ከመተከል እስከ አብደራፊ(ምድረ ገነት)በወፍ በረር!!!
ግዛው ዳኛቸው
* በመተከል አዋሳኝ ድንበሮች የሞት በቃኝ ህዝባዊ ትግሉ በድልና በመስዕዋት ቀጥሏል!!
* የአማራ ልዩ ሃይል ተገፍቶ እና ተመሮ እንዲበተን በውስጥም በውጭም እያሴሩበት ው!!
የህወሓትን ግራካሱ ምሽግ እንዳልነበር ያደረገችው የነበልባሉ የአማራ ልዩ ሃይል ከአብድራፊ ሰላም በር ማዶ ያደፈጠውን የሱዳን ጦር እያናገረው ነው !!
በመተከል ዝም ብሎ እየተሰቃዩ ከመሞት የዘለለ ገድሎ የጀግና ታሪካዊ ሞትም መሞት ተቀጣጥሏል። ይህ አብዩት ሲነሳ ያየው የገዳይ ቡድን በመንግስት ስም ያሉትን አለቆቹን አቤት ብሎ እንዲደርሱለት አመልክቷል።
ህዝብ ካለቀ በኃላ ገዳዩ የአብይ ቡድን ሌላ መካናይዝድ ጦር አስገብቷል!!
እስካሁን የኦሮሙማውን ገዳይ ቡድን የከፈተውን ጥቃት መከላከያ ማስቆም እያለበት በዝምታ ካየበት ፤ የአማራ ልዩ ሃይል ገዳይ ቡድኑን እንደለመደው መደምሰስ እየቻለ ተከልክሎ በቆመበት ሞት በቃኝ ብለው ለመመከት በገቡበት የመተከል አዋሳኝ ግንባሮች ገድለው ከተሰው ጀግኖች ውስጥ እስከአሁን 5 ቻግኒ ከተማ የተቀበሩ ሲሆን ከሰአት በኃላ ነበልባሉ የአማራ ልዩ ሃይል የብሬን ሽፋን በመስጠት ተጨማሪ የ 2 ጀግኖች አስከሬን እንዲወጣ በማድረግ ቻግኒ ከተማ እንዲቀበሩ ተልኳል።
በነገሮች ሁሉ ህዝባዊ ትግሉ ቀጥሏል።ለመሞት የማይፈልግ ሁሉ ከኃላው የሚያርደው እንጂ የሚያተርፈው መንግስት እንደሌለ አውቆ እራሱን ያዘጋጂና የጠላትን ጥቃት ይመክት።
ከ5 ወር በፊት በራያ ግንባር የህወሓትን መተማመኛ የግራ ካሱን ምሽግን ከአማራ ኮማንዶው ጋርሽ እንዳልነበረ ያደረገችው ሃይል አውደራፊ (ምድረገነት) ተቆናጣለች።
ሰላምበር ፣ አሴራ ፣ ባናት እስከ ማይካድራ ለመፈርጠጥ እንዲመቻት በያዘችው ብዛት ተሽከርካሪ ዛሬ መጡብኝ ነገ መጡብኝ እያለ በፍርሃት እየተኮሰ የሚያድረውን በህወሓት ቅሪት መሪነት የወረረውን የሱዳን ጦር ከፊት ለፊቱ እያንቦዥቦዥው ይገኛል።
