>

እንደ አቢይ ሸኔ ያልተደራጀ ህዝብ በዘንዶ ይበላል፣ ይዋጣል፣ ይሰለቀጣልም...!!! (ዘመድኩን በቀለ)

እንደ አቢይ ሸኔ ያልተደራጀ ህዝብ በዘንዶ ይበላል፣ ይዋጣል፣ ይሰለቀጣልም…!!!

ዘመድኩን በቀለ

ደሴ በተቃውሞ ስልፍ እየተናጠች ነው። ከመናፈሻ እስከ ፒያሳ ያለው መንገድ ጠጠር መጣያ እንኳን የለውም።
 
-የአማራ መሞት ሊቆም ይገባል!
-የአማራ ልዩ ሐይል ግፍ አይፈፀምበት!
-የደሴ ህዝብ እሬሳ መቀበል ይበቃዋል!
-አስታጥቁን አታስጨርሱን!
-እስኪጨርሱን አንጠብቅም !
-የአማራ ውርደት ሊቆም ይገባል!
-አብይ ሌባ፣ አስገዳይ፣ ገዳይ  ነው።…..የሚሉ ድምጾች ጦሳ ተራራ ስር እያስተጋባ ነው።
… ደሴ ከመዋጧ፣ ከመሰልቀጧ በፊት እግሯ ሥር የደረሰውን ዘንዶ ለመከላከል ስትል በዚህ መልኩ መሰባሰብ ጀምራለች። የሚናቅ ባይሆንም የሚደነቅ ግን አይደለም። በዘመነ ወያኔ ጎንደር፣ ጎጃም እሪሪ ሲል ለሽሽ ብላ የነበረችው ደሴ ዛሬ ዘንዶው እግሯ ስር ሲደርስ በድንጋጤ መንፈራገጥ ጀምራለች። ወልድያ ላይ ያ ሁሉ መዓት ሲወርድ እሷ ቢዝነሷ ላይ ነበረች። ዘንዶው አሁን በጎጃም አድርጎ፣ በሸዋ በኩል ከሚሴ ሲደርስ የእውር ደንብሯን ዛሬ ብትት ብላለች። ድርጅት የሌለው፣ መሪ የሌለው ስብስብ ምንም ዋጋ የለውም። ውጤትም የለውም። እንዲህ አይነቱን ከባድ አደጋ የ2ሰዓት ሰልፍና መፈክር  አይመልሰውም። መጀመሪያ ይሄን እመን።
… የሰዓታት ሰልፍ እና ጩኸት ገዳይ አቢይ ሸኔን ከመግደል አይመልሰውም። አያስደነግጠውም። አያስፈራውም። በ1997 አዲስ አበባ ሲቃወም፣ ሲገደል፣ ክፍለሃገሩ ቆሞ ያይ ይታዘብም ነበረ። አሁንም እንደዚያው ነው እየሆነ ያለው። አሁን ዐማራ መያዝ ካለበት መከተል ካለበትም የኩርዶችን መንገድ አይደለም። የኩርዶችን መንገድ መያዝ ለዐማራ አያዋጣውም ባይ ነኝ። ለዐማራ የሚያዋጣው፣ የምመክረውም የእስራአፀልን መንገድ ይከተል ዘንድ ነው። “በሆዳቸው የሚያስቡትን የቀነጨሩ ወደጎብ ባንዳ ዐማሮችን” መስማት ትቶ የእስራኤልን መንገድ ብቻ መከተሉ ነው ዘሩን ከመጥፋት የሚታደገው።
… ዐማራ ሆይ ባትሰማኝም ልንገርህ። ብትሰድበኝም ልምከርህ። በሰሜን በኩል ከአጣዬ፣ ከከሚሴ፣ ከጀውሃ፣ ከካራቆሬ፣ አጽድተውሃል። ከሸዋ የቀረው መንዝና ደብረ ብርሃን ነው። ኮምቦልቻ፣ ደሴ፣ ወልድያ እና ቆቦ ተረኞች ናቸው። እሱንም አሁን በቅርቡ ይመጡልሃል። በኮማንድ ፖስት ስም በትግራይ የመከላከያ ሰራዊቱን ከህወሓት ጋር መክሮ ያሳረደው ጄነራል ጌታቾ ጉዲና ተመድቧል ተብሏል እሱ ዋጋህን ይሰጥሃል። ጠብቅ።
… ከወለጋ ከምዕራቡ የኢትዮጵያ ክፍል ሙልጭ አድርገው አጽድተውሃል። የቀራቸው ምሥራቁ ክፍል ነው እሱንም ጀምረውታል። አይንህ እያየ ለዘር ሳያስቀሩ ውድም ያደርጉሃል።
… ከመተከልም አይንህ እያየ፣ ጆሮህ እየሰማ ሙልጭ አድርገው አጽድተውሃል። የቀራቸው ጎጃም ነው። እሱንም በቅርቡ ያሳዩሃል።
… በሰሜን በጎንደር በኩል በሱዳን አማካኝነት እያጸዱህ ነው። በቅማንት ስም እርስ በእርስህ ሊያናክሱህ ሊያጸዱህ እየወገሩህ ነው። የቀረው አዲስ አበባ ነው እሱም የጊዜ ጉዳይ ነው። ጠብቅ።
… ወዳጄ እንደ አቢይ ሸኔ ያልተደራጀ ህዝብ በዘንዶ ይበላል፣ ይዋጣል፣ ይሰለቀጣልም። ከተነሣህ ታሸንፋለህ። ትረዝማለህም። ከተቀመጥክ ትበላለህ። ታጥራለህም። ስለዚህ መፍትሄው ሰልፍ አይደለም። መፍትሄው ልክ እንደ እስራኤል አልሞትም፣ እምቢ ዘሬ ከምድር ላይ አይጠፋም ብለህ እሷ የተከተለችውን መንገድ በቁርጠኝነት ሳትልመጠመጥ መከተል ብቻ ነው።
… እግርህን የወጋህን እሾክ ጉንጭህን ስለዳበስኩልህ ህመሙ አይቆምልህም። ጥዝጣዜው አይቀርልህም። መፍትሄው የተሰካብህን እሾህ መልሰህ መንቀል ነው። የደሴው ሰልፍ ለወገን አጋርነቱን ማሳያ ቢሆን እንጂ፣ የወደመውን የዐማራ ንብረት መልሶ አይተካም። የሞቱትን፣ በአቢይ ሸኔና በመከላከያ ሠራዊቱ ጣምራ ትብብር የታረዱትን ዐማሮች ነፍስ አይመልስም። ሰልፉ ልክ የወዳጅ ልቅሶ በስልክ እንደመድረስ ያለ ነው። ቀድሞ ያልነቃና ያልተደራጀ ህዝብ እንዲህ አይኑ እያየ ይበላል። ራስን መከላከል ዓለምአቀፍ ሕግ ነው። በየትኛውም ሃገር ቅቡል ነው። ሰልፍ መፍትሄ አይደለም። አንተ ሜዳ የመጣውን ጨዋታ እንዴት አድርገህ ተከላክለህ በራሱ በአጥቂው ቡድን ሜዳ ላይ መልሰህ ትተገብረዋለህ ነው ጥያቄው።

