>
5:21 pm - Friday July 21, 6248

አይ የብልጽግና ወንጌላውያን ነገር....iii (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

አይ የብልጽግና ወንጌላውያን ነገር….iii

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

*… የኢትዮጵያ  ጥንታዊ   ታሪክ   በአዲሱ  የፓለቲካ ሴራ ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ ወደ   መደመርና  ብልጽግና ወንጌል
መናፍቃንን ለየት የሚያደርጋቸው ነገር ጭንቅላታቸው የእግዚአብሔርን ቃል ሐሳብ፣ መልእክትና ምሥጢር መረዳት የማይችል በመሆናቸውና ጥቅስን ያለቦታው በመጥቀሳቸው ነው!!!
በዚህ ሶፊያ ሽባባው በጠቀሰችው ጥቅስ ቅዱስ ጳውሎስ የሚናገረው በእምነት ለሚመስሉንና ሕግና ሥርዓትን ጠብቀው ለሚያስተዳድሩ ባለሥልጣናት ነው እንጅ “ተገዙላቸው አክብሯቸው!” ያለው ሃይማኖታችንን ማጥፋት ለሚፈልጉ፣ የሕግ የበላይነትንና ተጠያቂነትን ለማያውቁ ለአረማውያን፣ ለአላውያን፣ ለአሕዛብና ለመናፍቃን ባለሥልጣናት ወይም መንግሥታት ፈጽሞ አይደለም!!!
ለአረማውያን፣ ለአላውያን፣ ለአሕዛብና ለመናፍቃን ባለሥልጣናት ወይም መንግሥታትም ቢሆንማ ኖሮ ለምን ታዲያ እራሱን ይሄንን ያለውን ቅዱስ ጳውሎስን ጨምሮ ሐዋርያቱና ተከታዮቻቸው አረማውያኑ፣ አላውያኑ፣ የአሕዛብና መናፍቃን ባለሥልጣናት ወይም መንግሥታት የሚሏቸውን እያከበሩ አልተገዙላቸውም ነበር ታዲያ???
እንደሚታወቀው ሐዋርያቱና ተከታዮቻቸው በአሰቃቂ ሁኔታ እየተገደሉ በሠማዕትነት ያለቁት አረማውያኑ፣ አላውያኑ፣ የአሕዛብና የመናፍቃን ባለሥልጣናት ወይም መንግሥታት ጋር የእግዚአብሔር መንግሥት እያስተማሩ ሕጉን ለማስከበርና “ድሀ ተበደለ ፍርድ ተጓደለ!” እያሉ ለእውነት ለተበደለ በመቆም ያደርጉት በነበረ ተጋድሎ ነው!!!
ክርስቶስም ለዚህ ነበር አስቀድሞ “በሁሉም ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል፤
በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ!” ማቴ. 10፤22-23 , “በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጧችኋል ይገድሏችሁማል፥ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ!” ማቴ. 24፤9 , “አስቀድሞም ወንጌል ለአሕዛብ ሁሉ ይሰበክ ዘንድ ይገባል። ሲጎትቷችሁና አሳልፈው ሲሰጧችሁም ምን እንድትናገሩ አስቀድማችሁ አትጨነቁ፥ ዳሩ ግን በዚያች ሰዓት የሚሰጣችሁን ተናገሩ፤ የሚነግረው መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ እናንተ አይደላችሁምና።….
በሁሉም ዘንድ ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል!” ማር. 13፤10-13 ሲል አስጠንቅቋቸው የነበረው!!!
እናም ሃይማኖታችንን ለማጥፋት ለሚጥሩና የሕግ የበላይነትንና ተጠያቂነትን ለማያውቁ እንደ እነ ዐቢይ አሕመድ/ወያኔ ያሉ አላውያን፣ አረማውያን፣ መናፍቃንና አሕዛብ ባለሥልጣናትን ወይም መንግሥታትንማ የሚያዙንን እንድናደርግና እንድናከብራቸው ሳይሆን የታዘዝነው ሐዋርያው “ወዳጆች ሆይ፥ ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ!” ይሁ. 1፤3
እንዳለው ሁሉ እንድንጋደል ታዘዝን እንጅ ግራኝ አሕመድም ሲመጣና “ስለሙ!” ሲለን “ባለሥልጣናትን አክብሩ ተገዙላቸውም!” ተብለናልና ግራኝ እንዳዘዘን “እንስለም!” እንድንል፣ ፋሽስት ጣሊያንም ሲመጣ እንዲሁ “ባለሥልጣናትን አክብሩ ተገዙላቸውም ተብለናልና!” እያልን ሀገራችንን አሳልፈን ሰጥተን ቅኝ እንድንገዛ፣ ደርግ መጥቶ “ሃይማኖት የሚባል ነገር የለም ሃይማኖታችን ሶሻሊዝም (ኅብረተሰባዊነት) ነው!” ሲለን “እሽ!” ብለን ያለንን እንድናደርግ አይደለም!!!
