>

መጪው የምርጫ ውድድር ለኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ችግሮች መፍትሔ ያመጣ ይሆን ? ደረጀ መላኩ (የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች)

መጪው የምርጫ ውድድር ለኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ችግሮች መፍትሔ ያመጣ ይሆን ?

 

ደረጀ መላኩ (የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች)

Tilahungesses@gmail.com

 


መግቢያ

ምንም እንኳን አለም አቀፉ ህብረተሰብ እና የታወቁ የአለም መገናኛ ብዙሃን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር የተሃድሶ ለውጥ ያደነቋቸውና ያንቆለጳሷቸው የነበረ ቢሆንም( የጠቅላይ ሚንስትሩን የለውጥ ሂደት በተመለከተ የምእራቡ አለም የታወቁ ሚዲያዎችና ምእራባውያን መንግስታት የነበራቸውን የሙገሳ ቃላት ልብ ይሏል) በውስጣዊና ውጫዊ ምክንያቶች የተነሳ ጠቅላይ ሚንስትሩ በተደበላለቀ ውጤት ውስጥ ያሉ ይመስላል፡፡ ይህ አጭር ጽሁፍ the adverse impacts of a fractured፣ ruling party፣ በየጊዜው እያገረሸ ስላለው አለመረጋጋት፣የርእዮት አለም ambivalenceስለ ዲሞክራቲክ ተቋማት አለመጠናከር፣ገዢው ፓርቲ ህጋዊነት ለመላበስ ስላለው ፍላጎት፣የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች ስልጣን የመጋራት አስፓይሬሽን፣ስለ ህዝቡ የዲሞክራሲ ጥማት ( ፍላጎት)፣ የአናሳ ቡድኖች ኤክሳይትመንት minorities’ excitement for inclusion are favorable conditions with spillover effects to the Horn region፣ ለመዳሰስ ይሞክራል፡፡ ምንም እንኳን በተለያዩ ስፍራዎች የጸጥታው ሁኔታ አሳሳቢ ቢሆንም በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው የዲሞክራቲክ ስርዓት ግንባታ ተስፋ አስቆራጭ አይሆንም፡፡ በሌላ አነጋገር በኢትዮጵያ የዲምክራሲ ስርዓቱ ግንባታ ተስፋ አስቆራጭ ነው ለማለት ጊዜው ገና ነው፡፡ ስለሆነም የምእራቡ አለም ኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት እንድትገነባ ሊረዳት ይገባል የሚል ሀሳብ አለኝ፡፡

የፖለቲካው መሻሻል ለውጥ ሂደት (The state of political reform )

ኢትዮጵያ የአምባገነንት ታሪክ ያላቸው አገዛዞች ታሪክ ባለቤት ናት፡፡እነኚህ አምባገነኖች አልፎ አልፎ የፖለቲካውን ምህዳር ሲያሰፉት ይታያሉ፡፡ ባለፉት ዘመናት በነበሩት የምርጫ ሂደቶች ውጤታቸው የታወቀ ነበር፤ የምርጫው ውጤት ከተሰማ በኋላ የምርጫውን ውጤት አንቀበልም በማለት አደባባይ ከወጡ ዜጎች በርካታዎች ታስረዋል፣ ጥቂት የማይባሉት ደግሞ ተገድለዋል፡፡ ጠንካራ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲፈርሱ ተደርገዋል፡፡ በነገራችን ላይ ባለፉት አመታት በፖለቲካ ጭቆና ምክንያት ሀገሪቱ መረጋጋት ተስኗት ቆይታ ነበር፡፡ ኢትዮጵያን ለሃያ ስምንት አመታት እንደ ሰም አቅልጠው እንደ ብረት ቀጥቅጠው የገዙት የሕውሃት የፖለቲካ ፊትአውራሪዎች 99 ፐርሰንት የፓርላማ ወንበርን ጠቅልለው ከወሰዱ በኋላ የህዝብ አመጽ እየተቀጣጠለ በመምጣቱ ነበር ዶክተር አብይ ለስልጣን ያበቃቸው፡፡( የውስጥ ትግሉ ሳይዘነጋ ማለቴ ነው)

ዶክተር አብይ ጠቅላይ ሚንስትር ከሆኑ ወዲህ የፖለቲካ አንድነት እንዲኖር፣ ከብሔር ፖለቲካ ባሻግር አማራጭ የፖለቲካ አስተሳሰብ እውን እንዲሆን፣የኢኮኖሚ መነቃቃት ( ለውጥ) እንዲኖር፣ኮቪዲ በሽታን ከመከላከል አንጻር፣ በታላቁ የአባይ ግድብ ላይ ጊዜውን ጠብቆ የመጀመሪያው የውሃ ሙሊት ስራ በመካሄዱ፣ በከተሞች ላይ የመዝናኛ ስፍራዎች በማሰራታቸው፣ የወንዝ ዳር አረንጓዴ ልማት፣ የህውሃት የፖለቲካ ፊትአውራሪዎች ከዋና መቀመጫቸው መቀሌ ከተማ በአጭር ግዜ ውስጥ ለቀው እንዲወጡ በማድረጋቸው ( የህውሃት ህልውና በአጭር ግዜ ውስጥ መክሰሙ ( ቢያንስ አመራሩ ሞቷል ማለት ይቻላል) ወዘተ መልካም ተግባራቸው እንደሆነ በርካታ የፖለቲካ ተንታኞች የሄሱት ጉዳይ ይመስለኛል፡፡

ምንም እንኳን ይሁንና ከ 30 ወራቶች የስልጣን ቆይታ በኋላ ሙስና ፣የመልካም አስተዳደር ችግሮች በብዙ ቦታዎች ይታያሉ፣በትግራይ ክልል እየተራዘመ የመጣው ጦርነት ከአለም አቀፉ ህብረተሰብ ድጋፍ እየተነፈገው ይገኛል( በተለይም ከምእራቡ አለም)፣በአገዛዙ ፓርቲ ጥላ ስር ያሉት ዋና ዋና ፓርቲዎች ህብረት ፍንትው ብሎ አለመውጣቱ፣ከግዜ ወደ ግዜ እየባሰበት የመጣው የጸጥታ ሁኔታ መጪው ግዜ ምን ይሆን በሚል ምክንያት ህዝቡን ስጋት ላይ ጥሎታል፡፡ ስለሆነም መጪው የምርጫ ግዜ ከመድረሱ በፊት ቃል የገቡትን ሁሉ በነቢብም በገቢርም እንዲያሳዩ በርካታ ታላላቅ ኢትዮጵያውያን እየጠየቁ ይገኛሉ፡፡ ለአብነት ያህል መጪው 6ኛው ሃገር አቀፍ የምርጫ ውድድር ነጻ፣ገለልተኛ፣ተአማኒ እና ፍትሃዊ እንዲሆን መንግስታቸው በርካታ የቤት ስራዎችን ከወዲሁ ማጠናቀቅ ይጠበቅበታል፡፡ በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍል ያለውን አሳሳቢ የጸጥታ መደፍረስን መቆጣጠር፣ ሰላም ማስከበር የመንግስት ሃላፊነት ነው፡፡ ብሔርተኝነት ጫፍ ደርሷል፣ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ኑሮ እያዳፋ ወደ ተለያዩ ክልሎች በመሄድ የሚኖሩ ( ኑሮ ከተባለ ማለቴ ነው፡፡) የመምረጥና መምረጥ መብት ቀርቶ በህይወት የመኖር መብታቸው በአሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡( ለአብነት ያህል በኦሮሚያ ክልል ወለጋ እና ቤንሻንጉል ክልል፣መተክል ዞን ብረት ባነገቱ ቡድኖች የሚፈጸመው አስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ማሳያ ነው፡፡) ስለሆነም መንግስት የገባውን ቃል ገቢራዊ ሳያደርግ የምርጫ ውድድር ገቢራዊ የሚያደርግ ከሆነ ሀገሪቱ ችግሮች ውስጥ ልትወድቅ ትችላለች፡፡

