>

አሳዳጁና ተሳዳጁ በአንድ ታዛ ሥር ...!?! (እስክንድር_ነጋ የህሊና እስረኛ ከቃሊቲ)

አሳዳጁና ተሳዳጁ በአንድ ታዛ ሥር …!?!

እስክንድር ነጋ የህሊና እስረኛ ከቃሊቲ

“….ቀድመው ወደ ግቢው የገቡት  ስብኃት ነጋ ነበሩ። በአካል ሳያቸው ለሁለተኛ ግዜ መሆኑ ነው። የመጀመሪያ ግዜ የት እንዳየኃቸው አሁን አላስታውስም። ያኔ እንደአሁኑ በቅርበት ሳይሆን በርቀት ነበር ያየኃቸው። በጠባቂዎች ተከበው፣ ሙሉ ሰውነት ይዘው፣ ቀኝ እጃቸውን ኪሳቸው ውስጥ ከትተው፣  በልበ ሙሉነት  ፈጠን ፈጠን ብለው ሲራመዱ ነበር ያየኃቸው። አሁን እኛ ስብኅት የሉም። የሚራመዱት በግድ ነው። አንድ እርምጃ ተራምደው ወደ ጎን፣ ሌላ እርምጃ ተራምደው ወደጎን ይናጣሉ። በዕድሜ ይሁን በመጎሳቆል መለየት ባልችልም፣ ሰውነታቸው አልቁዋል። ዓይናቸው ቢያይም፣ መለየት እንደሚቸገሩ በግልፅ ያስታውቃል። ፊት ለፊት ሲያገኙኝ እጃቸውን ዘረጉልኝ። በሁለት እጆቼ ጨበጥኩዋቸው። ሳላስብ በደመነፍስ ያደረኩት ነበር። በኅላ ላይ ቆንጥጠው ያሳደጉኝን እናቴንና አያቴን አመሰገንኹ። ጨዋነት የኢትዮጵያዊነት መገለጫ ነው።
“ደህና ነህ?” አሉኝ ከእኔ ይልቅ ወደ ክፍላችን መግቢያ በአግራሞት  እየተመለከቱ።  ፊት ለፊታቸው የሚራመደውን ፖሊስ እየተከተሉ።
“ደህና። ቀስ ይበሉ፣ አቦይ” አልኩዋቸው በትህትና …..”  https://youtu.be/cyr5RdrSTyQ
Filed in: Amharic