በመሆኑም ጥራዝ ነጠቋ ሶፊያ ሽባባው ጨርሶ ባልገባት ነገር ላይ ነውና ዝምብላ እየቀባጠረች ያለችው “እባክሽን አፍሽን ዘግተሽ አርፈሽ ተቀመጭልን!” በሏት!!!
                    የኢትዮጵያ  ጥንታዊ   ታሪክ   በአዲሱ  የፓለቲካ ሴራ ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ ወደ   መደመርና  ብልጽግና 
አብይ አሀመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ጀምሮ መደመር እና ብልጽግና የተባሉ ሁለት ቃላት በጣም ገነው ወጥተዋል። የነዚሀን ሁለት ቃላት ምንጭ ማጥናት ወይንም የቀድሞው የስለላ ድርጅት ባልደረባ ሁለቱን ቃላት ክየት እንዳመጡት መረዳት አሁን ያለውን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ በትንሹም ቢሆን ለመረዳት ያግዛል። ብልጽግና (prosperity) እና መደመር (synergy) ለአብዛኛው ኢትዮጵያዊ አዲስ አደንቋሪ ቃላት (buzzwords) ቢሆኑም አለም ላይ የቴሌቪዥን ጥምቀት (televangelism) ከተስፋፋበት ከ1980ወቹ ጀምሮ ከቴሌቪዥን ጠማቂወች (televangelists) አፍ የማይወጡ ቃላት ናቸው።  አብዛኛወቹ ዝነኛ የቴሌቪዥን ጠማቂውች የብልጽግና ወንጌል በሚባል አስተምህሮ የሚያምኑ ፕሮቴስታንቶች ናቸው።
የብልጽና ወንጌል ምንድን ነው?
የብልጽና ወንጌል የሚባለው አስትምህሮ አንዳንዴ የጤናና የሃብት ወንጌል፤ አንድንዴ ደግሞ የመሳካት ወንጌል በመባል ይታወቃል። አስትምህሮው በአጭሩ የካቶሊክ፣ የኦርቶዶክስ እና ነባር የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖቸ ከሚያምኑብት የማቲውስ ዎንጌል 19፡24 “ባለጸጎች መንግስት ሰማያትን ከሚወርሱ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ብትሾልክ ይቀላል /it is easier for a camel to go through the eye of a needle than for someone who is rich to enter the kingdom of God” ክሚለው እና ክርስትናን የድሆች፣ ይተበደሉ፣ የተጨቆኑ፣ የተራቡ እና የታረዙ ሰውች ተስፋ የሆነ፣ የተስፋ እምነት ነው ክሚለው በተቃራኒው እግዚአብሄር ባለጸጋ እንድንሆን፤ ገንዘብ እንድናክማች፤ ነግደን አንድናተርፍ፤ ጥሩ አንድንበላ፤ ጥሩ አንድንለብስ ይፈልጋል። የአግዚአብሄርን መንግስት የሚወርሱት ድሆቸ፣ ሰነፎች፣ ምስኪኖች፣ ሃዘንትኞች፣ ደካሞች እና ያልተሳካላቸው ሳይሆኑ ባለጸጋወች፣ ብርቱወች፣ አነቃቂ ንግግር አዋቂወች፣ አውንታ ሃሳቢወች (positive thinkers) እና ኑሮ የሰመረላቸው ናቸው የሚል ነው።
