>

የኦነግ የግዛት ጥያቄና የኢትዮጵያ አንድነት...!!! (ታሪክ ተመራማሪው - አያሌው ፈንቴ)

የኦነግ የግዛት ጥያቄና የኢትዮጵያ አንድነት…!!!

ታሪክ ተመራማሪው አያሌው ፈንቴ

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) በመባል የሚታወቀው ጠባብ ጎሰኛ ድርጅት ኦሮሞዎች የሚኖሩበት አካባቢ ከኢትዮጵያ ተገንጥሎ ራሱን የቻለ አገር እንዲመሠረትና ኦሮሞ ያልሆኑ ነዋሪዎች ከአካባቢው እንዲወጡ በማለት በተለያየ መንገድ በተለይም በአማራ ሕዝብ ላይ ግድያ፣ ማፈናቀልና ዝርፊያ ፈፅሟል።
ኦነግ ለኦሮሚያ መንግሥት እውን መሆን እንዲረዳ የሀሰት ታሪኮችንም እየፃፈ ቆይቷል። የኢትዮጵያ ታሪክ የ100 ዓመት ነው የሚለውን የተለመደ ስብከት ትተን ሌሎቹን ሁለት ዋና ዋና የኦነግ ታሪኮች እንመልከት፦ (1ኛው) አማሮች የኦሮሞዎችን አገር በጉልበት መጥተው ያዙ የሚልና፣ (2ኛው) አማሮች የኦሮሞዎች መተዳደሪያ የነበረውን የገዳ ሥርዓት አጠፉ በማለት የሚኮንንበትን ታሪክ እናገኛለን፡፡ የእነዚህን ነጥቦች ይዘት በየተራ እንመርምር፡፡
(1ኛ) አማሮች የኦሮሞዎችን አገር በጉልበት መጥተው ያዙ ስለሚለው የኦነግ ትርክት
አማሮችና ሌሎች የኢትዮጵያ ዜጎች የትኛውም ክፍለ ሀገር አገራቸው እንደሆነ ያምናሉ። በዚህም ዕምነት መሠረት በየቦታው ሄደው ይኖራሉ። ሆኖም ኦነግ የግዛት ባለቤትነት ጥያቄ ስላነሳ ታሪካዊ መሠረቱን ማሳዬት አለብን።
ኦነግ ኦሮሚያ ብሎ የሚጠራው አካባቢ ዓለም ስትፈጠር ጀምሮ ኦሮሞዎች የነበሩበት አስመስሎ ይነግረናል። የኦነግ የሶሺዎ-ኢኮኖሚክና የፖለቲካ አመለካከት የሕዝብን ከቦታ ወደ ቦታ ዝውውር ከግምት ውስጥ አያስገባም። በኦነግ አመለካከት ሁሉም ነገር የህዝብ ዝውውርን ጨምሮ የማይነቃነቅ ቀጥ ብሎ የቆመ ነው። እውነቱ ግን ሰዎች እንኳን በአንድ አገር ውስጥ በአንድ አህጉር ይዘዋወራሉ፣ ይሰፍራሉ፣ ይኖራሉ። ትውልድም ትተው ያልፋሉ።
ለምሳሌ የአሜሪካ፣ የካናዳ፣ አብዛኛው የአወስትራሊያና የኒውዚላንድ፣ ወዘተ. ሕዝብ የትውልድ ሀረጉ የሚመዘዘው ከሌላ አህጉር ነው። በየግል ካየነው በውጭ ሀገራት የምንኖር ኢትዮጵያውያን ከኢትዮጵያ የመጣን ቢሆንም የምንኖርባቸው የአውሮፓም ሆነ የአሜሪካ ወዘተ. አህጉራት የእኛም መኖሪያ ሆነዋል። ለሌንጮ ለታም፣ ለሌንጮ ባቲም፣ ለአሰፋ ጀለታም፣ ለቡልቻ ደመቅሳም፣ ለዲማ ነገዎም፣ ለአባ ጫላ ለታም፣ ለዳውድ ኢብሳም፣ የዛሬው የኦነግ ኦቦ ቦሩ በረካም በያሉበት እንዲሁ።
