ክፍል ማስገባት ሲገባቸው አንድ ክፍል ውስጥ ደረቅ አልጋ ላይ
በመተው እንዲሞት የተውት ቢሆንም በእግዚአብሔር ቸርነት ያ ሰይጣናዊ ሳይሆን ቀረ ። ከዚህም የበለጠ መከራና ስቃይ እንኳ እየደረሰበት እስክንድር ከአላማውም ውልፍት አላለም ።
እስክንድር ለሰብዓዊ መብት መከበር ባደረገው ትግል ዘጠኝ ጊዜ ለእስር ተዳርጓል ። የ1997
ዓ.ም ምርጫ ውጤትን ተከትሎ ብዙ ጋዜጠኞችና አክቲቪስቶች ሲታሰሩ ከነዛ ውስጥ እሱና ባለቤቱ ሰርካለም ይገኙበታል ።
ከሁለት ዓመት እስር በኋላ የተፈታ ቢሆንም የጋዜጠኝነት ፍቃዱ ተሰርዞ ጋዜጣውም
በመታገዱ በኢንተርኔት መጻፉን ቀጠለ ።
ሆኖም የወጣውን የጸረ ሽብር ሕግ በመቃወሙና የታሰሩ የመብት ተሟጋቾች እንዲፈቱ
በመቀስቀሱ በሽብርና አገርን በመሰለል ወንጀል ተከሶ የግንቦት 7 አባል ነህ በሚል የ18
ዓመት እስር ስለተፈረደበት ወደ ወህኒ ተላከ ።
የግንቦት 7 አባል እንደሆነ እንዲፈርምና እንዲፈታ የተጠየቀ ቢሆንም በውሸት ላለመስማማት በአቋሙ ጸንቷል ።
ከሰባት ዓመት እስር በኋላ ፤ የፖለቲካ እስረኞችና ጋዜጠኞች በመፈታታቸው ከእስር ሊወጣ
ችሏል ።
እስክንድር የእድሜውን እኩሌታ ለታገለለት ሰበዓዊ መብት እና/ወይም የመናገር ነፃነት
ዓለምአቀፍ ሽልማቶችን ፣ እውቅናና ክብር አግኝቷል ።
ከእነዚህም :-
1. 2004ዓ.ም (2012) PEN/Barbara Goldsmith Freedom to Write Award
2. 2006ዓ.ም (2014 ) World Association of Newspapers’ Golden Pen of
Freedom Award
3. 2009ዓ.ም (2017) International Press Institute World Press Freedom
Hero
4. 2010 (2018) Oxfam Novib/PEN Award
እስክንድር ብሔርን፣ ቋንቋን፣ ዘርን መሰረት ሳያደርግ ለሰበዓዊነት የሚታገል ያሰበውም
ሳይሳካ እርምጃውን የማይገታ እንደሆነ ይናገራል ።
እስክንድር ነጋ ዛሬም በእስር ላይ ይገኛል
“ሁላችንም ተጓዦች ነን ፤ ፍጥነታችን
ቢለያይም መድረሻችን አንድ ነው – ነፃ ዲሞክራሲ” ብሎን ነበር ታላቁ ሰው ።
ፍትህ ለህሊና እስረኞች