ይህ አስተምህሮ የተጀመረበት አመት በውል ባይታወቅም ክ19ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ አሜሪካን ሃገር ውስጥ በነበሩ የፕሮቴስታንት ቤቴክርስትያኖች ውስጥ ክነበሩ የአዲስ ሃሳብ አራማጆች (New Thought Movement) ጋ የተያያዘ ነው።  አስተሳስቡ እያንዳንዱ ግለሰብ ለራሱ የኑሮ ሁኔታ፣ ጤና እና ደስታ ሃላፊነት አለበት ይሄንንም ለማድረግ የመንግስትም ሆነ የማህበረሰብ ትብብር አስፈላጊ አደለም ከሚለው የአሜሪካ ገላጭ ሃሳብ ( quintessential American idea) የተቀዳ ነው። የብልጽና ወንጌል አማኞች በአውንታ አሳቢነትና የአእምሮን ጉልበት ተገቢው ቦታ ላይ በማዋል ከሁሉም ችግሮቸ መዳን ይቻላል ብለው ያምናሉ። ለድህነት እና ሌሎች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መወቀስ ያለበት ግለሰቡ እንጂ በመዋቅራዊ እና ማሀበራዊ ፍትህ እጦት ማሳበብ ተገቢ አደለም ባይ ናቸው።
ሌላኛው የብልጽና ወንጌል መሰረት እግዚአብሄር ገንዘብም ሆነ ጤና የሚስጠው በእየሱስ ለሚያምኑና ለእየሱስ ለሚሰጡ ብቻ ነው የሚለው አስተምህሮ ነው። አስራት (tithing) ውይንም ገንዘብ ሰለመስጠት ለማስረዳት የብልጽግና ወንጌል ፓስተሮች የማርቆስን ወንጌል 10፡30ን ይጠቅሳሉ። ቅዱስ ማርቆስ 10፡30 “ስለ እኔና ስለ ወንጌል ሲል ቤቱን ና ዕርሻውን የተወ ሁሉ፣ አሁን በዚህ ዘመን መቶ ዕጥፍ የማይቀበል፣ በሚመጣውም ዓለም የዘላለም ሕይወት የማይወርስ የለም” ይላል። ኬን ኮፕላንድ የተባለ ጠቅላላ ሃብቱ 760 ሚሊዮን ዶላር ይሚገመት የብልጽግና ፓስተር አንዴ “ገንዘባችሁ ላይ መቶ ፐርሰንት ወለድ ከፈለጋችሁ ለእየሱስ ስጡት እሱ አባዝቶ ይመልሳላችኋል። እንደ እየሱስ ያለ ባንከር የትም የለም” ባማለቱ አነጋጋሪ ሁኖ ነበር።
ባለጸጋወቹ የብልጽና ወንጌል ፓስተሮች
_______________________________
ባለጸጋነትን የሚያወድስውን ከርስትና ለድሆች በመስበክ አንዲሁም አንድ ቀን የማርቆስ ወንጌል ትምቢት ይፈጸምልኛል ክሚሉ ምስኪኖች በሚሊዮን ዶላሮች በመሰብስብ የግል ቦይንግ አውሮፕላን የገዙ የብልጽግና ፓስተሮች በጣም ብዙ ናቸው። የብልጽግና ወንጌልም እነዚህን የሃይማኖት አባቶች ይሄን ይክል ገንዘብ ማከማችት እንደ ጽድቅ ሰራ እንጂ ከአንድ ክርስቲያን አባት እንደማይጠበቅ ያልተገባ ተግባር አይቆጥረውም። ለአብንት እስኪ የሚቀጥሉትን ሶስት ባለጸጋ የብልጽግና ፓስተሮች ሃብት እንመልክት:
1. ኬን ካፕላንድ/Kenneth Copeland፡ 760 ሚሊዪን ዶላር
2. ቲዲ ጄክስ/TD Jakes፡ 200 ሚሊዮን ዶላር
3. ዴቪድ ኦየዲፖ/ David Oyedepo: 150  200 ሚሊዮን ዶላር
የብልጽና ወንጌል እና የቴሌቪዥን ጥምቀት (televangelism) በኢትዮጵያ
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ መካነ እየሱስ፤ መሰረተ ክርስቶስ፣ቃለ ህይወት ና ሙሉ ወንጌል የመሳሉት ነባሮቹ የፕሮቴስታንት ቤተክርስትያኖች የተከታዮቻችው ቁጥር ና የገቢ አቅማቸው እየቀነሰ ሲሄድ ራሳቸውን ሃዋሪያ ና ነብይ ብለው የሚጠሩ የብልጽግና ወንጌል ፓስትሮች ግን የተከታዮቻቸው ቁጥር በሚሊዮኖቸ እይጨመረ ሄዷል። እንደ ዮናታን አክሊሉ፣ እዩ ጩፋ፣ እስራኤል ዳንሳ፣ ታምራት ታረቀኝ ና ብርቱካን ጣሰው የመሳስሉት የብልጽግና ፓስተሮች ትልልቅ ስብሰባወችን ና ቴሌቪዥንን በመጠቀም ለሚሊዮኖች ታምር እንሰራለን፣ ከእግዚአብሄር ጋ እናገናኛለን፣ ክህመማችሁ እንፈውሳለን፣ ብልጽግና ና ጸጋ እናስገኛለን እያሉ በነጻንት ይሰብካሉ። ግብር የማይከፈልበት በሚሊየኖች የሚቆጠር ገንዘብ ያለ ከልካይ ይሰበስባሉ። የኛ ሃገር ኬን ካፕላንድ የሆኑት እስራኤል ዳንሳና ዮናታን አክሊሉ ለባለጸጋ ፓስተርነት ስኬት የበቁት ከመሬት ተነስተው ሳይሆን ለአመታት ከነሱ የተሻለ የትምህርት ዝግጂትና ከውጭው አለም ጋር ጥብቅ ቁርኝት ባላቸው ግለሰቦችና ቡድኖች በተሰራ የረጅም ዓመታት ስራ ነው። ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ለፓስተር ዮናታን 20 ሽህ ዮሮ ጳጉሜ 1፣ 2011 ዓ/ም በሚሊኒየም አዳራሽ በተዘጋጀ “መልካም ወጣቶች” የተሰኘ ሃይማኖታዊ ፕሮግራም ላይ ሲይበረክቱ ገንዘቡን የት አመጡት? ለምን ይሄን ያክል ገንዘብ ለአንድ የሃይማኖት አባት ሰጡ ብሎ የጠየቀው ሰው ትንሽ ነው።
የብልጽግና ወንጌል ና የኢትዮጵያ ፖለቲካ
የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች በደርግ የስልጣን ዘመን ከሌሎች ሃይማኖት ተከታዮች የተለየ ወከባና እንግልት ይፈጸምባቸው እንደነበር የአደባባይ ሚስጥር ነው። በዚህም ምክንያት ህወሃት ለፕሮቴስታንቶች ቀና አመለካከት ነበረው። ህወሃት መሀል ሃገር ውስጥ ባይተዋር በነበረበት የመጀመሪያውቹ አመታት ክፕሮቴስታንቶች ውጭ የተማረ ና የከተማ ሰው አያምንም ነበር። ፕሮቴስታንቶች እንደ ትግራይ ህዝብ በደርግ ተጨቁነዋል ብናቀርባቸው ይጠቅሙናል፤ ለስልጣናችን ስጋት አደሉም የሚል አመለካክት ነበር በወቅቱ የህዋሃት ባለስልጣናት ዘንድ። በፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮችም ዘንድም ህወሃት የእምነት ነጻነት እንዲከበር በማድረጉ ለህውሃት ቀና አመለካክት ነበራቸው። ብዙ የተማሩና በተለያዩ የሙያ ዘርፍ የተሰማሩ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ኢህኣዴግን ተቀላቅለው ህውሃትን መሀል ሃገሩን አላምደዋል።
የብልጽግና ወንጌል ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በደምብ ታስቦበትና በተጠና መልኩ እንዲገባ ያደረጉት ሁለት ከአሜሪካን ሃገር የመጡ ፓስተሮች ናቸው። በፈረንጆች አቆጣጠር 2001 ዓ/ም ጀምሮ ነው ፓስተር ባደግ በቀለ ከካሊፎርንያ ግዛት፤ ፓስተር ገመችስ ደስታ ከ አተላንታ ጆርጂያ የተለያዩ ፕሮጄክቶችን በመቅረጽ የኢህአዴግን ጽ/ቤት ማንኳኳት የጀመሩት። በወቅቱ የነበሩ ባለስልጣናትም ሁለቱ ፓስተሮች ይዘዋቸው ለመጡት ፕሮጄክቶች አረንጓዴ መብራት በማብራት ረድተዋቸዋል።
ፓስተር ባደግ በቀለ በካሊፍርንያ ግዛት ለረጂም ዓመት የኖሩና ቅዱስ ኢማኑኤል የሚባል የብልጽግና ወንጌል ማስተማሪያ ቤተክርስትያን ባለቤት ሲሆኑ። የዶክትሬት ዲግሪያቸውንም የሰሩት እዛው ካሊፎርንያ ውስጥ የሚገኘው የብልጽግና ወንጌላውያን ዩንቨርሲቲ የሆነው አዙሳ ፓስፊክ (Azusa Pacific) የተባለ ተቋም ውስጥ ነው። ፓስተር ባደግ በአሁኑ ወቅት የዳሎል ኦይል፣ ስድስት ኪሎ የሚገኘው ኢንተርናሽናል ሊደርሽፕ ኢንስቲትዮት፣ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ አለም ጤና የሚገኘው የፕሮፌሰር ባደግ በቀለ አካዳሚ ባለቤት  እንዲሁም ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ በርካታ ባንኮችና ኩባያወች ባለድርሻ ናቸው።
