>

አገር ሲያረጅ ጃርት ያበቅላል...!!! (መርእድ እስጢፋኖስ)

አገር ሲያረጅ ጃርት ያበቅላል…!!!

መርእድ እስጢፋኖስ

*…. አማራ በሁለት መንገድ ይጨፈጨፋል አንዱ በአማራነቱ ሲሆን ሁለትም በሀይማኖቱ ነው። በከሚሴ በደረሰው ጭፍጨፋ መሀመድ ሊበን የተባለ ጎልማሳ ፀንፈኞቹ የኦሮሙማ ወታደሮች ሊገሉት ወደሱቁ ገብተዋል እናም እስላም በመሆ  ተውት ግን” ሽሀዳ” (ማለትም በእስላምኛው ንስሀ እንደመግባት መለት ነው) እስኪያደርግ ጠበቁትና ሲጨርስ “አማራ በመሆንህ ግን ” ልንተውህ አልቻልንም ብለው በ13 አመቱ  በዛው ሱቅ በተደበቀ ልጁ ፊት ገለውት ሄደዋል።

ከአጣዬ ተነስቶ ካራቆሬ እና ማጀቴ በስተደቡብ ደግሞ  ጀውሀ እና ሽዋሮቢት የደረሰው የአማራ ብሄረሰብ ጭፍጨፋ እና ማፈናቀል ዛሬ ሳምንት ሳይሞላው ገና በ3 ተኛ ቀኑ ልንረሳው ችለናል።
በየጎዳናው የወድቁት ወገኖቻችን ሬሳቸው እንኳ አፈር ሳይቀምስ የብልፅግና /አዴፓ ተብዬው በነዚሁ ቀበሌዋችና ከተማዎች የምርጫ ቅስቀሳ ጀምሯል።
አዎ  መኖርን ሳይሆን መጨፍጨፍን እንደመብታችን ተቀበሉ እያሉን ነው የአማራ ብልፅግና አመራሮች።አማራው በ27  አመት የወያኔ አገዛዝ ውስጥ   አስቀድሞ  ትጥቅ እንዲፈታ ያደረጉት ። የወያኔ አገልጋይ የነበሩት እነሱው እራሳቸው ወያኔ በወጋቻቸው ቫይረስ  ለዘመናት ሲሰቃዩ ቢቆይም ከወያኔ ውድቀት በኋላ ደማቸው ውስጥ ያለውን ቫይረስ አስመጥጠው ይደፉታል ስንል ኦሮሙማ የሚባል ሌላ ቫይረስ ጨመሩበትና አርፉት።
አሁን በጎን የአማራ ህዝብ  ታክስ ከፋይ በሚከፋላቸው ደመውዝ ቅንጡ ህይወት እየኖሩ ከጌቶቻቸው ከአብይ አህመድ  ከሽመልስ አብዲሳ በሚሰጣቸው ትእዛዝ አማራን እየገደሉ እና እያስገደሉ ቀጥለዋል። ከከሙሴ እስከ ሽዋሮቢት ድረስ ቢያንስ በጥቅሉ 400 የሚደርስ የአማራ ተወላጅ ተጨፍጭፎአል። የቁስለኞች ቁጥር ምን ያህል እንደሆነ ገና አልታወቀም እንደዚሁም ደግሞ የደረሰው የተቋም እና የንብረት ውድመት አልታወቀም። የዘረፋው መጠንም አልታወቀም።
አሁን ተስፋ ቆርጥርናል።በመሪዎቻችንም አፍረናል።ተከድተናል ከዚህ በኋላ ላለመገደችንም ዋስትና አጥተናል።ሆዳሞቹ የአማራ ኢሊቶች ልክ እንደ አብይ አህመድ ሁሉ ሰሞኑን በሰሜን ሽዋ የተፈፀመውን ድርጊት አታራግቡት በማለት ይገኛሉ።
የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ አገኘሁ ተሻገር አጣዬና ማጀቴ ውይም ጀውሀ ከተማዎች መጥተው ቢያንስ ያፅናኑናል ብለን ስንጠብቅ “መተከልም” አልሄድኩም ብለው መናገራቸው መሰማቱ እጅግ አሳፋሪ ነው።አዎ መተከል ቢሄዱና ወገናቸውን ቢፅናኑ ታላቅ ጀግንነት ይሆን ነበር።ታላቅ ወገናዊነትን ማሳየት በሆነ ነበር። ነገር ግን ቤንሻንጉል ጉምዝ ሆነና አቶ ሽመልስ አብዲሳና ታዬ ደንዳአን ካለማስቀየም ሲሉ ባህር ዳር ላይ  ሆነው በትህትትና አማራዎች መሞት እንኳ መናገር አልደፈሩም።
እስኪ ይታያችሁ አሁን ግን በክልላችን በራሱ በአማራ ክልል ላይ ነው ይህ ሁሉ ጭፍጨፋ የተካሄደው።አቶ አገኘሁ ተሻገር በርሳቸው ክልል ላይ ለተከሰተው ኢሰበዊ ድርጊት ሀዘናቸውን ለመግልፅ የአብይ አህመድን  ፈቃድ መጠየቃቸው ሲስቡት ከአይምሮ በላይ ነው።
የሚሳዝነው የአማራ ኢሊቶች አስቀድሞ ተላላኪ ሆኑ ።ቀጥሎ ተጋላቢ አህዮች ሆኑ ።አሁን ደግሞ “የተመረጡ ባሪያዎች ሆነዋል”
እናም ከዚህ ኢሊት የሚጠበቅ  አንዳችም ነገር የለም። አማራውን ትንሽ በትንሽ የማስጨረስ አጀንዳም የአማራው አመራሮች ጥምር የኦሮሙማ ፕሮግራም ነው ።አማራው ከዚህ በኋላ መኖር ካለበት መጀመያ መዝመት ያለበት በራሱ በሆዳም አማራው አመራር ላይ ነው። የኦሮሙማን ህያው ውክልና የያዘ ትንሽ እንጥፍጣፊ አማራነት ሰብእና እንኳ የሌለው በመሆኑ “የአማራው ህዝብ በህወት መቀጣል ካለበት ሁሉም በየቦታው መደራጀትና ራስን ለመከላከል መዘጋጀት ግድ ይለዋል።
በሁሉም የኢትዮጵያ ግዛቶች ተገፊው አማራ ነው ተፈናቃዩ አማራ ነው።ተጨፍጫፊው አመራ ነው። አማራ በሁለት መንገድ ይጨፈጨፋል አንዱ በአማራነቱ ሲሆን ሁለትም በሀይማኖቱ ነው።
በከሚሴ በደረሰው ጭፍጨፋ መሀመድ ሊበን የተባለ ጎልማሳ ፀንፈኞቹ የኦሮሙማ ወታደሮች ሊገሉት ወደሱቁ ገብተዋል እናም እስላም በመሆ  ተውት ግን” ሽሀዳ” (ማለትም በእስላምኛው ንስሀ እንደመግባት መለት ነው) እስኪያደርግ ጠበቁትና ሲጨርስ “አማራ በመሆንህ ግን ” ልንተውህ አልቻልንም ብለው በ13 አመቱ  በዛው ሱቅ በተደበቀ ልጁ ፊት ሊገሉት ችለዋል።
አዎ ከህውይማኖትና ከዘር ውጭ ሲሆን ደሞ ታርክ መቶ አመት ወደኋላ ተመልሶ “የታሪክ ባለእዳ “ተደርጎ ይገደላል።ታሪክን ሲጨርሱ የኢትዮጵያና የባንዲራ ፍቅር ስላለህ ተብሎ ይገደላል። አማራን ላለመግደል ምክንያት የማይሆነው ነገር” ኦሮሙማ ሰማይ ላይ ላይኖር ነው”…..ዛሬን እንዴት እንለፋት…ነገ ላይስ እንዴት እንድረስ …..? ይቀጥላል

Filed in: Amharic