ከሸኔ ጀርባ…!!!
አርአያ ተስፋማርያም
*…” ለህወሀት አንድ ሚሊዮን ነው የሰጠሁት” ሲል የዋሸው ዘርኡ ነገር ግን ከታች በተያያዘው ማስረጃ እንደሚታየው ለጁንታው የሰጠው 15 ሚሊዮን ብር ነው።
*….በወላይታ የተነሳ ጥያቄን ተከትሎ ብጥብጥ ሲፈጠር ይህ ግለሰብ 5 ሚሊዮን ብር ሰጥቷል። ህወሀት “ምርጫ አደርጋለሁ” ሲል ለተለጣፊዎቹና ስብሃት ” ጠፍጥፈን ሰራናቸው” ላላቸው ባይቶናና አራት ፓርቲ ተብዬዎች 5 ሚሊዮን ሰጥቷል…!
ከአመት በፊት መቀሌ “ፕላኔት” ሆቴል ስብሃትና ጌታቸው የሚመሩት ቡድን ከሸኔ ጋ ሚስጥራዊ ምክክር ያደርጉ እንደነበርና የድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ “እቅድ” እንደወጣ ዶ/ር አረጋዊ በርሄ አጋልጠው ነበር። “እኛ በስልጣን ከሌለን ኢትዮጵያ ትበታተናለች” ይሉ የነበሩ የህዝብ ደመኛ ጠላቶች ዛሬም ከዚህ መሰሪ ድርጊታቸው አልተቆጠቡም። ወደ መቃብር ከተሸኘው ጁንታው ጋ ግንኙነት ያላቸው ግለሰቦች (ሚሊየነር ያደረጓቸው) እና በሱዳንና ዱባይ የሚገኙ የህወሀት አመራር ተብዬዎች ሸኔን በመደገፍና በማሰማራት በወለጋ፣ በወሎና ሰሜን ሸዋ አካባቢዎች ጥቃት እየከፈቱ ንፁሃን ሰላማዊ ዜጎችን ህፃናት ሳይቀር እየገደሉ ይገኛሉ። የጁንታውን የጥፋት እቅድ እያስፈፀሙ ከሚገኙት አንዱ ዘርኡ ገ/ሊባኖስ ይጠቀሳል። በየኔታ ቲዩብ በስልክ ቃለምልልስ ስናደርግለት “ለህወሀት አንድ ሚሊዮን ነው የሰጠሁት” ሲል የዋሸው ዘርኡ ነገር ግን ከታች በተያያዘው ማስረጃ እንደሚታየው ለጁንታው የሰጠው 15 ሚሊዮን ብር ነው። ይህም ኢትዮጵያን ለማተራመስ የሰጠውና አላግባብ ከህዝብ የተዘረፈ ገንዘብ መሆኑ ልብ ይሏል! በወላይታ የተነሳ ጥያቄን ተከትሎ ብጥብጥ ሲፈጠር ይህ ግለሰብ 5 ሚሊዮን ብር ሰጥቷል። ያለፈው አመት ህወሀት የተባለ ቡድን ከህገመንግስቱ ውጭ “ምርጫ አደርጋለሁ” ሲል ለተለጣፊዎቹና ስብ
ሃት ጠፍጥፈን የሰራናቸው ላላቸው ባይቶናና አራት ፓርቲ ተብዬዋች 5 ሚሊዮን ሰጠ። አጣዬ ላይ ኢንቨስትመንት አለኝ የሚለው ይህ ግለሰብ ለሸኔዎች ድጋፍ እንዳደረገ ሲነገር፣ ከሶስት ቀን በፊት አዲስ አበባ ከሚገኝ ቤቱ ሶስት አይሱዙ ምንነቱ ያልታወቀ ነገር ጭነውና በሸራ ተሸፍነው በሌሊት መውጣታቸውን አንድ ታዋቂ ፖለቲከኛ የገለፁ ሲሆን ድርጊቱ ከተከናወነ በኋላ በማግስቱ መረጃው እንደደረሳቸው ጠቁመዋል። ቴንዶ ብረት እየተባለ የትግራይ ኮማንድ ፖስት ያስቀመጠውን አዋጅ በመተላለፍ ከመቀሌ የጦር መሳሪያ እየተጋዘ ለጁንታው ይደርስ እንደነበረና ከዛም አልፎ ቆቦ ድረስ እየመጣ ማንነታቸው ለማይታወቅ አካላት እንደሚሰጥ ማስረጃ አስደግፈን በየኔታ አጋልጠናል። የሚመለከተው አካል በዚህ አደገኛ ግለሰብ ዙሪያ የጀመረው ምርመራና ክትትል ምን እንደደረሰ አይታወቅም።
(በፎቶው ዘርኡ ገ/ሊባኖስ፣ ለጁንታው መሪ 15 ሚሊዮን አገር ለማፍረስና ለብጥብጥ ሲሰጥ)