ምንጊዜም እነ ሌንጮ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የሚያስጠይቃቸውን ወንጀል ፈፅመዋል። ምንም ዓይነት ሌላ መኖሪያ የሌላቸውን ድሃ የአማራ ገበሬዎች በዘር አማራ በመሆናቸው ብቻ በሐረር፣ በአሩሲ፣ በባሌ፣ በኤሉባቦር፣ በወለጋ፣ በከፋ፣ ወዘተ. ጭካኔ በተሞላበት ተግባር ከነነፍሳቸው በገደል ተወርውረዋል፣ ከነነፍሳቸው ተቃጥለዋል፣ ተገድለዋል። «በኋላ የመጣ አይን አወጣ» እንዲሉ ሆኖ ከመኖሪያ አገራቸው ተፈናቅለዋል፣ የቀሩትም «አገራችሁ አይደለም መጤዎች ናችሁ» («ኦሮሚያ ቢያን ኬኛ፣ ኬሱማ ገለቀባ») ተብለው ተባርረዋል።
ስለ ባላገርነት መብት ስንነጋገር ግልፅ መሆን ያለበት ጥያቄ አለ። ሰዎች ለሚኖሩበት አገር ባለቤት የሚያደርጋቸው ምንድነው? ከሌሎች ቀድሞ መገኘት ከሆነ ኦሮሞዎች ከቤናድር ከመነሳታቸውና ወላቡ (ኢትዮጵያ ውስጥ) ከመግባታቸው በፊት ዛሬ በወረራ የሠፈሩባቸው ቦታዎች (ሐረር፣ ባሌ፣ አሩሲ፣ ሲዳሞ፣ ወለጋ፣ ወሎ፣ ወዘተ) በአማሮችና በሌሎች ነባር ሕዝብ የተያዘ ምድር ነበር። ስለዚህ ኦሮሞዎች ዘግይተው በ16ኛው ክፍለ ዘመን የደረሱ ስለሆነ እንደ ነባር ሕዝብ የባለ አገርነት መብት ላይኖራቸው ነው። ይህ ደግሞ የኦሮሞን ኢትዮጵያዊነት ሊያስክደን ነው።
በሌላ በኩል ተቀባይነት ባገኘው በዓለም አቀፍ የዜግነት ህግ መሠረት የሚኖሩበት ወይም የተወለዱበት አገር አገራቸው ነው ብለን ካመንን ኦሮሞዎች ኑዋሪዎቹን አባርረው ከሠፈሩበት በኋላ የተባረሩት ዜጎች አገር ሠላም ሲሆን መጥተው የሰፈሩበት ኑዋሪዎች የአገሩ ባለቤትነት መብት አላቸው። ስለዚህ ቀድመውም የኖሩበት ሆነ በኋላ የመጡት የባለአገርነት መብታቸው እኩል ነው። በዚህ መልክ ስናይ ኦነግ ያነሳው የውጡልኝ ጥያቄ ከጠባብ ጎሰኝነትና ከታሪክ ዕውቀት ድህነት የተነሳ መሆኑ ግልፅ ነው።
(2ኛ) ኦነግ አማሮች የኦሮሞዎች መተዳደሪያ የነበረውን የገዳ ሥርዓት አጠፉ በሚል ስለሚያቀርበው ኩነኔ 
የገዳን ሥርዓት በሚመለከት አማሮችም ሆኑ ሌሎች ነገዶች እንዲጠፋም ሆነ እንዲኖር ጥረት አላደረጉም። ሥርዓቱ የጠፋው መጥፋት ስለነበረበት ብቻ ነው። በዘመናዊት ኢትዮጵያ የገዳ ፋይዳ የመከነው በሌላ በምንም ምክንያት ሳይሆን እንደ ማንኛውም አሮጌ ባህልና ሥርዓት ጊዜውን ስለጨረሰ ነው።