ፓስተር ባደግ ና አዙሳ ፓስፊክ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ፕሮጄክት ይሚል ፕሮግራም ቀርጸው በወቅቱ ሁለተኛ ዲግሪ ለመያዝ ያማይቆፍሩት ድንጋይ ያልነበረውን የኢህአዴግ ባለስልጣናት በስራ አመራር የሁለተኛ ዲግሪ ለማሰልጠን ፍቃድ ያገኛሉ። ስድስት ኪሎ የኦሮሚያ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት መሬት ተስጥቷቸው ትልቅ ህንጻ ገንብተው በመቶወች የሚቆጠሩ የሃገሪቱን ከፍተኛ የሲቪል ና ወታደራዊ ባለስልጣናትን የመጀመሪያ ዲግሪ ያላችውንም የሌላችውንም በስራ አመራር ዘርፍ በማስተርስ ፕሮግራም ማሰልጠን ይጄምራሉ።  ስልጠናው የሚሰጠው ኢትዮጵያ ውስጥ ቢሆንም ዲግሪውን የሚሰጠው አሜሪካን ሃገር ውስጥ የሚገኝ ዩኒቨርሲቲ በመሆኑ የሃገሪቱ ባለስልጣናት ከ ጠ/ሚ መለስ በስተቀር ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በአንድ ወቅት ያፓስተር ባደግ ና አዙሳ ፓስፊክ ተማሪወች ሁነው ነበር። ለምሳሌ ያክል የቀድሞው ጠ/ሚ ሃ/ማ ደሳለኝ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገዱ አንዳርጋቸው፣ ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን፣ መከላከያ ሚ/ር ለማ መገርሳ፤ የብልጽና ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊው አለሙ ስሜ፤ የቀድሞው የኮምኒኬሽን ጽ/ቤት ሚ/ር ድኤታ ኤርምያስ ለገሰ፣ እንዲሁም ኢህአዴግ ሹመት ሲስጥ የትምህርት ዝግጂት በስራ አመራር ሁለትኛ ዲግሪ የሚባልላቸው ቀጥራችው በጣም በርካታ ካድሬወች የፓስተር ባደግ ት/ቤት ምሩቃን ናቸው።
ፓስተር ባደግና አሱዛ ፓስፊክ ዩኒቭርሲቲ እነዚህን ሁሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት በክርስትያን ስራ አመራር ና ሃብት ፈጠራ ዘርፍ የማስልጠን አድሉን ያገኛሉ.።  እነዚህ የፓስተር ባደግ ተማሪ ባለስልጣናት ከአቶ መለስ ህልፈት በኋላ ስልጣኑን የተቆጣጠሩት የህወሃት ሰወች ሃሳብ ለማፍለቅ ሲቸገሩ፣ የድርጅቱን ካድሬውች ሰብስበው የሚመሩበት መሪ ሃሳብ ሲጠፋ ከፍትኛ የሆነ ውዝንብር ሲመጣ፣ የፓስተር ባደግ ተማሪውች የሆኑት እነ ሃ/ማርያም፣ ደመቀ፣ አለምነው፤ አርከበ፤ አለሙ፣ ገዱ፤ ለማ፣አብይ የድርጅቱ ሃሳብ አፍላቂውች ሆኑ። አብዮታዊ ዲሞክራሲ፣ ግብርና መር ኢኮኖሚ፣ ገበሬው ነው ማህበራዊ መሰረታችን የሚሉ አይነኬ ሃሳቦች የሃገሪቱን የፖለቲካ ሙቀት ተከትሎ ኢህሃዴግ ውስጥ አከራካሪ ሃሳቦች ሆኑ።   “We have produced more than 30 mayors, Deputy Prime Ministers, 15 ministers and state ministers in Ethiopia.” ይላል የፓስተር ባደግ በባለቤትንት የሚመሩት ኢንተርናሽናል ሊደርሽፕ ኢንስቲትዮት አካዳሚ ድረ ገጽ። እንግዲህ የኢትዮጵያ ህዝብ እስክ መኖሩም የማያውቀው አንድ ሃይማኖታዊ ተቋም 1 ጠ ቅላይ ሚኒስትር፣ 2 ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ፣ 15 ሚኒስትሮችንና 30 ከንቲባወችን  ና በርካታ ጄኔራሎችን በክርስቲያን ስራ አመራር ዘርፍ አስተምሮ አስመርቋል።
ሁለተኛው የብልጽግና ወንጌል የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የበላይ ሃሳብ ሆኖ  እንዲወጣ ትልቅ ስራ የሰሩት ክአትላንታ ጆርጂያ የመጡት ፓስተር ገመቺስ ደስታ ቡባ ናቸው።  ፓስተር ገመቺስ ሊድስታር ኢንተርናሽናል ሚኒስትሪስ (Leadstar International Ministries) የተባለ በተለያዩ የብልጽግና ወንጌል ማስፋፍያ ዘርፎች ላይ የተሰማራ ተቋምን በባለቤትነት ያስተዳድራሉ። ሊድስታር ዋን ሚኒስትሪ ትሪ ፍሮንትየርስ (One Ministry Three Frontiers)  በሚል መሪ ቃል ስር የብልጽግና ወንጌል በተለየዩ ቋንቋውች የሚስበኩባችው በርካታ ቤ/ክርስትያኖችን፣ የቴሌቪዝን ና ሬድዮ  ጣቢያወችን እንዲሁም ትምህርት ቤቶች ያሉት ትልቅ ተቋም ነው። ለመጥቀስ ያክል LTV  የተባለው ታዋቂ የቴሌቪዥን ጣቢያ ና ሊድስታር ኮሌጂ በፓስተር ገመችስ ባለለቤትነት የተያዙ ናቸው።
ፓስተር ገመቺስ የአለም አቀፍ የኦሮሞ ቤተክርስትያኖች ህብረት (Worldwide Union of Oromo Churches) ፕሬዘዳንትም ናቸው። ለኦሮሞ ፖለቲካ ባላችው ቅርበት ምክንያት ክብዙ የኦህዴድ ባለስልጣናት ጋር ቅርበት ና ጓደኝነት ለመፍጠር የቻሉ ሲሆን። ከጠ/ሚ አብይ አህመድ፣  ሽመልስ አብዲሳ ጋር ስላላቸው ቅርብ  ጓደኝነት ና የፖለቲካ አማካሪነት ሚና በኤል ቲቪ (LTV) አቅራቢዋ ቤቲ ታፈሰ ፕሮግራም ላይ ቀርበው ማብራራታቸው አይዘነጋም። የኦህዴድ ከፍተኛ ባለስልጣናት ሁሉም ማለት ይቻላል ፓስተር ገመቺስ ደስታ ና የሪፍት ቫሊ ዩንቨርሲቲ ባለቤት የሆኑት አቶ ድንቁ ደያሳ የፈጠሩት የሃይማኖትና የጥቅም ትስስር (ኔትወርክ) አባላት ናቸው። ይህ የሃይማኖትና የጥቅም ትስስር ሙስሊም ኦሮሞወችን ያገለለ በመሆኑ የኦሮሞን ፖለቲካ ለሁለት እንዲሰነጠቅ በማድረጉ የኦሮሚያ ክልል ባለፉት ሁለት አመታት ውስጥ ከየትኛውም የኢትዮጵያ አካባቢ በባሰ ሰላም የራቀው አካባቢ እንዲሆን አድርጎታል።
እነዚህ ከላይ የጠቀሱት የፓስተር ባደግ ና የ ፓስተር ገመቺስ የሃይማኖትና የጥቅም ትስስሮች በጣም ጠንካራ የሆነ የውጭ የሃይማኖትና የፖለቲካ አካላት ድጋፍ ያላቸው ሲሆን በዚህ ጽሁፍ ከተጠቀሱትና በስማቸው ከተመዘገቡት ተቋማት በተጨማሪ የኢሊሊ ሆቴል ባለቤት ሁነው እንደተመዘገቡት አቶ ገምሹ በየነ አይነት ሰውች ስም የተመዘገቡ በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ የሚንቀሳቀስበት ኔትወርክ ነው።
የብልጽና ወንጌል አብዮታዊ ዲሞክራሲን አንዴት ተካው?
