>

“ፕሮፌሰር” ብርሃኑ ነጋን  ወደ ጠበል የሚወስድ ዘመድ ይጥፋ? (አምባቸው ዓለሙ - ከወልዲያ)

“ፕሮፌሰር” ብርሃኑ ነጋን  ወደ ጠበል የሚወስድ ዘመድ ይጥፋ?

አምባቸው ዓለሙ (ከወልዲያ)


መማር ምንድን ነው? መማር ድንቁርናን ካጎለበተ፣ መማር ኅሊናን ካሳወረ፣ መማር ሆዳምነትንና የሥልጣን ሱስን ካልገረዘ፣ መማር ራስህ ከፈጠርከው ዓለም ውጭ እንዳታይ ካስገደደ … ጥቅሙ ምንድን ነው? ሳይማሩ የጤናማ ኅሊና ባለቤት የሆኑ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ የመጨረሻውን የትምህርት ጣርያ ደርሰው ሳለ ደግሞ የድንቁርናና የፍርደ ገምድልነት የመጨረሻው ጫፍ የሚሆኑ አሉ፡፡ ከነዚህም አንዱ ብርሃኑ ነጋ ለመሆኑ ጥርጣሬ አይግባችሁ፡፡ ወደ ፖለቲካው መድረክ ከገባ በኋላ ብዙ ጊዜ የሚናገራቸውን አጉራ ዘለል የጥጋብና የዕብሪት ንግግሮቹን ለጊዜው ትተን የሰሞኑን ብቻ እንመልከት፡፡ ትዕቢትና ዕብሪት፣ ዝናና ሀብት፣ የምኞት ባርነትና የፍላጎቶች አለመሳካት ለዚህ ዓይነቱ የተመሰቃቀለ ስብዕና መዳረጉ የሚደገፍ ባይሆንም የሚጠበቅ ግን ነው፡፡ ሰውዬው በርግጥም በቁም ነፍስ ይማር በሚያሰኝ ደረጃ ላይ ይገኛል፤ በበኩሌ አሳዘነኝ፡፡ አንድ ሰው ከማኅበረሰብኣዊና ከሃይማኖታዊ የሞራልና የእምነት ማዕቀፎች ራሱን ነጻ ካደረገ ልክ እንደብርሃኑ ነጋ እንደልቡ ይሆንና እንዳበደ ውሻ የሚያገኘውን ሁሉ እየዘለፈና እያስፈራራ ከተቻለ የርሱ አሸርጋጅና አጎብዳጅ ለማድረግ ይሞክራል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ሰው “ሰው ጤፉ” ይባላል፡፡ ሰው ባይኑ አይሞላም – ራሱ ትንሽ ሆኖ ሰውን ትንሽ ያደርጋል፤ ራሱ በሽተኛ ሆኖ ሰውን ታማሚ ያደርጋል ….፡፡ በሥነ ልቦናው መስክ “ሜጋሎማኒያ” በመባል የሚታወቅ በሽታ አለ – ብርሃኑ የሚሰቃይበት በሽታ ይህኛው ይመስለኛል፡፡ የሥነ ልቦና ደዌያት ደግሞ ተደጋጋፊም ተጫፋሪም ስለሆኑ ከሞላ ጎደል ሁሉም ወይንም አብዛኛው የሥነ ልቦና በሽታ ምልክቶች በአንድ ሰው ላይ የመከሰታቸው ዕድል ከፍተኛ ነው፡፡ እናም ብርሃኑና ታናሽ ወንድሙ አቢይ ከእነዚህ በሽታዎች በአንዱ ወይም በሌላው (ምናልባትም በሁሉም) የተለከፉ ስለመሆናቸው በየጊዜው ከሚያሳዩዋቸው ወጥነት የሚጎድላቸው ማንነቶች መረዳት ይቻላል፡፡ 

የአእምሮ ብልሽት  መገለጫዎችን ዘርዝሮ መጨረስ ያስቸግራል፡፡ በጥቂቱ ለማስታወስ ያህል ግን፡-  

Pathological lying, also known as mythomania and pseudologia fantastica, is a mental disorder in which the person habitually or compulsively lies.

Psychopathy, sometimes considered synonymous with sociopathy, is traditionally personality disorder characterized by persistent antisocial behavior, impaired empathy and remorse, and bolddisinhibited, and egotistical traits.

Paranoia is an instinct or thought process which is believed to be heavily influenced by anxiety or fear, often to the point of delusion and irrationality.

Narcissistic personality disorder (NPD) or megalomania is a personality disorder characterized by a long-term pattern of exaggerated feelings of self-importance,

In psychology, an inferiority complex is an intense personal feeling of inadequacy, often resulting in the belief that one is in some way deficient, or inferior, to others

Egocentrism is the inability to differentiate between self and other. More specifically, it is the inability to accurately assume or understand any perspective other than one’s own.