ነበልባሉ የአማራ ልዩ ሃይል እንደ አማራ ክልላችን ሳይሆን እንደ ኢትዩጲያ እንደ ሀገር ትልቁን ሀገር የማዳን ተግባራችንን በኦሮሙማው ሴራ እና ቁማር እያወቅነው ሁሌም ከእኛ ኃላ የሚሰለፈው መከላከያ እንኳን ጠላት ትንኮሳ ሲያደርጉ የአፀፉ ምት ስንመልስ ‘ እኛ አትተኩሱ ተብለናል ‘ እያለ እየሰማን በአብደራፊ ግንባር ከሰላም በር ወጣ ብለው የሱዳንና የህወሓት ጦር ሁሌም ዝግጁ ሁኖ በሚያስፈራው አባታችን ባላበሰን ግርማ ሞገግ እያናገረው ይገኛል።
የመተከል ህዝብ ካለቀ በኃላ ገዳዩ የአብይ ቡድን ሌላ መካናይዝድ ጦር ወደ መተከል ዛሬ መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ.ም አስገብቷል።
በኦነጎች ስውርና ግልፅ እጆች የሚመራው እና ከባህርዳር ወደ ወለጋ ደዴሳ በተጠና መልኩ የተወሰደው የምዕ / ዕዝ የጉምዝና የኦነግ አስፈላጊውን ትጥቅና ቦታወች ካሲያዘ በኃላ ዛሬ ላይ ህዝብን ለመታደግ በማስመሰል በደም ወደ ምትታጠበው መተከል ገብቷል። መግባቱን አንጠላም ። የምንጠላው ተግባሩ ዙሮ ህዝብን የወጋ እለት ነው።
የምንጠላውና የምንቆራረጠው ለጉምዝና ለኦነግ ጦር ሽፋንነቱን በተግባር እንደቀደመው ሁሉ ስናይ ነው።
በእርግጥ ይህንን ያደረገው ህዝብ ሊታደግ ሳይሆን የግብፅንና የሱዳን በአባይ ግድብ ዙሪያ እየነዙት ያለው ፕሮፕጋንዳ ተጠቅሞ የህዝባዊ ድጋፍ ለማግኘት ነው።
ሁሉንም ጊዜ ሲኖረን ከጉድጓድ ስንወጣ በየቀጠናው ያለውን ለማካፈል እንሞክራለን። ሁሉም አማራ ባለበት ይበርታ!! አይናችሁን ወደ ነፃነቱ መሬት የነካው ተግባራዊ ትግል እንጂ ለማስቀየሻ ወደ ሚወረወሩ አጀንዳወች አትጠመዱ !!
የአማራ ልዩ ሃይል ተገፍቶ እና ተመሮ እንዲበተን በውስጥም በውጭም እያሴሩበት ው!!
ከህዝብ የተሰበሰበው ተሽከርካሪ ተገዝቶበታል- ኑ አብረን እንፈር
የሚያስፈልገንን በመንሳት መስዕዋትነታችንን ብቻ የምትፈልጉት ፤ በእኛ ድካምና ጉዳት ፥ በረሃ ለበረሃ መንከራተት፥መቁሰልና ሞት ስልጣናችሁን አደላድላችሁ እንድትኖሩ የምትሹ አመራሮች ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ እናሳስባለን !!
ሀሳባቸውን እና ፣መሰረታዊ ጥቅማጥቅማቸውን የለም በመባሉ ቅሬታቸውን እንዳያቀርቡ የተከለከሉ ጓዶች ውስጥ በርካቶች መስዕዋታችንን እንጂ የእኛ መኖር አይፈልጉንም በማለት አሃዳቸውን ጥለው እየወጡ ነው!!
