>

ኦሮምያ ዛሬም የአማሮች መታረጃ ቄራ - እስከ መቼ...???  (ታደለ ጥበቡ)

ኦሮምያ ዛሬም የአማሮች መታረጃ ቄራ – እስከ መቼ…??? 

ታደለ ጥበቡ

*…. በስልክ ያነጋገርናቸው ሰዎች እንደሚሉት ከሆነ የእህል መጋዝናቸውን አላስነካም ያሉ አማራዎች፣ መጋዝን ተቆልፎባቸው ተቃጥለዋል!!
 
በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ጊዳ አያና ወረዳ መንደር በየቀኑ  10 እና 9 ንፁሃን አማራዎች በኦሮሚያ ልዩ ሀይሎች እየተጨፈጨፉ፣ ንብረታቸውን እየዘረፉና እያቃጠሉ ናቸው።
በስልክ ያነጋገርናቸው ሰዎች እንደሚሉት ከሆነ የእህል መጋዝናቸውን አላስነካም ያሉ አማራዎች፣ መጋዝን ተቆልፎባቸው ተቃጥለዋል።
ሬሳ ማንሳት አልቻልንም ሸሽተው ወደ ጫካ የገቡም አሉ ብለዋል። በመንደር 10 አዋሳኝ በሆነው መንደር 8 ላይ ቁጥራቸው ያልታወቁ አማራዎች በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ተገድለዋል። ኗሪዎች አሁንም ድረሱልን እያሉ ናቸው።
Filed in: Amharic