የተከፋፈለ የአገዛዝ ፓርቲ ለውጥ ለማምጣት ይቸገራል

ከ27 ዓመታት በላይ በስልጣን ኮርቻ ላይ ተፈናጠው የነበሩት የወያኔ የፖለቲካ ፊትአውራሪዎች፣ ሌሎች የትግል አጋሮቻቸው ‹‹ ኢህአዲግ›› የተሰኘውን ፓርቲ ስም መጠሪያ ወደ ጎን ገሸሽ በማድረግ ‹‹ ብልጽግና ›› በሚል አዲስ የፓርቲ ሰም የህብረት ችቦ ለኩሰናል ባሉ ማግስት እራሳቸውን ገሸሽ በማድረግ መቀሌ ከተማ ላይ መቀመጣቸውን፣ ራሳቸውን ለማእከላዊ መንግስት ታዛዥ ባለማድረግ ፣ እንዲሁም የሀገሪቱን ሕገመንግስት በመጣስ በመጨረሻም የሀገሪቱን ድንበር ይጠብቅ በነበረው የሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ከከፈቱ በኋላ በሀገር መከላከያ ሰራዊት በተከፈተባቸው መልሶ ማጥቃት፣ ህልውናቸው ያከተመ ይመስላል፡፡ ግራም ነፈሰ ቀኝ እነርሱ ( የሕውሃት ሃይል) ከብልጽግና ፓርቲ ጋር ህብረት ባይፈጥሩም ሌሎች የብልጽግና ፓርቲ አባል ፓርቲዎች በመጀመሪያዎቹ አመታት መልካም ህብረት ስለነበራቸው እንዲሁም በባለፈው የወያኔ-ኢህአዲግ አገዛዝ የአጋር ፓርቲ አባል ተብለው የሚታወቁት፣ የብልጽግና ፓርቲ አባላት እንዲሆኑበሀገሪቱ በርካታ የፖለቲካ ለውጦች ስለመምጣታቸው ብዙም የሚያከራክር አይመስለኝም፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና ከተወሰኑ ወራቶች በኋላ በመሃከላቸው ስላለው ህብረት በግልጽ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ በአንዳንድ የሀሪቱ ክፍሎች የተረኝነት ስሜት ይታያል የሚሉ ዜጎች በርካታ ናቸው፡፡ ግፍ እየበዛ ነው፡፡ ከአንድነት ይልቅ ልዩነት እየሰፋ ነው፡፡ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ እርዮትአለም፣ በመደመር ርእዮት አለም ከመቀየሩ ባሻግር፣ የተቀየረው ርዮትአለም በህዝቡ ዘንድ ግንዛቤ መፍጠር የቻለ አይመስለኝም፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች የስርአት አልበኝነት መስፋፋትና ዲስፕሊን አለመኖር፣ህብረብሄራዊ አንድነት እንፈጥራለን ቢባልም፣ አሁን ድረስ የብልጽግና ፓርቲ በብሔር ድርጅቶች የተዋቀረ መሆኑ፣በአዲስ አበባ የባለቤትነት ጉዳይ ያለው እሰጥ እገባ እልባት ባለማግኘቱ፣ የሕግ መንግስቱ መሻሻል በተመለከተ ምንም አይነት ፍንጭ አለመሰጠቱ፣ የዶክተር አብይ ጠንካራ ደጋፊ የነበሩት አንዳንዶች ዛሬ ድምጻቸው መጥፋቱ፣አክራሪ የኦሮሞ ብሔርተኞች የያዙት አቋም በሌሎች ለዘብተኛ የኦሮሞ ፖለቲከኞች እና ሌሎች የብልጽግና ፖለቲካ ፓርቲ አባል ድርጅቶች አባላት ዘንድ ወይም የዲሞክራቲክ ጽንሰ ሃሳብ አራማጅ በሆኑት የብልጽግና ፓርቲ አባላት ላይ ፍርሃትን ጥርጣሬን ማሳደሩ፡፡ ወዘተ ወዘተ በተጠቀሱት ምክንያቶችና ሌሎችም ምክንያቶች ተጨምረው ለለውጥ ደንቃራ ፈጥረዋል፡፡

የዶክተር አብይ መንግስት ምናልባት የትግራዩን ነጻ አውጪ ድርጅት አሸንፈው ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና የትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት የርእዮት አጋር እና ሰትራቴጂክ ወዳጅ የሆኑ ሀይሎች በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ሰላም ሲያደፈርሱ ይታያሉ፡፡ አንዳንድ ሀይሎች ደግሞ የትግራይ የበላይነት ፣ በኦሮሞ ፖለቲከኞች ተተክቷል በሚል መንግስታቸውን ሲከሱ ይሰማል፡፡ በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች በየጊዜው ለሚያገረሹ ረብሻዎችና ግጭቶች፣ እንዲሁም አስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለመግታት፣ መንግስታቸው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት መስጠት ባለመቻሉ የተነሳ በርካታ ሰዎች ተስፋ እየቆረጡ ይገኛሉ፡:

የረብሻና ግጭቶች መበራከት፣ለሰላምና መረጋጋት ጠንቅ ነው

ብሔርንና ቋንቋን ማእከል ያደረገው የኢትዮጵያ ህገመንግስት ኢትዮጵያን አደጋ ላይ የሚጥል የማእዘን ድንጋይ ነው፣ ወይም በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚፈጸሙ ግፎች የማእዘን ድንጋይ ነው ተብሎ ቢጻፍ ስህተት አይመስለኝም፡፡

The ethnolinguistic constitution remains the bedrock of Ethiopia’s existential threat.

