>

"--ከአማራ ፖለቲከኞች ጋር የተኩስ አቁም ድርድር እያደረግን ነው .....?!?"  (ሸንቁጥ አየለ)

“–ከአማራ ፖለቲከኞች ጋር የተኩስ አቁም ድርድር እያደረግን ነው …..?!?”

 

ሸንቁጥ አየለ


“ከአማራ ፖለቲከኞች ጋር የተኩስ አቁም ድርድር እያደረግን ነው ።”   ኦሮ አማራ በሚሉት የሸፍጥ መድረክ ኦነጋዉያን የሚቀልዱት መራራ ቀልድ ነዉ።

በመተከል አማራ ላይ የሚደረገዉን የዘር ፍጅት ሌንጮ ለታ የተባለ 70 አመታት አማራን ያረደ ሰዉ ሽምጥጥ አድርጎ ክዷል። የአማራን መጨፍጨፍ የካደዉ ሌንጮ ለታ ጉዳይ አስገራሚ ነዉ። የሌንጮ ክህደት ብቻ ሳይሆን የሚገርመዉ የሚደራደሩት እርስ በርስ እየተታኮስን ያለንዉ እናንተ የአማራ ፖለቲካ ሀይሎች እና እኛ የኦሮሞ ፖለቲካ ሀይሎች ነን።

ስለዚህ መደራደራችን የመተከልን ግድያ ያቆመዋል ሲል በአማራ ፖለቲከኞች ላይ ተሳልቆባቸዋል።

የአማራ ፖለቲከኞች ሳያፍሩ ከነዚህ አይነት ከሃዲዎች ጋር ቁጭ ብሎ ይደራደራል። ገዳይ እና አስገዳይ ጨፍጫፊ እና አስጨፍጫፊ ኦነግ ነዉ። እንደራደር ብሎ የአማራ ድኩማን ፖለቲከኞችን ሆን ብሎ ስብሰባ ጠርቶ የሚያነጋግር እራሱ ኦነጋዉያን/ኦህዴዳዉያን ናቸዉ።

ዞረዉም ፕሮፖጋንዳ ከአማራ ፖለቲከኞች ጋር የተኩስ አቁም ድርድር አደረግን  እያለ ኦሮ አማራ መድረክ እያለ ይቀልዳል። ኦነጋዊ/ኦህዴዳዊ ለድርድር በአንድ ጨረቃ ሰባት ጊዜ ምሎ ሰባቴ መልሶ የመክዳት ልምድ ያዳበረ ነዉ ሲባሉ የማይሰሙት ነፍዝ የአማራ ፖለቲከኞች ምን አደረግን ብለዉ ወይም ምን ይሁን ብለዉ ለድርድር እንደሚቀመጡም አያዉቁትም።

ህዝባቸዉ ሲታረድ ቆመዉ የሚያሳርዱት የአማራ ፖለቲከኞች ከተቃዋሚ እስከ ብአዴን እናንተም ትተኩሳላችሁ ሲባሉ አዎን ብለዉ ለድርድር መቅረባቸዉ ህሊና ቢስ መሆናቸዉ መገለጫ ነዉ።

ኦሮ አማራ የሚባል የኦነጋዉያን/ኦህዴዳዉያን አማራን ለማረድ የህጋዊነት ሽፋን ማሳለጫ መድረክ ላይ እየተሳተፋችሁ ያላችሁ የአማራ ፖለቲከኞች ሁሉ ህዝብ አንድ ቀን አንቆ ከኦነጋዉያን/ኦህዴዳዉያን ጋር አብሮ ለፍርድ እንደሚያቀርባችሁ ግን አትርሱ።

 ስለ መተከል አያገባኝም፡ ስለ ደራ አያገባኝም ከኦነግ/ኦህዴድ ጋር ላለመጣላት እያሉ ሽህ ጊዜ የሚምሉት የአማራ ፖለቲከኞች ስለአማራ ህዝብ ጨርሰዉ የሚያዉቁት ነገር የለም። የአማራ ህዝብ እንኳን ደራ እና መተከልን መላዉ ኢትዮጵያን አጽመ ርስቱ ናት እና መልሶ እጅ ያደርጋታል። እናንተ ግን ከኦህዴድ/ኦነጋችሁ ጋር አብራችሁ ትቀበራላችሁ።

Filed in: Amharic