Schizophrenia is a mental disorder characterized by continuous or relapsing episodes of psychosis. Major symptoms include hallucinations (typically hearing voices), delusions, and disorganized thinking

 (source: Wikipedia)

ብርሃኑ ነጋ ባጭሩ ያበደ ይመስለኛል – ዕብደት ከዚህ በላይ ማስረጃ ካላስፈለገው በስተቀር፤ እንዲህ የምለው አሁን ስለርሱ የሚናገር አንድ ዝግጅት አዳምጬ እኔም “ስላበድኩ” ነው፡፡ አንድ ሰው ካላበደ ደግሞ “ኢትዮጵያ ውስጥ የዘር ማጥፋት ወንጀል (ጄኖሳይድ) አልተካሄደም” ብሎ ለወንጀለኞች ነፃ ጥብቅና መቆም ከትዝብት በቀር አንዳችም ትርጉም የለውም፡፡ ይህ ሰው ለሥልጣን ያለው ጉጉት ለዚህ ዓይነቱ ተደጋጋሚ የአእምሮ መናጋትና ታላቅ ውርደት ሳይዳርገው አልቀረም – ደግሞም እኮ የአማራን መጨፍጨፍና መሳደድ ለመናገር በግድ አማራ መሆንን አይጠይቅም፤ ለአማራ ያለውን ጥላቻ መግለጽ ከፈለገ ደግሞ እውነትን በመሸምጠጥ ሳይሆን ሌላ መንገድ ቢፈልግ ይሻል ነበረ፡፡ ብሬ አሁን ገና በሚገባ ሞተ፤ አልሞትኩም ብሎ ቢዋሽ ታሪክ ራሱ አፍ አውጥቶ ይመሰክርበታል፡፡ ሰውዬው በሀብትም በዝናም በሙያዊ ዕውቀትም ያን ያህል የሚታማ አልነበረም፡፡ በዚያ በኩል ገፍቶ የሕይወት ጥሪውን ቢገፋ ከውርደት በዳነ፡፡ ግን መጥፎ ዐመል ሳያስቀብር አይለቅምና ይሄ የሥልጣን ሱስ ፍዳውን እያሳየውና አይሠሩ እያሠራው ዛሬ ባይሆን ነገ ተነገ ወዲያ ከጓደኞቹ ጋር ሳይቀር ሳያቆራርጠው የሚቀር አይመስልም፡፡ ቴዲ አፍሮ “ባይበላስ ቢቀር” አለ፤ ጥሩ መመርያ ነው፡፡ ሥልጣን ጥንቅር ብሎ ቢቀርስ! ኦሮሙማን ለማስደሰት ይህን ያህል መዝቀጥ? እንዴ፣ እንዲህና እስከዚህ ሲዘቅጥ እንዴት ትንሽ ቅፍፍ አይለውም? የተሸከመው 3ኛ ዲግሪስ ምን ይታዘበው?

አሁንም ቢሆን ብዙ የረፈደ አይመስለኝም፡፡ ይህ ሰው ማበዱ እውነት ነው፤ ምንም ዓይነት ክርክርና ሎጂክ የዚህን ሰውዬ ዕብደት አይሽርም፡፡ ካበደ ደግሞ ዘመድና ወገን ተመካክሮ እርሱ ባያምንበትም እንኳ ወደቀረበው ጠበል ሄዶ ለተወሰኑ ሰባቶች ይጠመቅ – እንዲህ የሚያሰቃዩትና እንደእስስት ጠባዩን የሚለዋውጡት የሠፈሩበት አጋንንት ጩኸውና ለፍልፈው ከሰውነቱ ይወጡለታል፡፡ ሰውዬው እንዲህ ያንቀዠቀዠው አለነገር አይደለምና ሁነኛ ዘመድ የሚያስፈልገው ጊዜ አሁን ነው፡፡ አማራ ጠልነቱን ወሰን ያብጅለት፡፡ ፀረ አማራነትም ሆነ በጥቅሉ ፀረ ሰው መሆን የኋላ ኋላ ለማወራረድ የሚከብድ ችግር ውስጥ ይከታል፡፡ ሕወሓት በማኒፌስቶ ደረጃ ቀርፆ አማራንና ኦርቶዶክስን ለማጥፋት ያወጀው ታሪካዊ ሰነድ እስካሁን አልተፋቀም፡፡ ያንን ሰነድ እንዳለ ተቀብሎ ተግባራዊ እያደረገ ያለው የአቢይ አህመድ ኦሮሙማም አማራን በያለበት አንገቱን እየቀነጠሰ እንደሚገኝ ሁላችንም የምናውቀው የአደባባይ ምሥጢር ነው፡፡ በቅርቡም በአጣዬ ላይ የደረሰው ነገር ይህን በግልጽ ያሳያል፡፡ የአቢይና የሽመልስ ታዛዦች በጠራራ ፀሐይ በሚዲያ እንዳስታወቁት “አማራን ከዚህች ከተማ ድራሹን አጥፍተነዋል፡፡ አማራን እዚያ ማዶ ተራራ ወትፈናታል፡፡ ከከተማዋ ጨርሰናታል፡፡  እዚያ አካባቢ የአማራ ልዩ ኃይል አለች ይላሉ፤ ግን እናጠፋታለን፡፡ እናንተ በዱኣ ዕርዱን፡፡ ነፍጠኛን በቅርብ ጊዜ እንደመስሳታለን” እያሉ በግልጽ ማወጃቸው በአማራ ላይ የሚካሄደውን የዘር ማጥፋት ኦህዲዳዊ ዘመቻ የሚገልጽ ነው፡፡ ይህ የሆነው ደግሞ በቀደም ነው፡፡ አጣየን በአንድ ሰዓት ውስጥ ማዳን ይቻል ነበር፡፡ ግን የብርሃኑ የአጎትና የአክስት ልጆች የላኳቸው ኦነግ ሸኔዎች ሰሜን ሸዋን ለሣምንታት ሲያተራምሱ ብርሃኑን ጨምሮ ሁሉም የፌዴራል ተብዬውና አብዛኛው ተፎካካሪ ፓርቲ ፀጥ ረጭ ነበር ያለው – ምክንያቱም እያለቀ የነበረው ሌላ ሣይሆን የፈረደበት አማራ ነበር፤ ነውም፡፡  