ሁላችንም እንደምንገነዘበው የኢትዮጵያው ህገመንግስት በእኩል ዜግነት ላይ የተመሰረቱ የፖለቲካ ክልሎችን ፈጥሯል፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና የክልሎች መሰረት ኋላቀር በሆነው ብሔር እና ቋንቋ ላይ መሰረት ማድረጉ ነው ዚቁ፡፡ በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎች ያለው ሁኔታ አስደንጋጭ ነው፡፡ ለአብነት ያህል ለሀገር ታማኝ ከመሆን ይልቅ ለባህላዊ ቡድን ታማኝ መሆንን የሚመርጡ በርካቶች ናቸው፡፡ ብሔራዊ አንድነትን ችላ ያሉ ኢትዮጵያዊ ወንድሞች ቁጥራቸው መጠን የለውም፡፡ በራሳቸው የብሔር ፖለቲካ ኤሊቶች ማህበር ዙሪያ መሰባሰብን ስራዬ ብለው መያዝ ከጀመሩ ውለው አድረዋል፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች የሚኖሩ ቁጥራቸው አንሰተኛ የሆኑ ኢትዮጵያውያን መብታቸው የተገደበ ነው፡፡ ይህም ብቻ አይደለም ከማህበራዊ ህይወትም እንዲገለሉ የተደረጉ አሉ፡፡ በአጭሩ ይህ የእኛ ክልል ነው በማለት በአንዳንድ ክልል የሚገኙ ባለስልጣናት የግለሰቦቸን ዴምክራሲያዊ መብቶች ሲጥሱ ማየት ብርቅ አይደለም፡፡ መሰረቱን ቋንቋ እና ብሔር ላይ ያደረገው ህገመንግስት ለግለሰብ መብት መጣስ በር የሚከፍት ነው፡፡

ብሔርተኝነት ባቆጠቆጠበት (በጎመራበት) የፖለቲካ አውድ ውስጥ ዘውገኝነት የአመራር ቦታውን ይይዛል፡፡ ይህም ማለት፡-

 • ፖለቲካው
 • የምጣኔሀብት
 • ትምህርት
 • ሌሎች ማህበራዊ ጥቅሞች  ለማግኘት ወዘተ በዘውግ አባልነት ላይ ሊንጠለጠሉ ይችላሉ፡፡( የአንድ ዘውግ አባል የሆነ ግለሰብ በሌላው የዘውግ ክልል ነዋሪ ከሆነ የሰብዓዊ መብቱ ምሉሄበኩልሄ በሆነ ሁኔታ ሊከበርለት አይቻለውም)  ለዚህም ነው የሀገሪቱን ብሔራዊ ኬክ በበላይነት ለመውሰድ በዘውግ ፖለቲከኞች መሃከል ሽኩቻ የሚታየው፡፡ ባለፉት 28 አመታት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሀብት ላይ አዛዥ ናዛዥ አነማን ነበሩ ?ዛሬስ ? ህሊና ያላችሁ ጠይቁ፡፡

ይህ በእንዲህ እያለ በተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች መሃከል ያለው የታሪክ አረዳድ ( ስለ ኢትዮጵያ ጥንታዊ ታሪክ ማለቴ ነው) እጅጉን የሰፋ ነው፡፡ ይህም ብቻ አይደለም አስደንጋጭም ነው፡፡ በዚህ ምክንያት የሀገሪቱን መጻኢ እድል አሳዛኝ ያደርገዋል፡፡ የጎሳ፣ፖለቲካ እና ሀይማኖት መደበላለቅ ለዘመናት ተቻችሎ በኖረው ህዝብ ላይ ስጋት ውስጥ እንዲወድቅ ጥላ እያጠላበት ይገኛል፡፡ እንደ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የመሳሰሉ የመብት አስከባሪዎች በየጊዜው በሚያወጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ( ላለፉት 29 አመታት በኢትዮጵያ ምድር በብቸኝነት የኢትዮጵያን የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታን በተመለከተ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ መደበኛ እና ልዩ መግለጫዎችን እንደሚያወጣ ልብ ይሏል፡፡) አበክረው መንግስትን እንደሚያሳስቡት የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳይፈጸም መንግስት በብርቱ መከላከል አንዳለበት፣ ከተፈጸመም በኋላ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጻሚዎችን ወደ ፍትህ አደባባይ ከማቅረብ አኳያ አስቸኳይ መፍትሔ መስጠት ከተሳነው የሀገራችን የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ከድጡ ወደ ማጡ መዶሉ አይቀሬ መራር ሀቅ መሆኑን ሳያሰልሱ ይወተውታሉ፡፡ ከዚህ ባሻግር ለዘመናት የነበረው የሃይማኖት መቻቻል እየከሰመ ከመጣ ወይም የሃይማኖት ጽንፈኝነት ከተቀጣጠለ፣ጎሳን ማእከል ያደረጉ መገናኛ ብዙሃን ስለ ጎሰኝነት መርዛቸውን መርጨታቸውን ከቀጠሉበት፣ የክልል ሚሊሻዎች ቁጥር መጨመር የሀሪቱን አንድነት ለማናጋት እንደ ቅመም የሚቆጠሩ ናቸው፡፡ 

. Simmering religion tension, escalating ethnocentric media campaign, building up of ethnic militia are recipes for disintegration, and it is real.

የርእዮትዓለም ልዩነት ወይም የጠራ ርዮትዓለም ከሌለው አዲሱ ፓርቲ በህዝብ ያለውን ቅቡልነት ሊቀንስበት ይቻለዋል Ideological ambivalence diminishes the popularity of the new party

 

በርካታ የፖለቲካ ተንታኞች በተለያዩ ጽሁፎቻቸው እንደሄሱበት ከሆነ በአዲሱ የብልጽግና ፓርቲ ውስጥ የርእዮት አለም ሽኩቻ ያለ ይመስላል በአንድ በኩል የአክራሪ ብሔርኝነት ትርክት አቀንቃኞች በግልጽም ሆነ በስውር አሉ ይባላል፡፡ እነርሱ የራስን እድል በራስ መወሰን እስከመገንጠል የሚለውን የህገመንግስቱን አንቀጽ 39 ገቢራዊ ከማድረግ ወደኋላ የሚሉ አይደሉም፡፡ በሌላ የሳንቲሙ ግልባጭ የሚገኙት የፖለቲካ ሰዎች ደግሞ ለዘብተኛ አቋም ያላቸው ሲሆን የእነርሱ ውስጠ ትግል የሚያጠነጥነው መሰረቱን ጂኦግራፊ፣ ማህበራዊና ባህላዊ፣ የአካባቢን ቋንቋ፣ ወዘተ ያደረገ የፌዴራል መንግስት እንዲቀጥል ነው፡፡

በነገራችን ላይ የብሔር ፖለቲካ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ምድር ማቆጥቆጥ የጀመሩት እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር 1960ዎቹ የኢትዮጵያ አክራሪ የማርክስሲት ሌኒንስት ተማሪዎችን እንቅስቃሴ ተከትሎ እንደሆነ አሁኑ ትውልድ መገንዘብ አለበት ብዬ አስባለሁ፡፡ የብሔር ፖለቲካን ከኢትዮጵያ ተጨባጭ (ነባራዊ) የፖለቲካ ሁኔታ  ሳያጣጥሙ (ሳያጠኑ) በኢትዮጵያ የጀመሩት የያው ትውልድ አባላት ነበሩ፡፡ ለኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ችግር ሰራሄ መፍትሔ ያመጣል በማለት የብሔርን ፖለቲካ የጀመሩት ብሄርተኞች የኢትዮጵያን ፖለቲካ ከእሳት ወደ ረመጥ ዶሉት እንጂ አንዳች መፍትሔ ማምጣት አልተቻላቸውም፡፡ የብሔር ፖለቲካ፡-

