>

አጣዬ በኦነግ ታጣቂዎች በከባድ መሳሪያ ስትደበደብ አደረች ...!!! (ሕብር ሬዲዮ)

አጣዬ በኦነግ ታጣቂዎች በከባድ መሳሪያ ስትደበደብ አደረች …!!!

ሕብር ሬዲዮ

*…. አጣዬ  ከትናንት ምሽት ጀምሮ በኦነግ ታጣቂዎች እና ሰላማዊ አማራዎች መካከል ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ እየተካሄደ ነው፣በርካታ የአማራ ሕዝብ ተጎድቷል፣ሕፃናትና ሴቶች ከተማውን ለቀው እየወጡ ነው። የተኩስ ልውውጡም በከባድ መሳሪያ የተደገፈ ነው!
 
የኦነግ ሽኔ ታጣቂዎች ማምሻውን በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት በአጣዬ ከተማ ህዝብ ላይ በመክፈታቸው ሕዝብ እየተሸበረ መሆኑን አሁን ከስፍራው መረጃ ደርሶናል።
የሚመለከታችሁ የመንግሥት ባለሥልጣናት ይህን በንጹሃን ሕይወት የሚቆምር የወረራ እርምጃ በአስቸኳይ እንድታስቆሙና ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጭምሮ ተጠያቂ የሚሆኑበት የዚህ መሰሉ የዘር ጭፍጭፋ አጠቃላይ አገሪቱን ወደ ትርምስ የሚወስድ በመሆኑ በመንግሥት ውስጥ ያላችሁ ወገኖች በዚህ መሰሉ ድርጊት ግንባር ቀደም የሆኑ ሀይሎችን ለማስቆም ሕዝብን መሰረት ያደረገና ንጹሃንን ከጥቃት የሚከላከል እርምጃ በመውሰድ ሀላፊነታችሁን ልትወጡ ይገባል።
ቀን ምሥራቅ ወለጋ ንጹሃን ላይ ጭፍጨፋ የፈጸመው የኦሮሞ ልዩ ሀይል ምሽቱን በዚህ ሀይል ከሚደገፈው ከአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን የመጡ ታጣቂዎች ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ለሁለተኛ ዙር ሕዝብ ላይ በከባድ መሰሰሪያ ጭምር  ተኩስ ሲከፍቱ የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ መንግስትና የተረጋጋ ሁኔታ ይኖራል ተብሎ እንደማይታሰብ ሁሉም መገንዘብ ያስፈልጋል። ሕዝብ ድረሱልን እያለ ነው። ዝርዝር መረጃ ይዘን እንመጣለን። ከሁሉ በፊት የሕዝብ ሕይወት ይቀድማልና መከላከያ የሚመለከታችሁ የክልልና የፌድራል ባለሥልጣናት በአስቸኳይ ይህን ጥፋት አስቁሙ።
Filed in: Amharic