>

በዋሽንግተን ዲሲ፣ በጄኔቫ ... ታላቅ የተቃውሞ ሠልፍ

በዋሽንግተን ዲሲ፣ በጄኔቫ … ታላቅ የተቃውሞ ሠልፍ እየተደረገ ነው ‼

በዋሽንግተንና በጄኔቭ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አስተባባሪነት የተዳፈነውን የአማራ ህዝብ የዘር ማጥፋት ወንጀል ለአለምአቀፉ ማህበረሰብ ማሳወቅን አላማው ያደረገ ፥ ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ሲደረግ ውሏል።
በሰልፉ ላይ እጅግ ብዙ ቁጥር ያላቸው ሰው የመሆንን ክቡርነት የተገነዘቡ ኢትዮጵያዊያና ትውልደ ኢትዮጵያውያን  ሁሉ   በቦታው በመገኘት ይኸን ማቆሚያ ያጣውን የዘር ፍጅት- እልቂት በመቃወም ድምፃቸውን ለዓለም ህዝብ በማሰማት ላይ ይገኛሉ ።
 በተለይም በአማራ ህዝብ ላይ እየተደረገ ያለውን  ጅምላ ፍጅት፣ የዘር ማጽዳት ዘመቻ በምስል የተደገፈ መረጃ በመያዝ ለአለም ህዝብ የማሳወቅ ፣ የአማራን ግድያ መፈናቀል ለማስቆም ፣ እኒህን ጄኖሳይደሮች በአለም አቀፍ ፍርድቤት ለፍርድ እስከማስቀረብ የደረሰ ጥያቄን ያነገበ ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል። ይህ ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ በቀጣይ ቀናት በሌሎችም የአለም ክፍሎች አማሮችና ሰብአዊነት የሚሰማቸው አገር ወዳድ ዜጎች ባሉበት ሁል ይካሄዳል።
Filed in: Amharic