 • ኋለቀር
 • አፋጀሽኝ ትርክት የሚቀነቀንበት እና
 • ለእኔ ብቻ የሚሉ ግለሰቦች የተሰባሰቡበት እንደሆነ በርካታ የፖለቲካ ተንታኞች ይከራከራሉ፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ አክራሪ ብሔርተኞች በኢትዮጵያ የረዥም ዘመን ታሪክ ላይ ያላቸው አረዳድ፣ በኢትዮጵያ ሰንደቅአላማ ላይ ያላቸው ምልከታ እጅጉን አሳሳቢ ነው፡፡ ስለሆነም በተጠቀሰው ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያ መንግስትና የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሁሉ ቢያንስ ግማሽ መንገድ ላይ ተገናኝተው መነጋገር መስማማት አለባቸው ብዬ አስባለሁ፡፡ ለአብነት ያህል የኡጋንዳው ሙሴቪኒና ተቀናቃኞቻቸው በኡጋንዳ ታሪክና በሰንደቅ አላማ በተመለከተ የነበረ ንትርክ አልነበረም፡፡ መጪው ሀገር አቀፉ የኢትዮጵያ ምርጫ ነጻ፣ገለልተኛ፣ ተአማኒንና ዲሞክራቲክ እንዲሆን ሁሉም የፖለቲካ ሀይሎች በሰከነ መንፈስ መነጋገር ያለባቸው ይመስለኛል፡፡ ከምርጫው ባሻግር፣የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሀይሎች ከአፍንጫቸው እርቀው በማሰብ ለመጪው ትውልድ የፖለቲካ፣ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ህይወት መሻሻል መጨነቅ፣መጠበብ ያለባቸው ይመስለኛል፡፡

የገለለተኛ ተቋማት፣የሲቪል ማህበረሰብ ተሳትፎ እና ነጻ መገናኛ ብዙሃን እጥረት ተሳትፎን ይገድባል

ምንም እንኳን በብዙ መንግስታዊ ተቋማት የአመራሮች ለውጥ ቢኖርም(የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽነር ተራማጅ በሆኑ ግለሰብ መተካት እንደ አብነት ይቆጠራል)፣ የድርጅቶቹ መዋቅር ባለበት ነው ያለው፣ ፖሊሲዎችም ምሉሄበኩልሄ በሆነ ሁኔታ አልተለወጡም፣ Despite leadership change, the policies and organizational structures under which institutions operate remains unchanged.

ይህ በእንዲህ እንዳለ ለውጡን ያግዛል በሚል የተመሰረተው የእርቅና የድንበር ኮሚሽን Reconciliation and Boundary Commissions አሁን ድረስ የተሰጠውን ተልእኮ ያጠናቀቀ አልመሰለኝም፡፡

ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የሲቪል ማህበራት ስላላቸው ብሔራዊ ህልም በታወቁ መገናኛ ብዙሃን ወጥተው ሲናገሩ አይስተዋልም፣ ሌሎች መሰረታቸውን ጎሳ ላይ ያደረጉት የኢትዮጵያን ህዝብ ፍላጎት ሲያንጸባርቁ አይስተዋልም፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና ጠንካራ የሲቪል ማህበራት የሉም ማለት አይደለም፡፡ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች፣ ዲሞክራሲያዊ መብቶችና የህግ የበላይነት እንዲከበር በብዙ የደከሙ እንደ ኢሰመጉ፣የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያዎች ማህበር፣ ቪዥን ኢትዮጵያ፣ የኢትዮጵያ ሴቶች የህግ ባለሙያዎች ማህበር፣ የሰራተኞች ማህበርና የመምህራን ማህበር የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ምንም አንኳን አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ተአማኒነት ያለው የምርጫ ውድድር ሊያዘጋጅ ይችላልን ? በማለት ምክንያታዊ ጥያቄ ቢያነሱም፣ በቅርቡ መጪውን 6ኛውን የኢትዮጵያ ምርጫ ውድድር ለመታዘብ የተመዘገቡ የሲቪክ ድርጅቶች ተስፋ ሰንቀው የተነሱ ይመስለኛል፡፡ በተለይም የሲቪክ ድርጅቶች በተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አባላት ላይ ሊደርሱ የሚችሉ ጥቃቶችን ወይም የመብት ረገጣዎችን በንጹህ ህሊና እና በማስረጃ በተደገፈ ሪፖርት ሲያወጡ ወከባ ካልደረሰባቸው፣ መብታቸውን የተነፈጉ ማህበረሰቦች መብታቸውን ገቢራዊ እንዲያደርጉ ማስተማር ከቻሉ፣ ህዝቡ የመምረጥና የመመረጥ መብቱን እንዲያውቅ ከተጉ፣ ነጻ እና የሰለጠነ የምርጫ ውድድር እንዲኖር ከፍተኛ ጥረት ካደረጉ ወዘተ ወዘተ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ተአማኒነት ያለው የምርጫ ውድድር ሊያዘጋጅ ይችላል የሚል የግል አስተያየት አለኝ፡፡

በጣም ጥቂት የሆኑ መገናኛ ብዙሃንና የህትመት ውጤቶች ተአማኒነት ያለው መረጃ ያሰራጫሉ፣ህዝቡን ያስተምራሉ፣ ሚዛናዊ ዜና ያዘጋጃሉ፣ ሰለማዊ የምርጫ ውድድር እንዲኖር ያበረታታሉ፣ ድምጽ የሚሰጡ መራጮችን ያዘጋጃሉ( ህዝቡ ድምጹን ለሚፈልገው ፓርቲ እንዲሰጥ ያስተምራሉ)፣ ሆኖም ግን ይሁንና ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ መገናኛ ብዙሃን( የህትመት ውጤቶች) ወገናዊነት ያጠቃቸዋል፡፡ ገሚሶቹ ብሔርን መሰረት ያደረገ ወገንተኝነት ሲያሳዩ ሌሎች ደግሞ ለሚፈልጉት የፖለቲካ አቋም የቆሙ ናቸው ተብሎ ቢጻፍ ስህተት የሚል ይኖር ይሆን ካለም በአመክንዮ አስተያየት እንዲሞግት ስጋብዝ በአክብሮት ነው፡፡

ነጻና ገለልተኛ የዲሞክራቲክ ተቋማት በሌሉበት፣ ነጻ መንፈስ የሌላቸው ጋዜጠኞች ባሉበት፣ አንዳንድ የፖለቲካ ሰዎች የህዝቡን አጀንዳ በማስቀየስ ወደ አክራሪ የብሔር ፖለቲካ ይወስዱታል፡፡ ይሄም ብቻ አይደለም በሀገሪቱ ሰርአት አልበኝነት እንዲፈጠር የማይበጥሱት ቅጠል፣ የማይምሱት ስር የለም፡፡  ይህ በእንዲህ እንዳለ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ከተገደበ የዲሞክራሲን መንገድ እንዲጠብ ያደርገዋል፡፡

In the absence of independent institutions and civic engagement, politicians easily subvert public interests and exploit discontented youth for radical agenda that causes social unrest. Reversal of the initial gains on media openings and freedom of speech further diminishes the hopes for democratization

