>

አዲስ አበባ የራሷ ልጅ እንደሌላት የመቁጠር አባዜ...!!! (ሀብታሙ ምናለ)

አዲስ አበባ የራሷ ልጅ እንደሌላት የመቁጠር አባዜ…!!!

ሀብታሙ ምናለ


በዚህ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ አንድ የክልል ተወላጅ ብልፅግናን ወክሎ ለአዲስ አበባ ም/ቤት እንደሚወዳደር በመግለጽ፣ ለዚህ ውሳኔ  ያበቃው በተወለደበት አካባቢ አሁን ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት መወዳደር እንዳልቻለ፣ በአቅራቢያው ካለ በሌላ ምርጫ ወረዳ ያልተወዳደረው ደግሞ በክልሉ አቅም ያላቸው ሰዎች እጩ ሆነው ስለቀረቡ ለእነሱ እድሉን ለመስጠት በማሰብ እና አዲስ አበባ ላይ ያለውን ከባድ ችግር  በመረዳት ችግሩን ለመፍታት በመወሰኑ በአዲስ አበባ ከተማ የብልፅግና እጩ በመሆን እንደሚወዳደር ፅፏል። የብልፅግና የእጩው ዋና ዋና ጉልህ ስህተቶች ብዬ የማስባቸው
ስህተት አንድ
• የአዲስ አበባ ልጆች የዘንድሮ ዋና አላማው ብልፅግና የሚባለውን በሕብረብሔራዊነት ካባ  ተጀቡኖ ብሔርተኝነትን እያራመደ፣ የሕዝቡን መብቶችና ጥቅሞች በመንጠቅ ደሃውን ያስለቀሰውን ፓርቲ ማስወገድ መሆኑን ረስቶታል።
ስህተት ሁለት
• የኦሮሞ ብልፅግና አዲስ አበባ ላይ ለሚሰራው ዝርፊያና የተረኝነት ስሜት የህዝቡን ሰቆቃ በየቀኑ እንዲጨምር  ድጋፍ ሰጪው የአማራ ብልፅግና  መሆኑን አለመረዳቱ፣
ስህተት ሦስት
• የዘንድሮ ትግል አዲስ አበባ ለሥልጣን ወደ ከተማ ለመጡ ሳይሆን ከተማዋ ላይ ባሉ በራሷ በነዋሪዋ እንድትተዳደር እየታገለች መሆኑን፣
ስህተት አራት
• በተወለደበት አካባቢ ለወንዜ ወዳጅ እጩዎች “አቅም አላቸው!” በማለት እንዲወዳደሩ የመወዳደሪያ መድረኩን ለቆ እዚህ መጥቶ የከተማዋን ተወላጆች ኮታ ለመቀማት እየጣረ መሆኑን “ይመርጠኛል!” ለሚለው ለሸገር ህዝብ በድፍረት እየተናገረ መሆኑን ለሰከንድ ቆም ብሎ አላሰበም። – አቤት ድፍረት …..
ስህተት አምስት
• ተወዳዳሪው ያለው ፕሮፋይል (ዶክተር፣ ፕሮፌሰር፣ መምህር ጸሐፊ፣ አርቲስት….) ለሸገር ሕዝብ ማማለያ ሊሆን፣ ተመራጭ ሊያደርግም እንደማይችል አልተረዳም።
የሸገር ሕዝብ ከዚህ በኃላ ባለሀብት ብትሆን፣ ታዋቂ ጋዜጠኛ፣ አርቲስት፣ የሀገር ሽማግሌ፣ ጉምቱ የሃይማኖት መምህር፣ ብዙ ደጋፊና ተቀባይነት ያለህ እንኳን  ብትሆን ጥያቄው የሸገር ልጅ ቁጭት ገብቶሃል ወይ? የደረሰበትን በደል ምን ያህል ተረድተህ መፍትሔ ምን ይዘኻል? የሚል ሲሆን ከክልል መጠተህ አዲስ አበባ ላይ  ሥልጣን ብታገኝ ከክልል ዘመድ አዝማድ በማምጣት አሁንም የሕዝቡን ስቃይ ስለምታስቀጥል ማንም ሊመርጥህ አይችልም።
•ኢትዮጵያ
•አዲስ አበባ
•ሸገር
•አዱ ገነት
Filed in: Amharic