ባለፉት 2 ወራት ውስጥ በጡረታና በዲስፒሊን በማሳበብ ከ2መቶ በላይ አባላትና የታችኛው አመራሮች ከአማራ ልዩ ሃይል እንዲገለሉ ተደርጓል።
የተሰው ጓዶች ለቤተሰብ ለልጆቻቸው እና የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ጡረታ እንዳይተከል እያደረጉ ይገኛል።
የጭንቁ ቀን ስልጣናቸው ሊነካ ሲል በፈጠሩት ቁማር ከህወሓት ጋር ለመግጠም የቱርክ ሽጉጥ ሰጠው ያስጠጉንን ምን እናደርግላችሁ እያሉ ሲሽረከረኩ የነበሩት የኦሮሙማ ምስለኔወች የኦነጉ ሴረኛው አብይ አህመድ የእጂ ስራወች የራሳቸውን ቢሮ ተቀምጠው የውሎ አበላቸውን እየላጡ የነበልባሉን የአማራ ልዩ ሃይል በረሃ ለበረሃ እየተንከራተተ ህይወቱን እየገበረ እንደሀገር ለፈፀመው ትልቅ ጀብዱ እና ለከፈለው መስዕዋትነት ትንሿን ደሞዝ ተብየ በጊዜ እንኳ መክፈል የማይችሉት እሱን ለሚጠብቁ ልጆቹ እንዳይደርስ ያደረጉ ሆድአደር ባንዳወች የአማራ ህዝብ ከሀገር ውስጥ እስከ ሀገር ውጭ በተጋድሎው የተበረከተለትን እያንዳንዱ ድጋፍን የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በልተው በመካድ የአማራ ልዩ ሃይልን ተጋድሎውን ክደው ወረታውን እረስተው ከኦሮሙማ/ኦነጉ ሴረኛው አብይ የተሰጣቸውን ተልኮ በመፈፀም ተመሮ እንዲበተን እየሰሩ ነው።
የአማራ ህዝብ በተለያየ አቅጣጫ የተበረከተለት ምንም አይነት ነገር ለልዩ ሃይሉ አልደረሰውም።
ይልቁን ለእያንዳንዱ የሚደርሰው ተወስኖ ይሰጣል ባሉን መሰረት ፣ የ5 ወር የበረሃ የውሎ አበል በሲቪል ሰርቪስ አሰራር መሰረት ይከፈላል ያሉትን ይከፍሉናል እያልን ስንጠብቅ በየብርጌዱ ከፍተኛ አመራሮች በኩል ምንም አይነት ጥያቄ መጠየቅ አትችሉም። አንድም የሚሰጥ ጥቅማ ጥቅም የለም ፣ ከህዝብ የተሰበሰበውንና ከባለሃብቶች የተለገሰውን መኪና ገስተንበታል። ማንም ምንም መጠየቅ አይችልም። እንደዜጋ ከዚህ በፊት የተደረጃችሁት የመኖሪያ ቤት መስሪያ ጉዳይ በተለይ ባህርዳር ላይ የተደራጃችሁት ማንም መጠየቅ አይችልም።በማለት ጥያቄና ሀሳብ ያላቸውን አባላት መናገር አትችሉም በማለት አፍነዋል።
ይህን የሚሉት አመራሮች ተሽከርካሪው ቢመጣ ለአመራሮች መንቀሳቀሻ እንጂ የቆሰለን ጓድ እንኳን ህክምና ማድረስ የሚከለከሉ ሲሆን ለእነሱ እያንዳንዱ ቀን የውሎ አበል የሚወስዱ እንዲሁም ባህርዳር ከተማን ጨምሮ በልዩ ኬዝ እየተባለ የመኖሪያ ቤት ቦታ እንዲያገኙ የሚያደርጉ መሆናቸው ህዝብ ሊያውቀው ይገባል።
እስካሁን የአማራ ልዩ ሃይልን በመካድ እና ተሰላችቶ እንዲበተን በጀመሩት ዘመቻ ከ10 ያላነሱ አባላት አሃዳቸውን ጥለው ተገፍተው እንዲወጡ ተደርጓል።የቀረነው ደግሞ አስቸኳይ እርምት እንዲፈጥሩ በማስጠንቀቅ መልስ እየተጠባበቅን እንገኛለን።
የአማራ ልዩ ሃይልን የኦነግ ተወካዩች መስዕዋትነታችንን ቢያጠለሹ አይግረማችሁ ክደው እንድንበተን በተልዕኮ የሚፈልጉ የእኛው ሆዳም አመራሮች አሉና!!
እጂግ ብዙ ግፎች እየተፈፀሙብን ብንገኝም ከዛሬ ነገ ይሻላል እያልን ከእኛ መከፉትና መበደል ከወገን ሞት አይበልጥም ብለን ዝም አልን ።
– ከስውሩ ጓድ የአማራ ልዩ ሃይል አባል