የግብጽ ተጽእኖ የሀገር ውስጥ አለመረጋጋትን ያባብሳል

በርካታ የፖለቲካ ተንታኞች በጥናት ወረቀቶቻቸው ላይ እንደተቀሱት ከሆነ ግብጽ  የታላቁን የአባይ ወንዝ ግድብ ግንባታን ለማስተጓጎል የምታካሂደው የዲፕሎማቲክ ተጋድሎ ለዶክተር አብይ መንግስት የውጪ ፖሊሲ ማእከል ነው ማለት ይቻላል፡፡ከዚህ ባሻግር ከታሪክ እንደምንማረው ግብጽ በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የነጻ አውጪ ድርጅቶችን ትረዳለች፣የኢትዮጵያን ጎረቤት ሀገራትን የአረብ ሊግ አባልሀገራት እንዲሆኑ ትወተውታለች(ሶማሊያ፣ዲጂቡቲ፣ ሱዳን ይጠቀሳሉ)፣ ኢትዮጵያ የአባይ ወንዝ ተፋሰሶችን ለማልማት የምታዘጋጀውን አቅድ የአለም የገንዘብ ድርጅት በገንዘብ እንዳይደግፍ በዲፕሎማቲክ ዘመቻ ጫና ታሳድራለች፡፡ ይህም ብቻ አይደለም ለምእራቡ አለም እና ለገልፍ ሀገራት ( በነዳጅ ሀብት ለበለጸጉት የመካከለኛው ሀገራት) ያላትን ስልታዊ ጠቀሜታ በመጠቀም ኢትዮጵያ የግብጽን ፍላጎት መሰረት አድርጋ እንድትስማማ የምታደርገው እረዥም እርቀት የዲፕሎማቲክ ዘመቻ ቀላል አይደለም፡፡ የቀድሞው የተባበረችው አሜሪካ ፕሬዜዴንት ዶናልድ ትራምፕ በኢትዮጵያ ላይ የሀይል እርምጃ እንዲወሰድ ድጋፋቸውን ሰጠተው የነበረው እንደው ዝም ብለው አለነበረም፡፡ የግብጽ ዲፕሎማቲካ ዘመቻ ከአሜሪካ ብሔራዊ ጥቅም ጋር ተቆራኝቶ ስለነበር እንደሆነ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ልብ ማለት ይገባናል፡፡ በነገራችን ላይ ይህ የትራምፕ አቋም የአፍሪካን ልማትና ዴሞክራሲን ችላ ያለ ነበር፡፡ ግብጽ በዲፕሎማቲክ ዘመቻ ብቻ ተገድባ ይትቆይ ሀገር አይደለችም፡፡ ታሪካዊ ጠላታችን ግብጽ በኢትዮጵያ ጎረቤት ሀገራት ( በተመቻት ሀገር) ወታደራዊ የጦር ሰፈር ከማቋቋም ወደኋላ የምትል ሀገር አይደለችም፡፡ (Egypt is actively seeking client states among Ethiopia’s neighbors to place its military base )

ከዚህ ባሻግር ግብጽ በኢትዮጵያ ላይ የሚከተሉትን ተጽእኖ ለማሳደር ትሞክራለች፡-

 • ግብጽ የባህር በር በሌላት ኢትዮጵያ ላይ ችግር ወይም መሰናክል የሚፈጠርበትን መንገድ ከመፈለግ ወደ ኋላ አትልም ( ለአብነት ያህል ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ወደለየለት ጦርነት ውስጥ ተዘፍቃ በፖርት ሱዳን እንዳትጠቀም ልታደርግ ትችላለች፣ ኢትዮጵያ ከጎረቤት ዲጂቡቲ ጋር ተቃቅራ መውጫና መግቢያ እንድታጣ፣ አንገቷ እንዲታነቅ ከማድረግ ወደኋላ የማትል መሰሪ ሀገር ናት፡፡ ግብጽ
 • አክራሪ ብሔርተኞችን በብዙ መልኩ ትረዳለች
 • ኢትዮጵያና ሱዳን በጋራ ድንበራቸው ዙሪያ የገጠሙትን ግጭት ለማባባስ ትሰራለች
 • በሀገራችን እዚህና እዚያ ቦግ እልም የሚሉ ግጭቶችን እንደ ጥሩ የፖለቲካ ካርድ መጫወቻ ትጠቀምባዋለች፡፡

ሆኖም ግን ይሁንና የዶክተር አቢይ መንግስት የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት በጀመረው ህብረብሔራዊ ጦር ባማከለ መልኩ ከቀጠለበት፣ በመንግስታቸው ውስጥ የተሰገሰጉ አንዳንድ አክራሪ ብሔርተኞች ለዘብተኛ አቋም ባላቸው ፖለቲከኞች ከተተኩ፣የኢትዮጵያ አንደነት የበለጠ ከተጠናከረ፣ ከተፎካካሪ ፖለቲከኞች ጋር አብረው መስራት ዳገት ከሆነባቸው፣ በኢትዮጵያ መሰረታዊ የፖለቲካ ችግሮችን ለመፍታትና ለሀገሪቱ አንድነት አብረው ከሰሩ ግብጽ የምትፈጥረውን ጫና ለመቀነስ ይችላሉ ብዬ አስባለሁ፡፡

እስቲ አሁን ደግሞ መድበለ ፓርቲ ለመመስረት የሚያስችሉ አንዳንድ ነጥቦችን ልጥቀስ

 1. አስተዳደሩ ህጋዊ መሆን ይገባዋል

ሁላችንም አንደምናስተውሰው ባለፈው አመት መካሄድ የነበረበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ውድድር ወደ ዘንድሮው አመት ሲታላለፍ በርካታ ህጋዊ ክርክሮችን አስነስቶ አንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ የባለፈው ፓርላማ የ5 አመት ቆይታ የሚያበቃው የነበረው እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር ጥቅምት 2020 ስለነበር በአስተዳደሩ ህጋዊነት ላይ ከባድ ጥያቄዎችንም አስነስቶ ነበር፡፡ አንዳንድ የፖለቲካ ተቀናቃኞች ወይም ተፎካካሪዎች መንግስት የኮሮና ቫይረስ በሽታን እንደ ምክንያት በመቁጠር ምርጫው ተራዘመ የሚል ስሞታቸውን አሰምተው ነበር፡፡ ሆኖም ግን ይህ ውተወታቸው ከመንግስት አኳያ ተቀባይነት አላገኘም ነበር፡፡ እንዲህ አይነት ወቃሳ ሲያቀርቡ ከነበሩት መሃከል አብዛኞቹ ዛሬ የሉም፡፡ ገሚሶቹ በጦር ሜዳ ተሸንፈው ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ተዋናይነት ተወግደዋል፡፡ የቀሩት ደግሞ በውህኒ ቤት ይገኛሉ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ  አንዳንድ የፖለቲካ ተፎካካሪ አመራሮች እንደሚሰጡት አስተያየት ከሆነ በሀገሪቱ ያለው አለመረጋጋት፣ ከግዜ ወደ ግዜ እየተባባሰ የመጣው የኑሮ ውድነት፣ አክራሪ ብሔርተኞች የሚፈጽሙት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ወዘተ ወዘተ ተደምረው የዶክተር አብይን መንግስት ቅቡልነት እየሸረሸረው ይገኛል፡፡ በሌላ አነጋገር አንድ ህጋዊ መንግስት ማከናወን የሚገባውን ተግባራት አላከናወነም በማለት ይተቻሉ፡፡ 