ለህወሃት የስልጣን ዘመን ማብቃት ምክያት ስለሆኑ ሁኔታወች የተለያዩ ሃሳቦች ቢሰነዘሩ ብዙም አይገርምም ምክንያቱም ህወሃት ከስልጣን የወረደበት አንድ ሚሊዮን የተለያዩ ምክንያቶች ስላሉ። ነገር ግን ህወሃት ኢህኣዴግ ውስጥ የነበረው የሃሳብ (የስልጣን ወይም የጉልበት ማለት አደለም) የበላይነት እየተሸረሽረ የሄደው አቶ መለስን በሞት አቶ በረከትን ደግሞ በህውሃት ሰወች ስልጣናችን ይወስድብናል ፍርሃት ካጣ በኋላ ነው። ይህ በኢህኣዴግ ውስጥ የነበረ የሃሳብ የበላይነት ማጣት መሬት ወርዶ ከተለያዩ በጣም ብዙ ውጫዊና ውስጣዊ ምክያቶች ጋር ተዳምሮ ወደ ስልጣን ማጣት ተቀይሯል።
አብዮታዊ ዴሞክራሲ ጥርት ያለ መርሆ ያለው ነገሮችን በግልጽ ለመተንትን የሚያስችል የተስናሰለና በአግባቡ የተሰነደ ርዕዮተአለም ባይሆንም መምህሩ የነበሩት አቶ መለስ ና ደቀመዝሙሮቻችው እንደ ዳዊት የሚደግሟችው የተለያዩ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሃሳቦች የያዘ ያላለቀ ነገር ግን ካድሬ ለማሰልጠን የሚይስችል ማንዋል ነበር ማለት ይቻለል። አብዮታዊ ዴሞክራሲ ማህበራዊ መስረቴ የሚለው መድብ (ገበሬው) ና ቡድኖች (ጭቁን ብሄሮች) እንደነበሩት ሁሉ ጠላት መደብና ጠላት ብሄር ማን እንደሆነ ለይቶ የሚያውቅ። ማህበራዊ መሰረቴ ለሚላቸው ቡድኖችን ጥቅም የሚያስከብር፤ ጠላቴ የሚለውን ብሄር ደግሞ ህልውና የሚያጠፋ ህገ ምንግስት፣ ፖሊሲ፣ አዋጅ፣ ደምብና መመሪያ የነበረው የፖለቲካ አስተሳሰብ ነው።
እነ አቶ መለስና አቶ በረከት ካድሬወቻቸውን በአብዮታዊ ዴሞክራሲ በሚያጠምቁበት ዘመን ለስልጣናችን አያሰጉነም እናምናቸዋለን ያሏቸው እነ ፓስተር ባደግና ፓስተር ገመቺስ ቀን አብዮታዊ ዴሞክራሲ ሲጋቱ የሚውሉትን የደኢህዴን ና የኦህዴድ ባለስልጣናትን ማታ የፕሮቴስታንት ቤተክርስትያን ውስጥ የብአዴን ካድሬወችን ደግሞ ኢንተርናሽናል ሊደርሽፕ ኢንስትዩት ውስጥ የብልጽግና ወንጌል፣ አውንታ ሃሳቢነት፣ አነቃቂ ንግግር፣ የብልጽግና ወንጌል ስራአመራር ጥበብ፣ ወዘተ ማታ ማታ ያስተምሩ ነበር።
