>
5:33 pm - Wednesday December 5, 2857

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ክስ...!?! ልጅ አቤል

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ክስ…!?!
ልጅ አቤል

በሳል አስተሳሰብ ያለው አመራር ወይም ስርአት አንድ እርምጃ ከመራመዱ በፊት ሁለት ሶስቴ ያስባል።  የዝች አለም የመጫወቻ ህግ በፍጥነት ከመቀየር አልፎ ውሸትን መደበቅ የማይቻልባት አለም ወደመሆን መታለች በተለይም ደግሞ በህዝብ ላይ የሚደረጉ ወንጀሎች።
የአገሪቱ መንግስት በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምን አይነት አማካሪወች እንዳሏቸው ወይም ሰውየው ከምን ተነስተው እንደሚያስቡ አላውቅም በእርግጠኝነትም ብዙ ሰወች ሀሳብ ሰተዋል ። መሪ አንዳንዴ ዜጎቸ ምን ይላሉ ብሎ ማዳመጥ አለበት በራሱ ብቻ ከመወሰን በፊት ካዛም አለፍ ሲል በዛሬዋ አለም ነገንም መተንበይ ቀላል መንገድ ሆኖዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከማንም በተሻለ የሰሜኑን ቀጠና ጠንቅቀው እንደማወቃቸው የሰሩትን ፋውል ላየ ደጋፊያቸው ካልሆነ በቀር ትልቅ ስህተት እንደሰሩ ያውቃል።
በጣም በቀላሉ አንድ የአገር መሪ ወደ ጦርነት እርምጃ ሲገባ ሶስት ነገሮችን ቀድሞ ያስባል ህወሓት ጀመረው አልጀመረው ጦርነት ጦርነት በመሆኑ
*ቀጠናዊ እውነታ ” surrounding situations)
*የአገር ሉአላዊ ግዛት ( country regional autonomy)
*የሚደርሰው ውድመት እና ውጤት 
አብይ አህመድ በሶስቱም ትክክል አልነበሩም ህወሓት ጦርነት እንደሚጀምር መቶ ፐርሰንት ያውቁ ነበር “ጦርነት እንደሚጀምር እናውቃለን ግን ደግሞ ይህን አይነት አሳፋሪ ድርጊት ያደርጋል ብለን አልጠበቅንም ) ነበር ያሉን ። ስለዚህ አንድ መሪ የሚመጣን አደጋ ካወቀ የፈለገው ታምር ቢሆን ይዘጋጃል በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ እንደሚመጣ ያውቃሉ ግን እንደ መሪ አልተዘጋጁም።
ሌላው የአገሪቱ ሉኡላዊ ግዛትን ፈፅሞ የረሱ ናቸው በእሳቸው ዘመን ላይ ያለ መሪ ይህን ማሰብ አለመቻሉ ብቻ ሳይሆን እየተነገረ አለመስማቱ ይደንቃል። አብይ አህመድ በነገሮች የመፍትሄ ሰው ከቶም አለመሆናቸውን በድጋሜ አሳይተዋል በቀጠናው ሰላምን ለመፍጠር ከጎረቤት አገራት ጋር ያደረጉት አካሄድ ” ሰውየው በመልመጥመጥ መንገድ ” የሄዱበት አካሄድ ከመከበር ይልቅ እንዳያስንቃቸው ስጋቴ ነው በሚል አንድ ኬንያዊ ጋዜጠኛ የሰጡት ጥልቅ ሀሳብ ገላጭ ነበር። ሰላምን መፍጠር ትክክል ነው ግን ደግሞ አብይ አህመድ እጅግ በጣም የቀለለ ማንነትን ይዘው በመቅረባቸው በቀጠናው ከመፈራት ይልቅ የመናቅ ፈተና ገጥሞዋቸዋል ካደረጓቸው የቀጠናው ውይይቶች ውስጥ አንዳቸውም ፍሬ አላፈሩም። ከዚህ ሁሉ በላይ ጦርነትን ያወቀ መሪ ጦሩን ወደ ግንባር እንደሚልክ ማወቅ ትንሹ ስራ ከመሆኑም አልፎ ቢያንስ አገሪቱን ለጎረቤት አገር ጦር ጠብቁልኝ ብሎ የሄደም ብቸኛው መሪ ነው ። ይህ ደግሞ በአለም ዙሪያም ታይቶ አይታወቅም ከአብይ አህመድ በቀር. ኮ/ል መንግስቱ ወደ ሶማሊያ ጦርነት ሲያመሩ በዛ ከባድ እና ፈታኝ ጦርነት ወቅት የወሰዱት እርምጃ ጦራቸውን ወደ ጦር ግንባር ቢያደርጉ እንኳን በሁለቱም ሱዳን ድንበሮች ድንበር ጠባቂ ሚኒሻ እና ጥቂት ወታደሮችን አስቀምጠዋል። አብይ አህመድ ጦሩን ወደ ጦር ግንባር ሲጠሩ ቢያንስ የአገሪቱን ድንበር ወይ በልዩ ሚኒሻ ወይ ለጊዜው ከሌሎች ክልሎችም ቢሆን ልዩ ሀይል አስጉዘው በሁለቱም ሱዳን ድንበር ማስጠበቅ ነበረባቸው ካዛ ይልቅ ሰውየው በአደራ ጠባቂ ታይቶ በማይታወቅ ቀይ ስህተት አገሪቱን ክፍት አረጓት ሱዳንም ገባች ከህወሀት የከበደ ሌላ ፈተና ውስጥ አሁን ከሱዳን ጋር ገቡ።