ገዳ ኦሮሞዎች በወቅቱ ጦራቸውን እንዲያደራጁ፣ አምልኮ እንዲፈፅሙና የተጣላ እንዲያሥታርቁበት የጠቀማቸው ሥርዓት ቢሆንም፣ ለምንገኝበት ዘመን የተሻሻለ ሕግና የአስተዳደር ሥርዓት ሲመጣ የገዳ ሥርዓት ቦታ እንደማይኖረው ግልፅ ነው።
ፍርድ ቤቶች እያሉ የከባድ ወንጀል ጉዳዮች በገዳ ሽማግሌዎች ሊታዩ አይችሉም። ሰዎች የተቀበሏቸው የክርስትናና የእሥልምና ሐይማኖቶች እያሉ በመናፍስት አያመልኩም። ከፈለጉም ማምለክ ይችላሉ። ይህ የሰዎች ምርጫ ነው። የገዳው የአስተዳደር ሥርዓት ዘመናዊ የፓርላሜንታሪ ዲሞክራሲ ሥርዓትን ሊተካ አይችልም። ለአገሩም ሕዝብ ፍትህና ዲሞክራሲን የሚያጎናፅፍ አይደለም።
ኦነግ የኢትዮጵያን መከፋፈል አጥብቆ ይደግፋል። ኦነግ ለኤርትራም መገንጠል ከወያኔ ትግሬዎች ጋር በመሆን የመጀመሪያው ድጋፍ ሰጭ ከነበሩት ውስጥ ነበር። በኦነግ ትንታኔ መሠረት ኤርትራ የኦሮሞ ሕዝብ ጭምር አይደለችም። እና ኦነግ ከዚህ የጠበበ የአገር ትርጉም በመነሳት «የኢትዮጵያ መፈረካከስ የኦሮሚያን መፈጠር ያፋጥነዋል» ከሚል ድምዳሜ ላይ ይደርሳል።
ምንም እንኳን ይህንን የኦነግ አቋም ለዘመናት ለተከታተልነው ወገኖች እንግዳ ባይሆንብንም፣ ለዘመናት ስለ ኦነግ አቋም ሲነገረው ማመን አዳግቶት «ጆሮ ዳባ ልበስ» ብሎ ለተቀመጠው ብዙኃን ሕዝብ፣ በ2009 ዓ.ም. (በ2016 በግሪጎሪያን አቆጣጠር) በኦሮሞዎች ስብሰባ ለንደን ላይ “ኢትዮጵያ የምትባል አገር ፈርሳ ኦሮሚያ አገር መመሥረት” እንዳለበት ከእነ ሊበን ዋቆ አፍ ፈንቅሎ ሲወጣና ተወርውሮ ሲፈነዳ፣ ብሎም ሞቅ ባለ ጭብጨባ ሲታጀብ ድንጋጤን ፈጥሯል።
የኦነግ ትንታኔ ትልቁ ችግር ሕዝብ አብሮ በመኖር የፈጠረውን መስተጋብር መገንዘብ አለመቻሉ ነው። ከአክሱም ዘመን ጀምሮ ኢትዮጵያውያን በደማቸው የጠበቁትንና ከኦሮሞዎች መምጣት በኋላ በአንድነት የጠበቁት አገር የአማሮች ወይም የትግሬዎች ብቻ አይደለም። የአገሪቱ የባሕር በር የነበሩት ወደቦች አገልግሎት ሲሰጡ የነበረው ለተወሰኑ ጎሳዎች አልነበረም። በዚህም ኦነግ ለኦሮሞ ሕዝብ ጥቅም የቆመ አለመሆኑን አስመስክሯል።
