እስክንድር ነጋ አልታስረም…!!!
ፋሲል መሳይ
እስክንድር ነጋ አልታሰረም ካላመንከኝ የትናንቱን ሰላማዊ ሰልፍ ተመልከት ።
እስክንድር ነጋ በሁሉም ልብ ውስጥ ካለ የእስክንድር ነጋ ስጋት እብድ ያስባለው ሰጋት በኢትዮጵያ ተፈፅሞ በድጋሚ በከፈ ሁኔታ ሊደገም ሲል እስክንድር ነጋ ያለው እውነት ነበር ከተባለ ።
እስክንድር ነጋ አልተሠረም
የ እስክንድር ነጋ አቋም ሁሉም ከያዘው እና ድምፅ ካረገው ።
እስክንድር ነጋ አልተሰረም
የእስክንድር ነጋን ቅድሚያ ሲናገረው የነበረውን ነገር ኢትዮጵያ ውስጥ ጄኖሳይድ ሊደረግ ነው ስሞታ ቀድሞው በያግዙትም ጄኖሳይዱ ከተፈፀመ በኃላም ቢሆን በዓለም ፍርድ ቤት ለማቅረብ የተካሄደበትን መንገድ ጥሩ ነው እና አበረታች ሰለ ሆነ ።
አዲስ አበባ ሲነሳ እስክንድር ነጋ ይነሳል ።
አዲስ አበባ ከተማ ከተመሰረተች አንድ መቶ ሰላሳ አራት ዓመት እየሆናት ነው ።
የከተማዋ የኢኮኖሚ እድገት ከፍ እያለ
ቢመጣም በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ኃላ ቀርታለች ። በተለይ ከ1983 ወደዚህ መጠነ ሰፊ ተግዳሮቶች አጋጥሟታል። አንድኛው ሊዚህ ችግር ያጋለጣት ሁሉም በዘር ቅርጫት ውስጥ ሲገቡ አዲስ አበባን ክልል 14 የነበረችውን ከተማ አወርደው የከተማ መስተዳድር ብለው ተጠሪነቷን ለፌደራል መንግስት አድርገው ለዘረፋ አመቻችተው አዋቅሩ ። ይሁን እንጂ በዘረኞች እጅ የወደቀችው አዲስ አበባ እና አዲስ አበቤ ከዚህ የዘር ቅርጫት ለመውጣት የ1997ቱ ምርጫ እና የህዝብ ማዕበል በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያውያን ላይ ተስፋን ፈነጠቀ። አዲስአበቤም በተማኝነት ድምፁን ለልጆቹ ሰጠ። ዘረኛነት በኢትዮጵያ እና በአለም አደባባይ እራቁቱን ቀረ። ይህን ተከትሎ የከተማ መስተዳድር የነበረችው አዲስአበባ በተጨማሪ የኦሮምያ ዋና ከተማ እንድትሆን ሲወሰን በወቅቱ ተፈጥሮ የነበረውን ሀገራዊ ቀውስ ለማረጋጋት አዲስአበባን በስጦታ መልኩ ለኦሮምያ ክልል አበረከቱ። ሌላኛው መከራችን ከዚህ ይጀምራል ማለት ነው።
….በኢህአዴግ መዋቅር ውስጥ በዘር ሊበክሉት መጠነ ሰፊ እንቅሰቃሴ ቢያደርጉም አዲስ አበቤ ወይ ፍንክች ማለቱ በነሱ የዘር መዋቅር ውስጥ አለመግባቱ የቆጫቸው የኢህአዴግ ሰዎች በዘር አልከፋፈልም ስላለ ህዝቡን በወጣት ሊግ በሴት ሊግ እያሉ ያልሞከሩት አልነበርም አዲስ አበቤ ግን ወይ ፍንክች ብሎ የአዲስ አበቤነት ስነልቦናን ተላብሶ አሸነፋቸው ።
