>
5:13 pm - Thursday April 18, 5118

የኦሮሞ ጽንፈኞች የአማራን ሞት "ፍትህ" አድርጎ   የሚመለከት ትውልድ  ፈጥረዋል ...!!! (ሙሉአለም ገ/መድህን)

የኦሮሞ ጽንፈኞች የአማራን ሞት “ፍትህ” አድርጎ   የሚመለከት ትውልድ  ፈጥረዋል …!!!

ሙሉአለም ገ/መድህን
*…የኦሮሞ ጽንፈኛ ኃይሎች በአማራ ላይ የከፈቱት ጥቃት ይቆማል? በፍጹም! ችግሩ ሐሳዊ ትርክት አዘል መዋቅራዊ ነው!!!

 

አብነቶችን እንመልከት፦ 
 
1. በክልሉ ሕገ-መንግሥት “ኦሮሚያ” የኦሮሞዎች  ብቻ መሆኑ ተደንግጓል። በዚያ ክልል የሚኖሩ “ሌሎች”  የማንነት ቡድኖች “መጤ” እንጅ ባለቤቶች አይደሉም።   ጽንፈኛው ኃይል ሲገልፆቸው Ormi/ባዕድ ይላቸዋል።   ባዕድ/መጤ ቢጠቃ ምንተዳቸው ነው!
 
2. የአኖሌ ሀውልት ቋሚ የጥላቻ ምልክት ሁኗል።     ተራ ሃውልት አይደለም፤ ሀውልቱ የሀሰት      ትርክት ያዋለደው ነውና የአማራን ሞት “ፍትህ” አድርጎ   የሚመለከት ትውልድ ለመቅረጽ ጥቅም ላይ እየዋለ ያለ የፖለቲካ ፕሮጀክት ነው። ለዚህ ነው     ፖለቲካቸው በቀል ተኮር የሆነው።
 
3. በሥርዓተ ትምህርት ደረጃ አማራው የኦሮሞ      ጠላት ተደርጎ ሲሰራበት ኑሯል። ይህን ውርስ በአማራ “ክልል” ከሚሴ ላይ ለማጋባት ልዩ ዞኑ እስከ 2006/7 ድረስ የኦሮሞ ክልልን ሥርዓተ ትምህርት ይከተል ነበር።      ሌሎች ከአንደኛ እና ከሦስተኛ ክፍል ሲጀምሩ ኦሮሞ   ክልል ላይ የአማርኛ ቋንቋ ከ5ኛ ክፍል እንዲጀምር የተደረገው በምክንያት ነው። ቋንቋ ለነሱ መግባቢያ   ሳይሆን ፖለቲካ ነው። ትውልዱን ነጥሎ ለማሳደግ   የሚጠቀሙበት በፖለቲካ መሳሪያቸው ነው። ይህን ሂደት አኖሌን ከመሰሉ የጥላቻ ሀውልቶች ጋር ስትደምረው  ቀላል ቁጥር በማይሰጠው የኦሮሞ ልሂቅና  ወጣት ላይ የአማራ ጥላቻ ሰርፆል።
 
4. አሁን ሥልጣን ላይ ያለው ኃይል በአማራ    ጥላቻ ተኮትኩቶ ያደገ የበቀልና ጥላቻ አውራሹ        የሥርዓተ-ትምህርቱ ፍሬ ነው። ሽሜንና ሸኔን ለመለየት የሚያስችል የግብር ልዩነት ያጣነው ለዚህ ነው።
 
5. የኦሮሞ ብልፅግና አማራን በሌሎቹ በድምፅ     እያስመታ የበላይ ሁኖ መዝለቅን ይፈልጋል።     ጥቃቱ ሁለገብ ነው አካላዊ፣ ፖለቲካዊና      ኢኮኖሚያዊ ጭምር ነው። አልተሳካም እንጅ አማራው አጋር አልባ እንዲቀር ታክቲካል የመነጠል ስራዎች በሰፊው እየተሞከሩ ነው። ኮማንድ ፖስት     የሚቋቋምባቸውን ቦታዎች የሰው ኃይል 
   ስምሪት ልብ ላለ ይኼ ገባዋል። ለዚህ ተልዕኮ    ሲቪሉም ሆነ የተወሰኑ ወታደራዊ አመራሮች    ተሰላፊ ናቸው። ካለፉት ስድስት ወራት ወዲህ     ጀ/ል ብርሃኑ ጁላ ተገኘባቸው መድረኮች    (የX,Y ብሔር ባለሃብቶች ውይይት) ጥያቄ    የሚያስነሱ ናቸው። ይህ አዲስ አበባን    የመዋጥ መሸጋገሪያ ድልድይ መሆኑ ነው።    በነገሬ ላይ ጀኔራሉ ሰፊ የሆነ የፖለቲካ    ኢንተረስት አለው። OSA ፍቅሩ ነው። ይህ ስለአማራ ብቻ  ሳይሆን ስለኢትዮጵያም ያስፈራል።
 