ኢትዮጵያ 80 ፐርሰንት የሚሆን ከእጅወደአፍ የሆነ ኑሮ የሚኖር ( ኑሮ ከተባለ ማለቴ ነው) ገበሬ የሚኖርባት ባህላዊ ሀገር ናት፡፡ የኢትዮጵያ ገበሬ መሬት በመንግስት ይዞታ ስር ያለ ነው፡፡( በኢትዮጵያ የመሬት ባለቤት መንግስት ነው)፣ የመሬት ህግ የሚወጣው በመንግስት ነው( በኢትዮጵያ የመሬት ፖሊሲ ላይ የገበሬው ተጽእኖ አነስተኛ ነው)፣ መንግስት ዋነኛ የመሬት አከፋፋይ ሲሆን፣የመሬት ድልድል ዋነኛ እቅድ አውጭ ገዥው ፓርቲ ነው፡፡ በመሬት ድልድል አኳያ ወይም ህግ ከማውጣት አኳያ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች አማራጭ ፖሊሲ አሁን ድረስ ገቢራዊ መሆን አልቻለም፡፡ ከመጪው ምርጫ ፍጻሜ በኋላ አማራጭ የመሬት ፖሊሲዎች ገቢራዊ ሊሆኑ ከቻሉ አብረን የምናየው ይሆናል፡፡ ለዚህ እውን መሆን የኢትዮጵያ መንግስት ተአማኒነት ያለው፣ ሁሉን አቀፍ የሆነ ምርጫ ለማካሄድ ቃል ገብቷል፡፡ በነገራችን ላይ የኢትዮጵያ መንግስት ቃል በገባው መሰረት መጪው የምርጫ ውድድር ተአማኒ፣ፍትሃዊ፣ነጻና፣ገለልተኛ፣አሳታፊና ሁሉን አቀፍ እንዲሆን ቅድመ ሁኔታዎችን ካሟላ ህጋዊ እና የሰለጠነ መንግስት ለመመስረት እዳው ገብስ ነው፡፡ ከሁሉም በፊት ግን የኢትዮጵያ መንግስት በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍል ሰላምና የግዛት አንድነት የማስከበር መንግስታዊ ሃላፊነቱን በፍጥነት መወጣት ያለበት ይመስለኛል፡፡

2.የህዝብ የጸጥታ ፍላጎትና የምጣኔ ሀብት መሻሻል

አፍሮ ባሮሜትር (Afro barometer) የተሰኘ አለም አቀፍ ተቋም በጥናቱ እንደደረሰበት ከሆነ 90 ፐርሰንቱ ኢትዮጵያዊ ወደ ዲሞክራሲ ጎዳና  ላይ እየተጓዝን ነው ብሎ የሚያምን ሲሆን፣ 54 ፐርሰንት የሚሞላው ደግሞ ሀገሪቱ ወደ ዲሞክራሲያዊ ጎዳና እየሄደች አይደለም ብሎ ያምናል፡፡ ምንም አንኳን የመካከለኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ቁጥር እየቀነሰ የመጣ ቢሆንም የከተሞች መስፋፋት፣ የመገናኛ አውታሮች መስፋፋት፣ በማህበራዊ ድረገጾች ላይ የአዎንታዊ መልእክቶች ከተስፋፉ( የማህበራዊ ድረገጽን ለህዝብ አስተማሪ በሆነ መልኩ መጠቀም ከተቻለ) ፤ የማህበራዊ ፍትህ አቀንቃኞች ቁጥር መጨመር፣ እኩል የምጣኔ ሀብት ተጠቃሚነት መኖር፣የጾታ እኩልነት ወዘተ ወዘተ ወደ ዲሞክራሲ ለሚደረገው ጉዞ ተስማሚ ሁኔታዎች ናቸው ብዬ አስባለሁ፡፡ 

ምንም እንኳን የሀገሪቱ የጸጥታ ሁኔታ ከእሳት ወደ ረመጥ እየሄደ ቢሆንም፣ የኑሮ ውድነት ጣራ ቢነካም (increasing price of living)፣ የኢትዮጵያ መንግስት የሀገሪቱን ጸጥታ ለማስከበር፣ ገበያውን ለማረጋጋት እና ስራ እጥ ወጣቶችን ስራ እንዲያገኙ ለማድረግ ህጋዊ ስልጣን ያለው ይመስለኛል፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵያ መንግስት አብዛኛውን ኢትዮጵያዊ እየተፈታተነ ያለውን የኑሮ ውድነት መክላት ባይሆንለት መጠነኛ ማስተካከያ ካበጀለት፣ የሀገሪቱን ጸጥታ ማስከበር ከቻለ ምርጫው ለሀገሪቱ ተስፋ ይዞላት ይመጣል የሚለው የግል አስተያየቴ ነው፡፡

3.ስልጣንን ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ማካፈል የፖለቲካ ፕሉራሊዝምን ያስተዋውቃል (Power sharing with opposition introduces political pluralism )

እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር ከ2015 ጀምሮ አሁን ድረስ በኢትዮጵያው ፓርላማ አንድም የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ ህጋዊ ወንበር እንደሌለው የታወቀ ጉዳይ ነው፡፡ የፖለቲካ ተሳትፎም አልነበረም፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ  እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር 2018 ወደ ስልጣን የመጡት ዶክትር አብይ በውጭ ሀገር የነበሩ የተቃዋሚ ሀይሎች ወደ ሀገር ቤት መጥተው ቢሮ እንዲከፍቱ ማድረጋቸውና ሌሎችም የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲንቀሳቀሱ ሁኔታዎችን ማመቻቸታቸውን በተመለከተ የሚያከራክር አይመስለኝም፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች በየጊዜው በሚያወጡት መግለጫ ላይ እንደተጠቀሱት ከሆነ ከደጋፊዎቻቸው ጋር ለመገናኘት እንደሚቸገሩ፣ ከቦታ ወደ ቦታ ተንቀሳቅሰው አለማቸውን ለህዝብ ለማስተዋወቅ እንዳልቻሉ፣ የብልጽግና ፓርቲ በዝግታም ቢሆን ወደ ነበረው የጭቆና ስልት እንዳይጓዝ ምንም ማስተማመኛ እንደሌላቸው ለማወቅ ይቻላል፡፡ በጣም ጥቂት ፓርቲዎች ደግሞ በመጪው የምርጫ ውድድር ላይ ላይካፈሉ እንደሚችሉ ከወዲሁ ሲናገሩ ይሰማል፡፡በገጠር ከተሞች ያሉ ቢሮዎቻቸውም እንደተዘጉ ለሚመለከታቸው ተቋማት አመልክተዋል፡፡( ለመገናኛ ብዙሃን ከሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ ተሰምቷል፡፡)