ተያይዞ መነሳት ያለበት የኦነግ አደገኛ ቀመር በሕዝብ ለሕዝብ ግጭት የፖለቲካ ትርፍን አገኛለሁ ብሎ የማስላቱ የቆየ አመለካከት ነው፡፡ ኦነግ ግቡን ሊመታ የሚችለው የጎሳ ግጭት በማስነሳት እንደሆነ ከወያኔና ከሻዕቢያ ተምሯል።
ስለሆነም በማንኛውም የኦነግ ስብሰባዎች ላይ ትናንትም፣ ዛሬም የመጀመሪያውና ዋናው የውይይት አጀንዳ አማራ ነው። እንዴት የአማራውን ቅሥም መስበር እንደሚቻል፣ እንዴት የኦሮሞውንና ሌሎቹን ነገዶች በአማራ ላይ ማስነሳት እንደሚቻል ዋናው የውይይት አጀንዳ ነው። መጀመሪያ አማራ ካልተመታ ኦሮሚያን የመፍጠሩ ጉዳይ የሚታሰብ አይደለም። ይህ ነው ዋናው የኦነግ ስሌት።
ነገር ግን ኦነግ ለረዥም ጊዜ ሲቀምረው ለቆየው የግጭቱ መፋፋም እንቅፋት የሆኑ ሁለት ነገሮች ነበሩ፦
1ኛ) በአጠቃላይ የገጠሩ ኦሮሞ ሕዝብ ከአማራ ሕዝብ ጋር በማህበራዊ ኑሮና በኢኮኖሚው የተሳሰረ በመሆኑና ሁለቱም ወገኖች ለጥል የማያመች መቻቻል ያለበት ባህል ያላቸው መሆናቸው ሲሆን፣
2ኛ) በከተማ ያለው ሕዝብ በአብዛኛው እርስ በርሱ የተጋባና የተዋለደ ከመሆኑም በላይ በአስተሳሰቡ ከዘርና ከሃይማኖት ልዩነት ዕምነት የተላቀቀ መሆኑ ናቸው።
በ1970ዎቹ መጨረሻ ላይ ኦነግ በደረሰበት ውሳኔ መሠረት ከላይ የተጠቀሱት ችግሮች ቢኖሩም ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ከጊዜ ብዛት ሁለቱን ችግሮች አስወግዶ የኦሮሞን ሕዝብ በኦነግ ሥር ማሰለፍ እንደሚቻል ታምኖበት ለዚሁ ይረዳ ዘንድ የሚከተሉት መፈክሮች በተራ አባላት በሰፊው እንዲነገርና እንዲሰራጭ ተደረገ፦
– ያ ጀሩ ጀረሪቲ ያ ጀሩ ጀረሪቲ፣ አማርቲቲን ነማ ሚቲ (አማራ ሰው አይደለም!)
– አማራን ሃሬ ዳ (አማራ አህያ ነው!)
– አማራን መግደል ነው!
– ለማሸነፍ ጠላትህን አጥብቀህ ጥላ!
– እንግዳ (መጤ) ከአገራችን ይውጣ!
– ወዘተ.
በ70ዎቹ የኦነግ የፕሮፓጋንዳ እንቅስቃሴ ከብዙዎቹ አገራዊ አጀንዳን ከሚያራምዱ የወቅቱ የፖለቲካ ቡድኖች በተለየ መልኩ በኦነግ ላይ የታየ አንድ አሳዛኝ ጉዳይ ነበር፡፡ በቀይ ሽብር የተገደሉ የኦሮሞ ሰዎች እየተመረጡ የአማራ መንግሥት የገደላቸው፣ ለኦሮሚያ ነፃነት የሞቱ ኦሮሞዎች እየተባለ በኦነግ መፅሔቶችና በራሪ ወረቀቶች ላይ ይወጣ ጀመር።
እነዚያ የኦነግ የፕሮፓጋንዳ ጽሑፎች ከገዳዮቹ ወገን እነ ቀልቤሳ ነገዎና እነ አሊ ሙሳ እንዳሉበትና ከሟቾቹ ወገን አማሮችና ሌሎች የኢትዮጵያ ዘሮችም እንዳሉ ግን አይገልፁልንም።