6. የኦሮሙማ ማሸነፍ በአማራ ታሪክ ሽንፈት ላይ     የተመሰረተ ነው። በልሂቃኑ ብዙ የተጻፈላቸው     አምስቱም የኦሮሞ ጥያቄዎችን ለማስመለስ      የአማራ መሰበር የግድ ነው። በፍሬ ነገሯ ሰሜናዊ     “ሐበሻዊት” ነች የሚሏት ኢትዮጵያ ኦሮማይዝድ     መሆን የምትችለው በአማራው መቃብር ላይ     ነው-ለነሱ። 
 
7. አሁን ያለው አብዛኛው (2/3) የኦሮሞ      ብልፅግና አመራር በእኩልነት የመቆም ፍርሃት    ያለበት፣ ከተጠያቂነት ለማምለጥ ፍላጎቱን    በኢ-መደበኛ ታጣቂ ማስፈጸም የሚፈልግ፣   በአማራ መቃብር ወንበሩን የማጽናት “ህልም”   ያለው አደገኛ ቡድን ነው። ሴራን ለመካን    እየሞከረ ያለውም የዚህ ፍላጎቱ ማስፈጸሚያ   ለማድረግ ነው።
 
የኦነግን መንፈስ የወረሰው ይህ አደገኛ ኃይል፣ ኦነግ “ሰሜን ኦሮሚያ” ነው በሚል የተስፋፊነት ቅዥቱ ካርታ ውስጥ ያስገባውን ወሎን በመጠቅለል  territorial irredentist ዓላማቸውን ለማስፈጸም ከሚሴን የመስፈንጠሪያ ሜዳ አድርገውታል። እናም by means of non-state actors continuance attack, and at some degree by military campaigns ዓላማቸውን ማስፈጸም ተያይዘውታል። ስሌቱ “ሰሜን ኦሮሚያ” ወሎን ከጠቀለልን ሸዋን እንውጠዋለን። ሸዋን ማስጨነቅ አንድም መሻገሪያ ነው ሌላም አዲስ አበባን ለማንበርከክ ሞዴል ነው። አባይ ማዶ Under the Shadow of Tigray War will be busy and the scheme will get…there. Metekel is also…then, after ‘EVERY THING’ Amhara will crash across the country. This is Orommuma’s Road Map for ‘Oromia Republic’. ለዚህ ማስፈጸሚያ Plan A, B, C ተብሎ እየተሰራበት ነው። በሁሉም አማራጭ ዕቅዶች ግን አማራን ማጥቃት መዳረሻ ግቡ ነው። ወላ Plan C የኩሽ መንግሥት ላይም ቢሆን!! 
 
መፍትኄ አለ? 
 
ሞልቶ። ባይሆን ለእንዲህ ያለ ጉዳይ ስትራቴጅያዊ መፍትኄ አደባባይ ላይ አይጻፍም። የአማራ ልሂቅ ዛሬ ነገ ሳትል የዐማራ ስትራቴጅያዊ ጉዳዮች ማዕከል መስርትና ከዋሻው ጫፍ ብርሃን የሚታይበትን መውጫ አፈላልግ። በያገባኛል ስሜት በርህን ዘግተህ ምከር፤ አጋር ወዳጆችህን መለየት ብቻ ሳይሆን የተነሳብህ ኃይል ስስ ተረከዙንም ደጋግመህ ፈትሽ። በኢትዮጵያ ህልውና አጣብቂኝ ስር ከመውደቅ ይልቅ ሌሎች አማራጮችም ሊፈተሹ ይገባል። ያኔ ነው የመደራደር አቅም የሚያድገው። ሌላው መዘንጋት የሌለበት ነገር የፖለቲካና የዲፕሎማሲ አማራጮች መቼም ቢሆን በራቸው የተዘጋ ሊሆን አይገባም። ቁምነገሩ ቁልፍ አጀንዳዎችን መለየት መቻሉ ላይ ነው። ከቀዝቃዛው የዐለም ጦርነት ወዲህ የዐለም ፖለቲካ ጠባይ መልኩ ሌላ ነው። ሀገራት ይሁኑ የፖለቲካ ቡድኖች ለመውደቅና ለመነሳት የውጭ ጉዳይ ግንኙነቶች ቁልፍ ሚና አላቸው። ኃይል ማሰባሰብ በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ብቻ ሳይሆን ከአትላንቲክ ወዲያ ማዶም የግድ ነው። 
 
በተረፈ ትንሹ መለኪያ አማራዊ አንድነትን ማጽናትና ትርጉም ላለው መስዋዕትነት መዘጋጀት ነው። 
 
የአማራ ልጆች 
 
መዋቅር በመረከብ እንጅ በማፍረስ ባለማመን ለትልቁ ሕዝብ የሚገባውን ውለታ መመለስ የትግሉ አዕማድ ሊሆን ይገባል። በእስካሁኑ የተገኙ ድሎችን (ራያና ወልቃይት) ማስጠበቅና ለሌላ ታሪካዊ ድል መዘጋጀት እንጅ ኃይል የሚበትን የትግል ስልት ውስጥ መግባት ለጠላት መታነቂያ ገመድን የማቀበል ያህል ሕዝባዊ  አደጋ አለው። 
 
