>

"ልጆቼ ሁሌም ስለ እናንተ እንዳለቀስኩ ነው፤  ጌታ ሆይ ፍረድ!! በቁሜ የልጆቼን ሰቆቃ ከምታሳየኝ ሞቴን አቅርብልኝ...!" (ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ) 

“ልጆቼ ሁሌም ስለ እናንተ እንዳለቀስኩ ነው፤  ጌታ ሆይ ፍረድ!! በቁሜ የልጆቼን ሰቆቃ ከምታሳየኝ ሞቴን አቅርብልኝ…!”

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ  ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት/

 

” ልጆቼ እኔ የሃይማኖት አባት ነኝ። እኔ የእናንተ ጠባቂ ነኝ። ይሁንና ከመታረድ ልታደጋችሁ አልቻልኩም። ከሞት ላድናችሁ አልቻልኩም። እኔ የጦር መሪ አይደለሁም። ገዳዮቻችሁን ለፍርድ ለማቅረብ አቅሙ የለኝም። በእጄ ሽጉጥ ሳይሆን መስቀል ነው የምይዘው። “
” … ልጄቼ እንባዬን እያፈሰስኩ ስለ እናንተ ስቃይ አምላካችንን በፀሎቴ እየጠየኩት ነው። መንግስትንም ዘወትር እየተማጸንኩኝ ነው። ዛሬ ሆድ ብሶኛል፣ አልቅስ አልቅስ ልክ እንደ ህፃን ይለኛል፣ ልቤ በሐዘን ተኮማትሯል፣ እንቅልፍ በአይኔ ጠፍቶ እንባ ብቻ ሆኗል። ከዛሬ ነገ ይሻላል እያልን መንግስትንም እንዲያስቆም ብንጠይቅ ምንም ያየነው ለውጥ የለም። ይልቅስ ልጆቼን አስጨረስኩ። ሰላም ሰላም እያልኩ እናንተን ሳስተምር ሰላምን ማያውቁ ሰላም ነሷችሁ። ልጆቼ አትቀየሙኝ … “
” … ዝም ያልኳችሁ እንዳይመስላችሁ። ሁሌም ስለ እናንተ እንዳለቀስኩ ነው። ጌታ ሆይ ፍረድ!! በቁሜ የልጆቼን ሰቆቃ ከምታሳየኝ ሞቴን አቅርብልኝ። ልጆቼ ላይ የሚፈጸመውን ልከላከልላቸው አልቻልኩም፣ አንተው ተመልክተህ ፍርድ ስጥ!”
 
/ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ  ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት/
Filed in: Amharic