አርአያ ተስፋ ማርያም
አክቲቪስት ስዩም ተሾመና አክቲቪስት ሚክታሮቪች በትላንትናው እለት፣ ከምሽቱ አንድ ሰአት ግድም ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች የግድያ ሙከራ እንደተፈፀመባቸው የአይን እምኞች አስታውቀዋል። እነስዩም የተሳፈሩበትን መኪና መንገድ ዘግቶ ካስቆማቸው አምቡላንስ የወረዱና አንዱ ሬንጀር ጄኬት የለበሰ እነስዩምን ከመኪናቸው በሃይል ካስወረዷቸው በኋላ በአምቡላንሱ ጭነው፣ የአደጋ ጥሪ እያሰማ በፍጥነት ወደ ጎሮ አቅጣጫ ካመራ በኋላ ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈጸመባቸውና ስልካቸውንና የያዟቸውን ዶክመንቶች እንደወሰዱባቸው ታውቋል። በሰዎች እርዳታ ወደየረር ሆስፒታል ተወስደው በህክምና ላይ ይገኛሉ። ሃሳብን በሃይልና በግድያ ለመጨፍለቅ የሚደረግ እንቅስቃሴ በጥብቅ የሚወገዝ ነው! ሃሳብን በሃሳብ ማሸነፍ ያቃታቸው ድዊዎች የግድያ ሙከራ ለማድረስ መንቀሳቀሳቸው አስደንጋጭ ብሎም አሳሳቢ ነው! የሚመለከተው የመንግስት አካል እነዚህን ወንበዴዎች በአስቸኳይ ለፍርድ ማቅረብ ይኖርበታል! የሃሳብ ነፃነት ይከበር!!