…ህወሃት መራሹ ኢህአዴግ ደደቢት ተወልዶ ኢትዮጵያ ውስጥ አድጎ አዲስአበባ ሲሞት የቀብር ስነስርዓቱ በተወለደበት ደደቢት በተወለደ በ30 አመቱ እየተፈፀመ ባለበት ሁኔታ ታናሽ ወንድሞ ኦህዴድ ተረኝ ሆኖ አዲስ አበባን እና አዲስ አበቤን እንዲሁም ኢትዮጵያን ህልውናዋን የሚፈታተን የመከራ ጊዜ ላይ መሆናችን የሚታወቅ የአደባባይ ሚስጥር ነው።
…ልዩ ጥቅም በሚል የተቀበረው ፈንጂ ዛሬ ወደ ባለቤትነት አድጎ የሁሉም ኢትዮጵያዊ እናት የነገበረችው አዲስ አበባ አሁን ለአንደኛው እናት ለሌላኛው የእንጀራ እናት ሁና አንደኛው መጤ ሰፋሪ ሌላኛው ባለቤት በሚል የዘገምተኞች ፖለቲካ እየተወረረች ትገኛለች። የአዲስ አበባም ህዝብም በዚህ ሁኔታ ተጨነቀ ተጠበበ ትንሽ እንደቆየ በቡራዩ ዘር ተኮር ጭፍጨፋ ተካሄደ ፊንፊኔ ኬኛ የሚል ቃል በሙሉ አገር ተስፋፋ ከኢትዮጵያ አልፎም ከውጭም መሰማት ጀመረ። ውጡ የሚል ዘፈን ተዘፈነ ይህ ብቻ አይደለም መንግስታችን ተነካ ብለው ከስሉልታ ከለገጣፎ እየመጡ ነበር ብሎ በፓርላማ የአዲስ አበቤ መንግስት እንዳልሆነ አስረግጦ ነገረን። አሁን የመጨረሻው ፌሽካ ተነፋ ማለት ነው። አሁን አዲስ አበቤ መመካከር መነጋገር ጀመረ ማለት ነው።
…ይሄ ሲሆን የአዲስ አበባ ህዝብ ሲጨነቅ አዲስ አበቤ እየጨፈር ያሰገባቸው ፖለቲከኛ ነን የሚሉ እና የሰባአዊ ተከራካሪ ነን የሚሉ በሙሉ ድምፅ በጠፈበት ሰዓት አንድ ሰው ብቅ አለ ለአዲስ አበባ ለትንሿ ኢትዮጵያ ሊቆም ቃል ገባ ።
…በዚህ ቆራጥ ልበ ሙሉ ጀግና የተነሳ አዲስ አበቤ በድጋሚ ተሰፋ አየ። የዛሬ ሁለት ዓመት ባልደራስ ሲቪክ ማህበር ሆኖ ተቋቋመ። አሁንም አዲስ አበቤን ለመወጥ የቆረጠው መንግስታዊ አካል በግልፅ በመዛት ግልፅ ጦርነት በትንሿ ኢትዮጵያ ተወካይ ባልደራስ ላይ የስብሰባ አዳራሾችን በመከልከል እርምጃውን ሀ ብሎ ጀመረ። ልዩ ጥቅም እና በአንዳንድ የኦሮሞ ፅንፈኛ የሚመጣውን የኬኛ ጥያቄ የመንግስትም መሆኑን በአደባባይ አስመሰከረ ።
… አይበገሬው እስክንድር ነጋ ህወሃትን በብዕሩ ካሸነፋት እና ለኢትዮጵያውያን የሰላማዊ ትግል ተምሳሌት የሆነውን መሳሪያ እንማዘዛለን በሚል ንግግር እንዲሁም በሰኔ 15/2011 የግድያ ሙከራ በማድረግ መንግስት ለኬኛ ጥያቄ በተዘዋዋሪ መልስ ሰጠ ።