በነገራችን ላይ የኢትዮጵያ መንግስት ነጻና ገለልተኛ፣ተአማኒና ነጻ የምርጫ ውድድር የበኩሉን ሚና ከተጫወተ ፣ በተለይም በከተሞች አካባቢ በሚደረጉ የምርጫ ውድድሮች ላይ ከፍተኛ ፉክክር ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በውጤቱም መድበለ ፓርቲ ስርዓት እውን ሊሆን ይቻለዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ መንግስት ሁሉም በሰላማዊ ትግል የሚያምኑ የፖለቲካ ሃይሎች የሚያሰሙትን ሮሮ ተቀብሎ መልስ ለመስጠት መንፈሳዊ ወኔ ከታጠቀ፣ ሁሉም ሰላማዊ የፖለቲካ ሀይሎች በምርጫው እንዲሳተፉ ከተደረገ፣ ፖለቲካዊ ችግሮች ፖለቲካዊ መፍትሔ ከተሰጣቸው፣ መጪው ግዜ ብሩህ ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

የተረሱ አናሳ ማህበረሰቦች፣ የፖለቲካ ውክልና ይፈልጋሉ

ተጽእኖ ፈጣሪ የብሔር ቡድኖች (Dominant ethnic groups ) አናሳ ቁጥር ያላቸው ማህበረሰቦች ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና የሲቪክ መብቶቻቸው ተወካዮች እንዳይኖራቸው ተጽእኖ ማድረጋቸው ወይም መከልከላቸው የታወቀ ጉዳይ ነው፡፡  በተለያዩ ክልሎች የሚኖሩ በቁጥር አነስተኛ የሆኑ ማህበረሰቦች መብት ገፈፋ እየቀጠለ ከሄደ የማህበረሰቡን የርሰበርስ ግንኙነት ይጎዳል፡፡

ይህም ብቻ አይደለም ዛሬም ቢሆን የአናሳ ቁጥር ያለቸውን ማህበረሰብ መብት ገፈፋ ሰምቶ እንዳልተሰማ፣ አይቶ እንዳለታየ ከሆነ ዜጎችን ተስፋ ቢስ ከማድረጉ ባሻግር፣ የሀገሪቱን አንድነት ሊሸረሽር ያስችላል፡፡

ስለሆነም መንግስት የገባውን ቃል ገቢራዊ በማድረግ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች በእኩልነት ማሳተፍ ከሆነለት፣ መጪው ምርጫ በሁሉም ህብረተሰብ ዘንድ ሊታመን ይቻለዋል፡፡ ከዚህ ባሻግር መብታቸውን ለተገፈፉ አናሳ ቁጥር ላላቸው ማህበረሰቦች ፍትህን ሊያጎናጽፍ ያስችለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የፖለቲካ ነጻነት ገቢራዊ ከሆነ ለአፍሪካው ቀንድ ሠላም መከበር ይበጃል

ሁላችንም እንደምናስታውሰው ዶክተር አቢይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር በሆኑበት የመጀመሪያው አመት የኢትዮጵያን የረጅም ዘመን አመታት ታሪክና ጥንታዊነት በአደባባይ በመናገራቸው ምክንያት በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ብሩህ ተስፋን ጭሮ ነበር፡፡ በሌላው የሳንቲሙ ግልባጫ ደግሞ ጎሳ ተኮር ግጭቶች፣ አስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መበራከታቸው ብዙዎችን ግራአጋብቷል፣ከባድ ጭንቀት ውስጥም ዶሏል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር 2018 ኢትዮጵያና ኤርትራ የሰላም ስምምነት ተፈራርመዋል መባሉ፣ በሁለቱ ሀገራት መሃከል ሊከሰት የሚችለውን ደምአፋሳሽ ጦርነት ሊገታው ችሏል፡፡ ይህም ብቻ አይደለም ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ሶማሊያ አብረው ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸው በአፍሪካው ቀንድ የትብብር መንፈስ እንዲሰርጽ የሚያግዝ ይመስለኛል፣ድንበር አቋራጭ የንግድ ግንኙነትን እንዲሻሻል ይረዳል፣ የአካባቢ እንክብካቤ ግንዛቤን ይፈጥራል፣የአካባቢውን ጸጥታ ለማስጠበቅና ህገወጥ የንግድ ዝውርርን ለመቀነስ ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡

ስለሆነም ኢትዮጵያ ዴሞክራቲክ ሀገር መሆኗ የቅንጦት አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲ የጎመራባት ሀገር እንድትሆን መንግስት መንፈሳዊ ወኔ መታጠቅ አለበት፡፡ በኢትዮጵያ ነጻነትና ዴሞክራሲ እውን መሆን ከቻሉ ለአፍሪካው ቀንድ ሰላም መሆን ይረዳል፣ በቀይባህር ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ የንግድ መርከቦች የስራ እንቅስቃሴ የተመቻቸ ይሆናል፡፡ Thus, democratization in Ethiopia would favorably affect the region and the Red Sea shipping lanes.

ለተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስልጣን ማካፈል የፖለቲካ ፕሉራሊዝምን ያመጣል

እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር 2011 ጀምሮ አሁን ድረስ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በኢትዮጵያ ፓርላማ ውስጥ ህጋዊ ወንበር ማግኘት አልቻሉም፡፡ እውነተኛ የፖለቲካ ተሳትፎም አልነበረም ማለት ይቻላል፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር 2018 ላይ ዶክተር አብይ ወደ ስልጣን ማማ ላይ ከወጡ በኋላ የፖለቲካ ምህዳሩ እየሰፋ ስለመምጣቱ የሚያከራክር አይመስለኝም፡፡ ከቅርብ ግዜ ወዲህ ደግሞ ከአንዳንድ የፖለቲካ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራርና አባላት የብልጽግና ፓርቲ ቀስበቀስ በአባላቶቻቸው ላይ ወከባና እስር እንደሚፈጸምባቸው ለመገናኛ ብዙሃን ከሚሰጡት ቃለምልልስ ተሰምቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በመጪው ምርጫ ላይሳተፉ እንደሚችሉ፣በአንዳንድ የገጠር ወረዳዎች ከቦታ ወደ ቦታ የመንቀሳቀስ መብታቸው እንደተገፈፈ፣አባላቶቻቸውንና ደጋፊዎቻቸውን መሰብሰብ እንዳልቻሉ፣ በየጊዜው ሲናገሩ ይሰማል፡፡

ስለሆነም የኢትዮጵያ መንግስት የምርጫውን ሜዳ ማስፋት፣ነጻና እኩል እድል የሚሰጥ ( ለሁሉም የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች) እንዲሆን የበኩሉን ድርሻ መወጣት አለበት ብዬ አስባለሁ፡፡

