ሰብአዊነት ነው አትበለኝ….!!!
አብዲሳ አጋ
አርቲስት ነኝ ብለህ ከወለጋ ከመተከል ከኮንሶ እዚሁ ሀገርህ ውስጥ የተፈናቀሉ በመቶ ሺዎች እያሉ ፤ ሱዳን ያሉት ናቸው የሀገር ልጅ የማር ልጆቼ ማለትህን
* ሰብአዊነት ነው አትበለኝ *
አባ ገዳ ነኝ ብለህኝ 100 ሺ በላይ እናቶች እና ህጻናት እዚችው ከአ.አ 300 ኪ.ሜ የማይበልጥ ሜዳ ቦታ ላይ ወድቀው እያሉ ፤ ለፖሎቲካ ትርፍ ተልከህ 1ሺ ኪ.ሜ ተሻግረህ እርዳታ ስታረግ
* ሰብዓዊነት ነው አትበለኝ *
የሀገር መሪ ነኝ ብለህኝ ከወለጋ ከመተከል ኮኮንሶ መሪ አለኝ ብለዉ በተቀመጡበት የተፈናቀሉ ወገኖችህን ትተህ፤ ቦሌ መንገድ ላይ የተነቀለው አበባ ካሳሰበህ
* ሰብዓዊነት ነው አትበለኝ *
ለፖሎቲካ ተላላኪነትህንና ለፖሎቲካ ጥቅምህ ያረካቸውን ነገሮች “
ሰብአዊነት ነው አትበለኝ “
ሰብአዊነት ማለት ሰውነት ነው ፤ ሰውነት ደሞ አያበላልጥም ፤አያወዳድርም ፤ ለማን ምን ባደርግ ትርፍ ያስገኝልኛል አያስብልም ።
( ያኛውን አትርዳ ያንን እርዳ አላልኩሁም ፤ ሰብዓዊነት ተሰምቶህ ከረዳህ ለሁሉም እኩል እርዳ )