* ስለሚደርሰው ውድመት ቀድሞ አለማሰብ 
በእርግጠኝነትም ያውቃሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በየትኛውም መመዘኛ ዛሬ ላይ የሚደረጉ ጦርነቶች ከመቸውም ጊዜ በላይ አውዳሚ ናቸው ጦርነት ማን ጀምረው ማን ከጀመረ ጦርነት ነው በጦርነት ወቅት መሪወች ከፍተኛውን ሚና ይጫወታሉ በተለይም ደግሞ በእኛ አገር ከበቂ በላይ ልምዱም ጉዳቱም አለ። በሚደርሰው ማንኛውም ጉዳይ ተጠያቂው መሪወች ናቸው ይህ ለአብይ ብቻ አይደለም ለሁሉም አገራት መሪወችም ነው። አብይ አህመድ የመጀመሪያ እርምጃቸው መሆን ያለበት የአገሪቱን ሰላም ማስጠበቅ ነው ። አንዳንዶች እሱ ብቻውን ምን ያድርግ በሚል ሲጋተቱ እንሰማለን ሀይሉም አቅሙም አመራሩንም የያዘ መሪ እንደዚህ ተብሎ አይጠይቅም ጎረቤት አገራት ሳይቀር የኬንያ እና ታንዛኒያ መሪወች ፈተና ውስጥ ነበሩ ግዴታቻው ስለነበር መፍትሄ አመጡ። ብቻውን የሚባል ነገር የለም ለመሪ መሪ አገርንም ያቀናል አገርንም ያወድማል። አይደለም መለስተኛ ግዛት ያላት ኢትዮጵያን ይቅርና ግዙፍ አገራት እና ህዝብ የያዙ መሪወች መሪ እስከሆኑ ድረስ በማንኛውም ነገር በአገራቸው ጉዳይ ተጠያቂ ናቸው። አብይ አህመድ ትልቁ ችግራቸው በራስ የመተማመን ችግር ይመስለኛል ዛሬ ላይ ከአንድ መቶ አስር ሚሊዮን ህዝብ እና አቅም አለ ዛሬ ላይ የመሪው ስራ የዚህን ህዝብ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ሞቢላይዝድ ማድረግ ነው እንኳን ዛሬ ትናንት በታሪካችን ሶስት ሚሊዮን በማይሞላ ህዝብ የአገሪቱን ድንበር ታድገዋል።
አሁንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጣም ይቸኩላሉ ባለፈው ሰሞን የአለም ሚዲያን ማስገባት ከፈለጉ ቀድመው መውሰድ ስላለባቸው ዝግጅት በሚገባ እኔም ሀሳብ ሰጥቻለሁ ብዙወችም ሰተዋል። እሱ ብቻ አይደለም ተመልሳችሁ አንብቡ አብይ አህመድ ቅድመ ጥንቃቄ ሳያደርጉ ከፈቀዱ ስለሚመጣው ጉዳይም አስቀምጫለሁ። አሁን ሁለቱንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሳያደርጉ በራቸውን እንደ በጣም ታች ያለ መሪ ከፈቱ።
በጦር ወንጀል መጠየቃቸው እንደማይቀር ከወዲሁ አምነስቲ ያወጣውን ዛሬ ተመልከቱ በጦር ወንጀል ከተከሰሱ ደግሞ እጅግ አደጋ ውስጥ መግባት ብቻ አይደለም ፈታኝ ጊዜ ይጠብቃቸዋል ይህን ያለው ልጅ አቤል አይደለም አምነስቲ ኢንተርናሽናል ነው war crime ተፈፅሞዋል ሲል ዛሬ ያወጣው ይህ እጅግ እጅግ መጥፎ ከመሆን አልፎ አሁብንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካላስተዋሉ ገፍቶ መቶ ሄግ ፎት እንዳያቆማቸው የሚሰጉ አሉ። በመተከል በማይካድራ ጉዳይ ገና እጅግ ውስብስብ ክሶች ከፊታቸው ተደቅነዋል። በራቸውን ከፍተው ያስገቧቸው አለማቀፍ ሚዲያወች የፈረንሳዩ ፍራንስ ሀያአራት ያወጣውን ዘገባ ተመልከቱ።
አሁንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢያስተውሉ ባይ ነኝ ዘላቂ መፍትሄን እንጅ ይበልጥ ለውድቀት የሚዳርጉ ሂደቶችን ባይመርጡ። አሁንም ድረስ በሱዳን ጉዳይ እያሳዩት ያለው ትልቅ የስህተት አቋም ወደባሰ ችግር እንዳይጥላቸው እሰጋለሁ። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እባከወን ያስተውሉ ።
Filed in: Amharic