ደብረ ማርቆስ …
 የበላይ ዘለቀ ልጆችም ለተቃውሞ አደባባይ ወጡ  “ሞታችሁ ሞታችን ነው!’ ብለዋል!!!
 
የበላይ ዘለቀ ልጆች በደብረ ማርቆስ ከተማ፣ በንጉሥ ተክለሃይማኖት አደባባይ ያሰሙት ተቃውሞ የትግል ማስጀመሪያ ችቦ እንደ መለኮስ ተደርጎ ይወሰዳል። በታሪክ መዝገብም “ተቃውሞው የጀመረው በ2013 ዓ.ም. ሚያዝያ 10 ቀን አዲስ አበባ በሚማሩ የአማራ ተማሪዎችና የደብረ ማርቆስ ወጣቶች ነው” ተብሎ ሲዘከር ይኖራል!
 ከፍኖተ ሰላሞች ቀጥሎ ለሸዋ  ዐማራ ሞታችሁ ሞታችን ነው፣ ስደታችሁም ስደታችን፣  በአረመኔው የዐቢይ አሕመድ ወራሪ ቡድን እና በመከላከያ ሠራዊቱ በደረሰባችሁ ጭፍጨፋ እጅጉን አዝነናል በማለት አደባባይ በመውጣት አጋርነታቸውን በዚህ መልክ አሳይተዋል።
… ከዘመነ ግራኝ አሕመድ ቀጥሎ ዐማራ በዚህ ዘመን በአብይ አሕመድ የደረሰበት እልቂት ይበልጣል። ይከፋልም። ግራኝ የታወቀ ባላንጣ ነበር፣ ትዋጋዋለህ፣ ያሸንፍህሃል ታሸንፈዋለህ። ይሄኛው ግን ሲበዛ ክፉ፣ ሲበዛ መሰሪ፣ በደም የሰከረ፣ አፈ ቅቤ ሆደ ጩቤ፣ ለዐማራ ሞት ግድ የማይለው፣ ኦርቶዶክስ የሆነ ትግሬ፣ ጉራጌ ኦሮሞ የማይምር ሲበዛ ጨካኝ ነው።
… የዚህ ክፋቱ ዐማራውን መሪ አሳጥቶ በነፃነት በይፋ ያለከልካይ ማረዱ፣ ማሰቃየቱ ነው። ዐማራን ባረደ፣ ባወደመ ቁጥር አጀንዳ እየፈጠረ በልቅሶአቸው ላይ ዳንኪራ ይመታል። ፍርድ ከእግዚአብሔር ነው። ሳዳም ሁሴን፣ ሙሐመድ ጋዳፊ… ምስክር ናቸው።
… በታሪክ መቼም ይሁን መቼም “የሚሸነፍ መንግሥት እንጂ…የሚሸነፍ ህዝብ የለም።
ይኸው ነው።
Filed in: Amharic