መጪው የምርጫ ውድድር ነጻ፣ተአማኒ እና ገለልተኛ እንዲሁም አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መሆን ከቻለ፣ በተለይም በትላልቅ ከተሞች ከባድ ፉክክር ይኖራል ብዬ አስባለሁ፡፡ ውጤቱም የስልጣን መከፋፈልን ያስገኛል የሚል የግል አስተያየቴ ነው፡፡ ( ስልጣን በአንድ ቡድን ብቻ ሊከማች የሚችልበት እድል ይጠባል)፡፡ ለሁሉም የፖለቲካ ሃይሎች እኩል እድል የሚሰጥ የምርጫ ውድድር ለሀገሪቱ መጻኢ እድል ብሩህ መሆን የሚረዳ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በአንክሮ መከታተል ያለብን ይመስለኛል፡፡ የምርጫ ጉዳይ የመንግስትና የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ ጉዳይ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡

አለም አቀፉ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ ዲሞክራሲ እውን እንዲሆን መርዳት አለበት

በነገራችን ላይ በአንዲት ሀገር ላይ ዴሞክራሲና ነጻነት እውን እንዲሆን ዋነኛው ተዋናይ የዛች ሀገር ህዝብ ነው፡፡ የነጻነት ዋጋው ከባድ ነው፡፡ በዚች ምድር ላይ ነጻ ምሳ የለም፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና የምንኖረው በአለም ላይ ነውና ከአለም ተጽእኖ ማምለጥ አንችልም፡፡ ስለሆነም ለዲሞራሲና ነጻነት እውን መሆን የሚደማ ልብ ያላቸው የአለም ህብረተሰብ አካላት በኢትዮጵያ መጪው የምርጫ ውድድር ነጻ፣ገለልተኛና አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ በታሪክ ፊት ቆመዋል፡፡ እነርሱ ቢያንስ፣ቢያንስ መጪው 6ኛው የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የምርጫ ውድድር ተአማኒ፣ሁሉንም የፖለቲካ ሀይሎች አካታች ስለመሆኑ፣ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ልዩነት መቻቻል ስለመኖሩ፣ በቁጥር አነስጠና የሆኑ ማህበረሰቦች መብት ስለመከበሩ ወዘተ ወዘተ የህሊና ምስክርነት መስጠት አለባቸው፡፡

የአናሳ ማህበረሰቦች መብት መከበር፣ ነጻ ህዝባዊ ውይይት፣ የተፎካካሪ ፖለቲካ ሃይሎች ተሳትፎ ለብሔራዊ አንድነት ጠቃሚ ነው፡፡ ይህን ማድረግ ከተሳነን የምርጫው መጨረሻ አያምርም፡፡ ስለሆነም የምርጫውን ሂደትና ፍጻሜ በተመለከተ አለም አቀፉ ህብረተሰብ በትኩረት እናገለልተኝነት አቋም መከታተል ያለበት ይመስለኛል፡፡

በእኔ አስተሳሰብ አለም አቀፍ ወዳጆች በእውነትና ህሊና መሰረት ላይ ቆመው ለዲሞክራሲ መስፈን የራሳቸውን ድርሻ ለመወጣት መንፈሳዊ እና ህሊናዊ ወኔ ለመታጠቅ ከቻሉ ብሔራዊ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ያስችላቸዋል ፡፡( የሌላውን ሀገር ብሔራዊ ጥቅም ሳይጋፉ በመከባበር ላይ የተመሰረተ ስምምነት በማድረግ ማለቴ ነው፡፡ ) ይህም ብቻ አይደለም እነርሱ በአንዲት ሀገር ዴሞክራሲ እውን እንዲሆን ከልብ ፍላጎታቸውን ካሳዩ አምባገነኖች ቦታ አይኖራቸውም፡፡

በነገራችን ላይ በ1997 ዓ.ም. ግንቦት ወር ምርጫ ውድድር እንደ አጀማመሩ ሁሉ መጨረሻው ያላማረው ኢትዮጵያ የኮሚንስት አለሙን ክፍል ድጋፍ ስለነበራት አልነበረም፡፡ ኢትዮጵያ በአለም አቀፉ የጸረሽብር ትግል የተባበረችው አሜሪካ ዋነኛ ሸሪክ ስለነበረች በዲሞክራቲክ ሂደት የተጀመረውን የምርጫ ውድድር የአቶ መለስ ዜናዊ አገዛዝ በሃይል የህዝብን ድምጽ ሲነጥቅ ከምእራቡ አለም ጠንካራ ተቃውሞ አልገጠመውም ነበር፡፡ የተባበረችው አሜሪካ በኢትዮጵያ ምድር ለተፈጸመው አስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሰጠችው ምላሽ ቢኖር አይንን መጨፈን ነበር፡፡ ሰምታ እንዳልሰማች፣ አይታ እንዳላየች ነበር የሆነችው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር የወያኔ አገዛዝ 100 ፐርሰንት የፓርላማ ወንበር ሲቆጣጠር የተባበረችው አሜሪካ ይሁንታ ሰጥታ ነበር፡፡ አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ ፖለቲካ ሰው ምርጫው ዲሞክራሲው ነበር በማለት ተሳልቀውብናል፡፡ በነገራችን ላይ ይህ የአሜሪካ መንፈስ አይመስለኝም፡፡ ብዙዎችም በምእራባውያን ዴሞክራሲያዊ እሳቤ ጥርጣሬ እንዲያድረባቸው የሚያደርግ ነው፡፡

በአጠቃላይ አለምአቀፉ ህብረተሰብ ከአገዛዞች ወይም ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ሳይሆን ከዲሞክራሲ ጋር እንዲቆሙ እንማጸናል፡፡ ከዚህ በተቃራኒ መንገድ ከተጓዙ ለአንድ ጨቋኝ አገዛዝ ቀጣይነት መንገዱን ሊያመቻቹለት ይችላሉ ብዬ በብርቱ እሰጋለሁ፡፡

In the 1990s, the third wave of democratization did not penetrate Ethiopia not least because it was not part of the communist bloc, but strategic imperative on counterterrorism made the US turn a blind eye on Ethiopia’s heavy hand on human rights.  In 2015, US administration approval of Ethiopia’s 100% claimed victory as free and fair election did not lead to democratization but raised doubts about the West’s commitment to democracy

ማጠቃለያ

በአንዲት ሀገር ላይ ምርጫ ማካሄዱ ምንም ክርክር የሚያስነሳ አይመስለኝም፡፡ የምርጫ ውድድር እውን መሆን ያለውን መንግስት እና የተፎካካሪ የፖለቲካ ሃይሎች ያሉበትን አቅምና ሁኔታ  ለመገምገም የሚያስችል ነው፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀው ስድስተኛው የኢትዮጵያ የምርጫ ውድድር አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ፣ ፍትሃዊ፣ተአማኒ፣ ገለልተኛ እና ሁሉንም ሰላማዊ የፖለቲካ ሀይሎችን ያካተተ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ በአንድ የገበያ አዳራሽ  እቃዎችን ለመሸመት የሚሄድ ግለሰብ ከብዙ አማራጮች በኋላ የሚፈልገውን ሸቀጥ ወይም እቃ መርጦ እንደሚገዛ ሁሉ፣ በተስተካከለ የምርጫ ሜዳ ላይ ሰላማዊ ውድድር የሚያደርጉ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች እና የመንግስት እጩዎች መወዳዳር ያለባቸው ይመስለኛል፡፡

Filed in: Amharic