…መንግስት ይህን ካለ በኃላ ልዩ ጥቅም ወደ ኬኛ ሙሉ በሙሉ ዞረ ይሄ ሁሉ ሲሆን ለምን ያለ ፖለቲካ ፓርቲ ወይም ግለሰብ አልነበረም ። የአዲስ አበባ ህዝብ እኔን ጨምሩ ጨፍረን ሰርገኛ ይሆናሉ ያልናቸው ሚዜ ይሸለናል ብለው ዶሮ ሳይጮሁ ከዱን ።
…እንዲሁም መግለጫ ማወጣት ምን ይሰራል ወደ ሚል መታበይ ውስጥ ገቡ በተለይ መሰቀል አዳባባይ አምስት ሰው በስናይፐር ሲገደል ቴዎድሮስ ፀጋዬ ርዕዮት ላይ የቀረቡት ግርማ ሰይፉ እና የሺዋስ አሰፋ ለትንሽ ትልቁ መግለጫ አናወጣም እኛ የመግለጫ ፓርቲ አይደለንም ያሉትን አስታወሳለሁ ።
…ከአንድ ዓመት በኃላ የባልደራስ የሲቪል ማህበር ( የትንሿ ) ኢትዮጵያ መሪ ወደ አሜሪካ አቅንቶ በተለያዩ ድርጅቶች ኢትዮጵያ ላይ ጄኖሳይድ ሊከሰት እንደሆነ ቀድሞ የተረዳው ታላቁ እስክንድር ለኢትዮጵያውያን እና ለአለም መንግስታት ተናገረ። ይህን ሲል ከሃገር ውስጥ እስከ ወጪ ያሉ ተደማሪ ተደገፊዎች እብድ ብለው ሊሳለቁበት ሞከሩ። ይሆን እንጂ ጊዜው ደርሶ የያኔው እብድ ጤነኛ የዛን ጊዜ ጤነኞች ደግሞ እብድ መሆናቸውን ታላቁ እስፔሻሊስት ዶክተር ጊዜ ደጉ አሳየን። አንዳንዶቹ ከጥፋት መንገዳቸው ሲመለሱ ቡዙዎቹ አይናቸውን በጫው አጥበው የቁልቁለት መንገዱን ተያይዘውታል። ይህ በእንዲህ እንዳለ…
…በዚያው መድረክ ላይ ለኢትዮጵያ ጥሩ ሀሳብ ባላቸው ኢትዮጵያዊያን እና በአዲስ አበቤ ጥያቄ መሠረት ባልደራስ ወደ ፖለቲካ ፓርቲነት አደገ። በቆራጡ ታጋይ እስክንድር ነጋ እየተመራ አዲስ አበባ ክልል ነበረች ክልልም ትሆናለች ( አዲስ አበባ እራስ ገዝ ) ከተማ ትሆለች በሚል ቆራጥ ውሳኔ በፓርቲነት ቀጠለ ።
…ባልደራስ ለሁሉም ከሁሉም የተቋቋመ ፓርቲ በመሆኑ ምክንያት እንኳን መንግስት የመንግስት ተቀዋሚ ፓርቲዎች ዘመቱበት። አንዳንዶቹማ በህብረ ብሔራዊ ስም ተደራጅተው ጭራሽ ገዥውን ፓርቲ ሳይሆን እኛን ይታገሉን ጀመር። ምክንያቱም የባልደራስ ሃሳብ ትልቅ እና ተራማጅ እንዲሁም የኢትዮጵያን ችግር መንገድ ጠራጊ እንደሆነ ስለተገነዘቡ ነው። የባልደራስ አካሄድ የዘር ፖለቲካን ከኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ ባይሆን እንኳን በግማሽ ያኮላሸዋል። በተለይ ደግሞ አዲስ አበቤ ወደ ቀድሞ ክልል 14 ( እራስ ገዝ ) ከተመለሰች የኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ችግር ሃምሳ በመቶ ይፈታል። ምክንያቱም የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሚያጠነጥነው አዲስአበባ ስለሆነ ነው።