የአማራ ብልጽግና አመራሮች 
 
መወሰን ካልቻላችሁ ሕዝብ በናንተ ላይ ይወስንባችኋል። ፖለቲካ በአንድ ገጹ የቅራኔዎችን ዕድገት ከጊዜ ጋር የማስታረቅ ጥበብ ጭምር ነው። ‘የጦርነት ጊዜ መሪ’ መሆን ለጥያቄ የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም። የሁኔታዎች ፍጥነት ከሬሳ ሪፖርት ወደ ወደሙ ከተሞች ቆጠራ አሻግሯችኋል። ይህ ተራ ሽብር አይደለም፤ ማንም ይሳተፍበት ‘ግራንድ የፖለቲካ ፕሮጀክት’ ነው። 
 
ግልጽ ነው ሀገሪቱን የሚፈትኑ፣ እጃቸው የረዘመ የውጭ ጠላቶች አሉ፤ ግን ደግሞ “የኦሮሙማ ማሸነፍ በአማራ ታሪክ ሽንፈት ላይ የተመሰረተ ነው” ብሎ የሚያምነው አደገኛ ኃይል ከጎናችሁ ሆኖ Territorial Irredentist ዓላማውን እያስፈጸመ ነው! ይህ እንኳንስ ሪፖርት ሁኔታዎችን ለሚያነብ ግልጽ ነው።
 
አሁን ሁኔታው ለጊዜው ሊቀዘቅዝ ቢችል እንኳ ነገ ሌላ ሴራ መጎንጎኑ አይቀርም። በፓርላማ ደረጃ በኤጀንቶቻቸው ክስ ያቀረቡበት ልዩ ኃይላችን ብዙ ወጥመድ ይጠብቀዋል። መከላከያ ውስጥ ያሉትን የአማራ ጀኔራሎች ሁኔታው ሲረጋጋለት በመፈንቅለ መንግሥት ስም ወይም በትግራይ “ሰብዓዊ መብት ጥሰት” ግምገማ ሽፋን ሊጠርጓቸው ይችላሉ። በዚህ ሂደት ልዩ ኃይሉን የመበተን ዕድል አገኙ ማለትም አይደል🙊?
 
በሌላ አቅጣጫ የኢምፔሪያሊስቱ ኃይል ጫና በርትቶ በትግራይ የተነሳ ዐለማቀፍ ማዕቀብ ቢመጣ፣ በእናንተ [አማራ ክልል አመራሮች] እና ቁልፍ የጸጥታ አካላት መሪዎች ላይ ማዕቀብ ለማስጣል ውስጥ ለውስጥ ከመስራት ወደኋላ የማይል አደገኛ ቡድን ነው ከጎናችሁ ያለው። 
 
ነገሩን ሳሳጥረው፦ ብልጽግና ፓርቲ ሲመሰረት አዴፓን አምነው የገቡ ቢያንስ አምስት ድርጅቶች አሉ። ዛሬ ነገሮች ገብተዋቸዋል። በአማራ ተጀምሮ በአማራ የሚያበቃ ጥቃት እንደሌለ ያውቃሉና የሚጠብቁት የእናንተን ውሳኔ ነው። ማፍረስ መፍትኄ ካልሆነ ስጋት የሆነው የኦሮሞ ብልጽግና ማሰናበት አንድ እርምጃ ነው። መዋቅር ጉልበት የሆነውን ኃይል አባብለህ አታስታግሰውም! መወሰን ይጠይቃል። እደግመዋለሁ ‘መወሰን ካልቻላችሁ ሕዝብ በናንተ ላይ ይወስንባችኋል’ !  
 
____/____
[ይህ ምስል ተወርዋሪው የኦሮሞ ጃንጃዊድ ሚሊሻ ነው። አጣየ፣ አንፆኪያ፣ ማጀቴ፣ አላላ፣ ሸዋ ሮቢት፣…በዚህ ኃይል ነው የወደሙት። ሁኔታዎች በዚህ ከቀጠሉ ምስሉ አካባቢው በመጭው ዘመን የአሸባሪዎች መፈልፈያ እንደሚሆን የሚናገረው እውነት አለ። መቼም ቁማርተኞቹ ‹ኦሮሚያ ሪፐብሊክ› ለሚሉት ቧልት፣ የመርከቧ ሳሎን ሰጥሞ ‹የካፒቴኑ ሩም› ሲንሳፈፍ የታየበት ማዕበል እንደሌለ ዓለም የሚያውቀው እውነት ነው፤ እነሱ ባይቀበሉትም ቅሉ። እኛ ግን እናውቃለን ብቻቸውን አንድ ቀን ውለው ማደር እንደማይችሉ!]
Filed in: Amharic