አቶ መለስ ከሞቱ በኋላ የተለያዩ የጥቅም ኔትውርኮች እንደ አሽን ሲፈሉ የፓስተር ባደግና የፓስተር ገመቺስ የማታ ትምህርት ተማሪውችም የራሳችውን ጠንካራ ኔትውርኮች ከህውሃት ኔትውርኮች በተጓዳኝ መስርተዋል።  በስልጣንና በገንዘብ ያበዱት የህውሃት ባለስልጣናትም እርስ በርስ በሚያድርጉት የሃሳብም ሆን የስልጣን መገፋፋት ትግል ውስጥ እንደ አስፈላጊነቱ የፓስተር ባደግንና የፓስተር ገመቺስን ስውች በሃሳብ አመንጪነት ደረጃ እንዲሳተፉ አድርገዋል። ይህ ተሳትፎ ከተላላኪነት ያለፈ ሚና ላልነበራቸው ስውች የሞራል ስንቅ ሰጠ፤ የህውሃት ስውችን ኢህአዴግ ውስጥ መሞገት እንደሚቻል አሳየ። ከጊዜም በኋላም የሃገሪቱ ጉዳይ ላይ የመወሰን ይተሻለ ሚና ይገባናል ብሎ ደፈር ብል ወደ መጠየቅ እየተሽጋገረ ሂዷል።
በአማራ ክልል ና ኦሮሚያ ውስጥ ባሉት ዘርፈ ብዙ ችግሮች ምክንያት ወጣቶች በማህበራዊ ሚዲያ አንቂወች በመታገዝ አገዛዙን ሲቃወሙ ብአዴንና ኦሀዴድ ካድሬወች እሳት ከማጥፋት ይልቅ አይዟችሁ እያሉ ነዳጅ ወደ ማቀበል ተሽጋገሩ። የአብዮታዊ ዲሞክራሲ አንዱ ትርክት ኢትዮጵያ ውስጥ በቁጥር አብላጫ ያላቸው ሁለት ብሄሮች ግንኙነት የጨቋኝና የተጨቋኝ ነው እነዚህ ሁለት ቡድኖች ፍላጎቶቻቸው መቸም አይታረቁም፤ አብረው ሊስሩ አይችሉም፤ የነዚህ ሁለት ብሄሮች ፉክክር እንደ ትግራይ ላሉ ኣናሳ ብሄሮች ሲሳይ ነው የሚል ነው።  ነገርግን ህወሃት አምናቸዋለሁ ለስልጣኔ ስጋት አደሉም ብሎ ነገሮችን አልጋባልጋ ያደረገላችው ፓስተሮች ለአመታት የብልጽግና ወንጌል ቤተክርስትያን ውስጥ ና ኢንተርናሽናል ሊደርሽፕ ኢንስቲትዩት ውስጥ ያስተማሯችውን የ ኦህዴድና የብአዴን ካድሬውችን በማስተባበር የአሜሪካንና የአውሮፓ ህብረትን ቡራኬ በመቀብል  ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝን ያለ ህውሃት ፍቃድ ስልጣን እንዲለቁ በማድረግ፣ አብይ አህመድን በማንገስ፤ ህዋሃትን ከአራት ኪሎ እንዲባረር አድርገዋል።
የብልጽግና ወንጌል አቀንቃኞች ስልጣን ክመያዝ ባለፈ የብልጽና ወንጌል ለኢትዮጵያ ችግሮች መፍትሄ ነው ብለው ያምናሉ። ለዚህም የረዳ ዘንድ የብልጽግና ወንጌል መሰረታዊያን የኢትዮጵያን ዘርፈ ብዙ ችግሮች እንዴት ሊፈቱ እንደሚችሉ የሚያሳየው በጠቅላይ ሚኒስትር በአብይ አህመድ እንደተጻፈ የሚነገረው መደመር የተሰኘ አለማዊ መጽሃፍ በሚሊዮን በሚቆጠር ቅጅ ታትሞ እንዲሰራጭ ተደርጓል። ገዥው ፓርቲም ስሙን በአደባባይ ወደ ብልጽግና ፓርቲ ቀይሯል።
ሰው መናገር እንጅ መገመት በመላ፣
የነገን ማን ያውቃል ከፈጣሪ ሌላ          
ስምና      ተግባር    ይለያያልና  ፦፦
Filed in: Amharic