>

ኦህዴድ ና ኦነግ ምናምን ናቸው....???  (ጌታነህ ካሳሁን)

ኦህዴድ ና ኦነግ ምናምን ናቸው….??? 

ጌታነህ ካሳሁን

*,,,, ባንክ ዘራፊ: አጭበርባሪና ከሃዲ የሚሾምባት የጉድ ሀገር ኢትዮጵያ…!
 
1) ሰሞኑን የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ባወጣው ሪፖርት 81 በዳቦ ስም የ”ኦነግ-ሽኔ” በሰሜን ሸዋ አጣዬና አካባቢው በጭፍጨፋ የተጠረጠሩ (በተግባር የኦህዴድና ኦሮሞ ክልል) ታጣቂ ኃይሎች በ”በላይ አካል” ትዕዛዝ መለቀቃቸውን ማሳወቁ ይታወሳል:: ለታሪክ ተመዝግቧል:: እንብበናል:: ባንገረምም በኦህዴድ መንግስት ተብዮ ይበልጥ አዝነናል::
2) ከሁለት ዓመት በፊት በታህሳስ 2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የዘረፉ የኦነግ አሸባሪዎች–ከቅጣት ተነስተው በኦህዴድ ሹመት እንደተሰጣቸው ስንቶች እናስታውስ ይሆን? ከታች የተያያዘውን በወቅቱ በሪፖርተር ጋዜጣ የወጣውን ዘገባ ይመልከቱ::
ሰሞኑን ሰሜን ሸዋ ላይ አማራዎችን የጨፈጨፉ: ያቃጠሉና ያፈናቀሉ “ኦነግ-ሸኔ” (የኦሮሞ ክልል ልዩ-ልይ ኃይሎች) በወንጀል ያለመጠየቅ “በበላይ አካል ትእዛዝ” መለቀቅ ብቻ ሳይሆን ሊሾሙና ሊሸለሙ እንደሚችሉ የከዚህ በፊት ተሞክሮ ይመሰክራል::
በኦህዴድ አይን ጭፈጨፋ ሳይሆን ተልእኮ ነው የተፈፀመው:: ኦነግ/ሸኔ እና ኦህዴድ ምንና ምን ናቸው?
Filed in: Amharic