ጥል በተባባሰና ደም በፈሰሰ ቁጥር ልዩነት እየሰፋ ይሄዳል፣ ብዙ መተላለቅ ይደረጋል። ከዚያ በኋላ አማሮችና ኦሮሞዎች ጠላት ስለሚሆኑ አብረው ሊኖሩ አይችሉም። ይህም የኦሮሚያን መፈጠር ዕውን ያደርገዋል። ይህ ነው የኦነግ ነባርና አስፈሪ ትልም፡፡ አስፈሪ የሚሆነው ኦነግ የኢትዮጵያን ሕዝብ ደም እርስ በርሱ በማፋሰስ ለማትረፍ በመፈለጉ ነው፡፡
በዚህ ዕምነት መሠረት ከትግሬ ወያኔዎች ጋር ሥልጣን ላይ ሲወጡ፣ ኦነግ የድርሻውን ሥልጣን ያገኘ ጊዜ የወሰደው እርምጃ በደኖና ወተርን ጨምሮ በምሥራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አሩሲ፣ ባሌ፣ ኢሉባቦርና ወለጋ ውስጥ አማሮችን መግደል፣ መደብደብና፣ ማባረር ነበር። በወቅቱ የምክር ቤቱ አባል የነበረው የኦነግ ተወካይ ኃላፊነቱ የኦነግ መሆኑን አመነ። የሚያሥከትለውንም ችግር በማዬት ሌንጮ (ዮሐንስ) ለታ በአሥቸኳይ አስተባበለ።
ኦነግ በወያኔ ፊት ተነስቶት ከሥልጣኑ ሲገፈተርና ከሽግግር መንግሥት ተብዬው ሲወጣ በወቅቱ የማሥታወቂያ ሚኒስትር የነበረው ዲማ ነጎ የሚባለው የኦነግ አባል ሥልጣኑን ከመልቀቁ በፊት በመጨረሻዋ ሰዓት በኦረምኛ የራዲዮ ፕሮግራም ያሥተላለፈውን ማጤን አለብን። «በእጃችሁ ባለው መሣሪያ በጠላታችሁ ላይ ተነሱ» ብሎ ነው ከሥልጣን የተሰናበተው።
ግለሰቡ ይህንን መልዕክት በራዲዮ ሲያሥተላልፍ ሠላምን፣ አንድነትን፣ ነፃነትን፣ ዲሞክራሲን መስበኩ አይደለም። እስከዛሬዋ ዕለት ድረስ የኦነግ የመጀመሪያው ጠላት አማራ ስለሆነ፣ እንደ ሩዋንዳ ሁቱዎችና ቱትሲዎች ዓይነት እልቂት እንዲጀመር መቀስቀሱ ነበር። ግን ያልተማረው ተራ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብሮ በመኖር ያለው አስተሳሰብ ከኦነግ ብዙ የላቀ ስለሆነ፣ ኦነግ የሕዝቡን ድጋፍ ባለማግኘቱ የተመኘው ዕልቂት እንዳሰበው አልሆነለትም።
ግን ኦነግ እንደ ድርጅት ያሰበውን ያህል ባይሆንም በዚያች በሥልጣን ላይ በነበረባት አጭር ጊዚያት ውስጥ ብዙ አማራዎች ጨርሷል። ቀኝም ነፈሰ ግራ የኦነግ ሰዎች የሚደክሙለትን የመሪነት ሥልጣን ለመያዝ እድል አላገኙም*። [* ይህ ጸሑፍ ከተጻፈ ከ4 ዓመታት በፊት መሆኑን እዚህ ላይ ልብ ይሏል!]
