ብሩክ ደሳለኝ
ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ወዲህ የመጡት ምናምንቴ መሪዎች እንዲሁ እነዳበደ ውሻ ሲቅበዘበዙ አለፉ፡፡ የማያውቋትን ኢትዮጵያ እንመራለን ብለው አንዱም ፈርጥጦ በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ አገሩን አዋርዶና ለሌሎች የቀን ጅቦች አመቻችቶ ዚምባብዌ ይኖራል! ቴድሮስ መቅደላ ላይ ራሱን ሰዋ፣ ዮሃንስ መተማ ላይ ራሱን ተቀላ፣ መንግሰቱ ሃራሬ ሆዱን ሞላ! ስንቱ ጀግና በሱ ስር ተሰልፎ ህይወቱን ሰውቶ ከአገሩ አፈር ጋር ተቀላቅሎ እሱ ግን እየኖረ ነው – ኑሮ ከተባለ ፡፡
ሌላው በትግራይ ባንዶች የጠላ ቤት ዲስኩር የተኮተኮተው ባንዳ የወያኔ አለቃ አዲስ አበባን የአማራ አገር ብቻ አድርጎ በዊንጌት አጥር ኢትዮጵያን እየመነዘረና የእንግሊዛውያን አስተማሪዎቹን ቱለቱላ መርዝ ተግቶ እስከሞቱ ድረስ ሲቀባጥር ከነነፍስ አባቱ(ነበረው እንዴ?) እግዜር ጠርጎ ጣለው፡፡ የቀሩት ቅንጭር ወያኔዎች፣ ቅንጭር አማሮችና ሆዳም አሮሞዎች እንኳን ከነሱ ከጌታቸው ከመለስ ዜናዊም ሆነ ከጌቶቹ ከምዕራባውያን በላይ የሆነችውን ኢትዮጵያን እንገዛለን ብለው ይኸው መከራቸውን እየበሉ አገሪቷንም መከራ እያበሏት ነው፡፡
የማይችሏትን በመንፈሳዊም በስጋዊም እጅግ የተወሳሰበች አገር እንመራለን ብለው መከራቸውን እየበሉና እኛንም መከራችንን እያበሉን ነው፡፡ ያ ውስብስብነት የፈጠረው የአእምሮ ውስብስብነት የሌላቸው ሰዎች ልክ ሃቁን ሲረዱት ወደ ንዴት፣ ብቀላና አጥፍቶ መጥፋት ውስጥ ይገባሉ፡፡ በቅርቡ እንኳን እንደ አንበሳ አገር ይመራሉ ተብለው ጥጃ ሆነው ቄራ የተገኙት ያቺን ውስበስብ ሜንታሊቲ ማምጣት ስላልቻሉ ይኸው ራሳቸውን – ስለዚህም ፓርቲያቸውንና ሜዲያቸውን – ለሰላሳ ምናምን ሽያጭ አቅርበው፣ ባነዲራ ካላቃጠልን እያሉ ሲደነፉ በፖለቲካው ቄራ ታርደዋል፡፡ የዕውር መሪ ሆነው ሰውየውንም ወደገደል እየመሩት ነው፡፡
ያልተፈጠርክበትን ወርቅ ከየት ታመጣዋለህ? ብር ከሆንክ ብርነትህን ጠብቀህ በብርነት መኖር፣ መዳብም ከሆንክ መዳብነትህን አውቀህ በመዳብነትህ ተከብረህ መኖር፡፡ እንደ መለስ ይሄኛው ጎሳ ወርቅ ነው ያኛው ጎሳ መዳብ ነው ማለቴ አይደለም፣ ግለሰቦች በተለይም ለከፍተኛ ኃላፊነት የሚታጩት ግን ደረጃቸው ይለያያል፡፡ ከመሬት ተነስተህ ባላደግህበት ኢትዮጵያዊ ውስብስነት የፖለቲካ ፓርቲ መሪ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ስለሆንኩ፣ ስለለፈለፍኩ መሪነትን አገኘዋለሁ ካልክ መጨረሻህ እንደ መንግስቱና መለስ እየተሰቃየህ በመጨረሻም በታሪክ ቆሻሻ መጣያ መራገፍ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን ማንም አገር በመደዴ አስተሳሰብና መሪ ሊመራ አይገባም፡፡ ከሰው መርጦ ለሹመት፣ ከእንጨት መርጦ ለታቦት የተባለው ያለምክንያት አይደለም፡፡ ኢትዮጵያም የግድ ለእርሷ የሚመጥን አስተሳሰብ ትፈልጋለች፡፡ እርሷ በትንሹ የሶስት ሺህ ዘመን ሙሽራ ናት እርሷን ለማግባት የግድ ቢያንስ የሶስት ሺህ ዘመን ታሪኳን ማወቅና ኩሩ ኢትዮጵያዊ ሆኖ ማደግን ይጠይቃል! አለበለዚያ ያንተን በልኳ ያለተሰፋ ጥብቆ በጫጭቃ ትጥልልሃለች፡፡ ባለፉት ሶስት አመታትም ኢትዮጵያ ያሳየችን ይህንኑ ነው – የበሻሻ ጥቡቆ በፍጹም አልበቃትም! ከገባህ እየበጫጨቀችልህ ነው፡፡ አንተም እየበጫጨካት ነው፡፡ ግን ቢያንስ መበጫጨቅህን አቁም፡፡ በጊዜም ብጭቅጫቂህን ይዘህ ጥግህን ያዝ!