…ይሁን እንጂ ብረቱን እስክንድር ነጋን እና ባልደረቦቹን እያሰሩ እየፈቱ ከአላማው ለማሰናከል ቢሞክሩም አልተሳካም ። ቪ8 መኪና ሲቀርብለት ቤተመንግስት ጥሪ ሲደረግለት ላመነበት ሟች የሆነው ታላቁ እስክንድር ሁሉንም እንዳመጣጡ በመመለስ እኔ የቆምኩት ለህዝቤ እና ለህሊናዬ ነው ብሎ በአጭሩ አይበገሬነቱን ዳግም ለኦህዴድ ብልፅግና እና ለተደጋፊ ተደማሪው አሰረግጦ ተናገረ። በተግባርም አሳያቸው።
… እዚህ ላይ ሳልገልፀው ባልፍ የሚቆጨኝ ነገር የኢሳት ዕለታዊ ላይ እስክንድር ነጋ ቄሮን ተሳደበ። በጅምላ የኦሮሞን ህዝብ ወነጀለ ብለው መሳይ መኮንን ሲሳይ አጌና እና አጋሮቻቸው የተወያዩት በጣም የሚያሰገርም ነበር። ስድስት ዓመት የእስክንድር ነጋ ፎቶ በመሸጥ ይተዳደሩ የነበሩት ኢሳቶች እስክንድር ነጋ አርበኛ ባለው አፋቸው የጥላቻ ሰባኪ አሉት። በእኔ እምነት አስክንድር የተናገረውን በማጣመም አሁን ለተከሰሰበት የውሽት ክስ የመጀመሪያውን የድረሰት ክስ ለአቃቤ ህግ አቅረበዋል ባይ ነኝ። ለዚህ ደግሞ ኢሳት አይነተኛ ሚና ተጫውቷል።…እስክንድር ነጋ የአዲስ አበቤን ወጣት ይዞ በጥሩ ሁኔታ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ እየመራ ባለበት ሰዓት ጊዜ እና ቦታ ይጠብቁ የነበሩት ዶክተር አብይ የሀጫሉ ሁንዴሳን ሞት ምክንያት በማድረግ ቢያስሩትም ከዚህ በኋላ የአዲስ አበባ ህዝብ ብቻ አይደለም በኢትዮጵያ ህዝብ ህሊና ውስጥ የሚቀመጥ ጥያቄ አስቀመጧል። አዲስ አበባ ክልል ነበረች ክልልም ትሆናለች። አዲስአበቤ እራሱን በራሱ ታስተዳድራለች።
…ይህ የትግል መሰመር ለትውልድ የሚቀመጥ ታሪክ የሚያወሳው ይሆናል። ሰለ አዲስአበባ ሲነሳ እስክንድር ነጋ የትግሉ ችቦ ለኮሽ ፋና ወጊ ሁኖ ለዘላለም ሲወሳ ይኖራል። አዲስ አበባን ወደ ክልልነት ለመቀየር እና የአዲስ አበባ እራስ ገዝነት ለማረጋገጥ ከፊት ተሰልፎ ዋጋ እየከፈለ መሆኑን ያየን እንመሰክራለን ለወደፊቱ ትውልድ ታሪኩን ሳይጨመር ሳይቀነስ እናወርሳለን።
…ወንድሜ ፣ እህቴ ፣ እናትና አባቶች የአዲስ አበባ ህዝብን ወክሎ ለመጀመሪያ ጊዜ የተቋቋመው ፓርቲ የእስክንድር ነጋ ባልደራስ ብቻ ነው ። ባልደራስን ከመረጡ አዲስአበባን እራስገዝ እድትሆን የራሱን ታሪክ አሰቀመጡ ማለት ነው።