ሰዎች ኦሮሞ በብዛት ከሚኖርባቸው አካባቢዎች (ኦሮሚያ ተብዬው) ወደመጡበት አገር ይመለሱ የሚለው የኦነግ ፖሊሲ ሥራ ላይ ቢውል ከመጥፎ የሞኝነት ሥራ ውስጥ እንገባለን። ቀድሞ የመጣው ሲኖር፣ በኋላ የመጣው ሊወጣ ነውና።
እንግዲህ አወጣጡ በኋላ ከመጣው ሲጀመር፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰፍረው የሚኖሩ ኦሮሞዎች በሄዱበት አኳኋን ከየአቅጣጫው ተሰባስበው በመጀመሪያ ወደ ኦዳ ነቤ፣ ከኦዳ ነቤ ወደ ወላቡ መመለስ ሊኖርባቸው ነው። በዚህ ጊዜ ወሎ ላኮ መልዛ፣ የጁ ቤተ አማራ፣ ወረኢሉ ዋስል፣ ወለጋም ቢዛም፣ አርሲ፣ ሲዳሞና ጎምጎፋም ፈጠጋር፣ ሐረር ደዋሮ፣ ኢሉባቡር ላሎ ቅሌ ወዘተ ይሆናሉ።
እነ ሌንጮ ለታ፣ እነዲማ ነጎ፣ እነ ዲማ ጉርሜሳ (ሻምበል ወልደሰንበት)፣ እነአሰፋ ጀለታ፣ እነ ሌንጮ ባቲ፣ እነቦሩ በረካ ከያሉበት ሄደው በነገሌና በአባያ አካባቢ ወደሚገኘው ወላቡ ይገናኛሉ ማለት ነው እነግዲህ። ከዚያም ወደ ቤናድር አውራጃ ቀጥሎም ወደ በርበራ ይሄዱና ይሠፍራሉ። እዚህ ላይ አንድ የሚነሳ ችግር አለ። ከኦሮሞና ከሌላ ዘር የተወለዱ ሰዎችስ እንዴት ይሆናሉ?
ለዚህ ኦነግ አስቀድሞ የወሰነውን መፍትሔ ሥራ ላይ ያውል ይሆናል። ተደጋግሞ እንደ ሰማነው የትግሬው ወያኔ በትግሉ ወቅት እንቅፋት ናቸው ያላቸውን እንዳረዳቸው ሁሉ፣ ለኦነግ ትግል እንቅፋት ናቸው የሚባሉት እነዚህ ሰዎች መጀመሪያ መታረድ አለባቸው። ይህ ሲሆን ደግሞ ብዙ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያልቃል። በዚህም ኦነግ እወክላለሁ የሚለውን ሕዝብ አለመወከሉን እናረጋግጣለን።
ይህን የኦነግ የውጡልን ጥያቄ ሠፋ አድርገን ካዬን የበለጠ ከልጆች ጨዋታ የባሰ ከንቱ ሆኖ እናገኘዋለን። ከላይ ባጭሩ ልናሳይ እንደሞከርነው ዛሬ አብዛኛው የዓለም ሕዝብ የሚኖርበት ሥፍራ የመጀመሪያው ትውልድ የኖረበት ሥፍራ ሳይሆን በዝውውር የሰፈረ ነው።
ከሰሜን አሜሪካ ብንጀምር በኦነግ ቀመር መሠረት እነግዲህ ድፍን አሜሪካና ካናዳ ወደ አውሮፓ መጓጓዝ አለበት። ለዚህም ምን ዓይነት መጓጓዣ ይበቃ ይሆን? እነ ክሊንተን፣ እነ ቡሽና ትራምፕ ከእነ ቤተሰቦቻቸው መጀመሪያ መሣፈር ሊኖርባቸው ነው። ጥቁር የሰሜን አሜሪካ ሕዝብ ወደ አፍሪካ መሄድ አለበት። ነባር ናቸው የሚባሉት ዘሮች ደግሞ ወደ እስያ መሄድ አለባቸው።
የኦነግ ሕዝብ-አፈናቃይ ቀማሪዎች ኦሮሞ ውሎ ያደረበት ምድር ሁሉ ኦሮሚያ ይሆናል ካላሉን በስተቀር፣ በአሜሪካና አውሮፓ ግሪን ካርድና ዜግነት የወሰዱትም ኦሮሞዎች ወደ ወላቡ ከዚያም ወደ ቤናድርና ወደ በርበራ መቀጠል ይኖርባቸዋል ማለት ነው።
በዚህም ገፅታው ሲታይ የኦነግ የውጡልን ጥያቄ የፖለቲካ ቂልነት እና የቲዎሪ ድህነት የሞላበት፣ በማንኛውም መንገድ የአንድ ጎሳ መንግሥት መሥርቶ ሥልጣን ለመጨበጥ መሆኑን መገንዘብ አያዳግትም።
Filed in: Amharic