>
5:28 pm - Tuesday October 10, 6305

የአብይ ሸኔ፣  ሽሜ ሸኔ ጥምር ጦር የአማራውን ጎጆ በውድቅት ለሊት ሲያነደው አደረ...!!! (ሀብታሙ ምናለ)

የአብይ ሸኔ፣  ሽሜ ሸኔ ጥምር ጦር የአማራውን ጎጆ በውድቅት ለሊት ሲያነደው አደረ…!!!

ሀብታሙ ምናለ

ይህ የምትመለከተው የህዳር ሚካኤል ጭስ እንዳይመስልህ  የነሽመልስ አብዲሳ (ኦህዴድ ሸኔ ጦር) እንደ ጧፍ የሚያነደው የአማራ አርሷደር ቤት ነው።
ለሊቱን ከወለጋ እስከ መተከል በጎጆው እሳት እየለቀቁ፣  ጎተራውን፣ ሰብሉን እየማገዱ … የሽመልስ አብዲሳ ሰራዊቶች፣  የአብይ አህመድ ሸማቂዎች… ግዳይ ጥለው ይሸልላሉ…
በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ መንደር 10 ቀበሌ በውድቅት ሌሊት  ጭፍጨፋ ተፈፅሟል። በዚህ ሰዓት የዘር ማጥፋት ወንጀል ሰለባ የሆነው የአማራ ማህበረሰብ  ቤቶች በእሳት እየጋዩ መሆኑን ከስፍራው እየተነገረ ነው።
በዚሁ መንደር ባለፈው የካቲት 21/2013 ዓ/ም የኦሮሚያ ልዩ ኃይል በንፁሃን ላይ በከፈተው ተኩስ በርካታ የአማራ ብሔር ተወላጆችን መግደሉ ይታወሳል።
ከሌሊቱ 9:40  የእናቶችና የህጻናት የድረሱልን የጭንቅ ጩህት ያስተጋባል …ቤቶች እንደ ጧፍ ይነድዳሉ  ሰሚ የለም።
ሰላም ሚንስትር የዩኒፎርም ምርቃት፣  ባጫ ደበሌ ለዱቄት እናቡንን መግለጫ፣   ብርቱካን ሚደቅሳ “ጭሱ ቢጋርዳችሁም በነዲድ እሳት የከሰለ የልጆቻችሁን አፅም እንዳትረግጡ ተጠንቅቃችሁ ዴሞክራሲ እንዲያብብ  ኑ ምረጡ” …  እዚህም እዚያም ጥሪ ነው።
ድምፃችንን አሰሙልን የሚል ጩህት ያስተጋባል
Amhara Media Corporation
Amhara Communications
Agegnehu Teshager
Demeke Mekonnen Hassen
Ethiopia Insider
Temesgen Tiruneh – ተመስገን ጥሩነህ
እንግዲህ ምን እንላለን እግዚአብሔር  ይፍረድ !!
Filed in: Amharic