የኢትዮጵያን ሥጋዊና መንፈሳዊ ውስብስብነት የተረዱት ከየትም ይነሱ፣ ከቋራ ሆነ ከዐድዋ ወይም ከአንኮበር፣ ከኤጀርሳ ጓሮ ሆነ ከየትም መለኪያው የትም ተወለድ ኢትዮጵያዊ ሆነህ ዕደግ ነው! ይሄን ጸጋ ያልተጎናጸፉ ሰዎች ኢትዮጵያን መምራት አይችሉም፡፡ ሁለህም ልክህን እወቅ፡፡ ኢትዮጵያን ለመምራት ምዕራባውያኑ ራሳቸው የተዋረዱበትንና የዘቀጠ ህብረተሰብን ያፈሩበትን መንገድ ኢትዮጵያ ላይ መትከል አያዋጣም! ኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲ እያልክ የምትለፋደድ ሁሉ በመጀመሪያ የኢትዮጵያን ማንነት ማወቅ እንጂ የማንም መደዴ የሚሰባሰብበትን ስርዓት ዲሞክራሲያዊ እያልክ አሞካሽተህ የምትኖርባትና የምትገዛት ተራ አገር አይደለችም፡፡ ነገርንህ – የእግዚአብሔር አገር ናት! ኢትዮጵያ ነፍስ ያላት አገር ናት፡፡ ይሄ ለመደዴ ሰው ቀልድ ይመስለዋል ጥበበኛ ግን ይረዳዋል፡፡ ጥበበኛ መሪም የኢትጵያን የነፍሷን ፍላጎት ተረድቶ ለማስፈጸም ይተጋል እንጂ ኩሬ ሲቆፍር፣ ፓርኪንግ በመገንባትና በልፈፋ ጊዜውን አያጠፋም፡፡
ለማንኛውም ኢትዮጵያ ምንም አትሆንም የምንለው ከመሬት ተነሰተን አይደልም፡፡ ሩዋንዳ፣ ሊቢያ፣ ሶሪያ ዩጎዝላቪያ እያልክ የምትለቀልቅና የምትለፈልፍ ጥራዝ ነጠቅ ሁሉ ቢያንስ መጀመሪያ የሩዋንዳንና የሶሪያን ጉዳይ በጥልቀት ዕወቅ፡፡ የዓለሙ ገዢዎች የሰጡትን ልፈፋ እያራገብክ እውቀት አለኝ አትበል፡፡ ሊቢያም በነሱ ባንክ ያስቀመጠውን ዶላር ዘርፎ ነዳጁንም የነሱ ድርጅቶች እንዲቦጠቡጡት ለማድረግ ነው ጋዳፊን ያሰወገዱት፡፡ የሶሪያም ጉዳይ የጋዝ መተላለፊያ ቱቦ በመሬትህ ላይ አሳልፍልኝ አለበለዚያ እገለብጥሃለሁ ነው መነሻው፡፡ ኢራቅ ሆነ ሶርያ ወይም ሊቢያ ጸረ ኢትዮጵያ አቋም ሲያራምዱ የነበሩ መንግስታት መሆናቸውን ሳንረሳ ብቻ ሳይሆን እየተገረምን እነርሱ ላይ የደረሰው ፈረንረጆቹ እንደሚያወሩልን አለመሆኑን መረዳት ደግሞ የግድ ነው፡፡ የነረሱን ጉዳይ ግን ከኢትዮጵያ ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር የለም፡፡ የኢትዮጵያ ጉዳይ ጥንትም አሁንም አንድ ነው! ቀሪዋ በሰይጣን እጅ ሙሉ በሙሉ ያልገባች አገር መሆኗ ነው፡፡ የሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ውጊያ መንፈሳዊ ነው! ከገባን እኛ ኢትዮጵያውያን ለውጊየው የሚሆን ምሽግም መሳሪያም አለን፡፡ ለዘመናት ተዋግተን አገራችንን ያቆየንበት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነታችን፡፡ በእስልምናውም ከአሳሳች ሃሳብ ተጠብቆ ከማንም ቀድሞ ቱባ የእስላምና አገር ባለቤት ስለሆነ ቱባ እስልምናውን መጠበቅ!!!