ሌላውን እንተወው፡፡ ባንተወውማ ከአርባ ጉጉ ጀምሮ በአሰቦት ገዳም፣ በባሌ፣ በበደኖ፣ በሻሸመኔ፣ በሐረር፣ በድሬዳዋ፣ በወለጋ፣ በመተከል፣ በመሀል አዲስ አበባ፣  በአዲስ አበባ ዙሪያ … በመላዋ ኢትዮጵያ ላለፉት 30 ዓመታት በአማራ ላይ የደረሰውን የዘር ጭፍጨፋና መፈናቀል በዝርዝር ማንሳት እንችል ነበር – በህክምና ስም በመርፌ የተደረገውን የማምከን ሤራ ጭምር፡፡ ተመርዘው የሞቱትን የብአዴን ጉልቻ ባለሥልጣናትንና በፖለቲካ ሤራ እስከወዲያኛው የተሸኙትን እነአምባቸውንና አሣምነውንም ሳንዘነጋ፡፡

የዘር ጭፍጨፋው በአማራ ላይ ብቻ የተወሰነ እንዳልሆነም ሰሞነኛው የትግራይ ሁኔታ በግልጽ ያስረዳል፡፡ “ዐይጥ በበላ ዳዋ ተመታ” እንዲሉ ሆኖ ሕወሓት ባጠፋ የትግራይ ምሥኪን ዜጋ ያልበላውን ዕዳ እያወራረደ ነው፡፡ የኔ የሚለው የፌዴራል ተብዬው የኦህዲድ-ኦሮሙማ መንግሥት፣ የመበቀያ ጊዜ ይጠብቅ የነበረ የጠላትን ሀገር ወታደር አስገብቶ የትግራይን ሕዝብ ያለርህራሄ እያስጨፈጨፈው እንደሚገኝ ከዚያ አካባቢ ከሚወጡ መረጃዎች መገንዘብ ይቻላል፡፡ የትግራይ ሕዝብ ከትግሬነቱ በስተቀር እንዲህ በዐረመኔዎች ሴቶቹ የሚደፈሩበት፣ ኑሮው የሚመሰቃቀልበት፣ ከትምህርትና ከዕውቀት ማዕድ ተገልሎ ለጨለማ ሕይወት የሚዳረግበት፣ ሕይወቱ እንደቅጠል የሚረግፍበት፣ ርሀብና ጥማት የሚፈነጩበት፣ ዕርዳታ የሚታገድበት፣ ከእርሻና ከምርት ተግባሩ የሚስተጓጎልበት፣ በቤቱ ታፍኖ እንዲያልቅ የሚደረግበት፣ ከቀየው የሚፈናቀልበት…. ሌላ ምክንያት የለም፡፡ ይህንና የዘመናት የአማሮችን ማለቅ መካድ ከይሁዲነት የባሰ ስም የለሽ ክህደት ነው፡፡ ብርሃኑና ብርሃኑን መሰል በዜጎች ደም የሚቆምር ሁሉ ዋጋውን የሚያገኝበት ዘመን ሩቅ ባይሆንም እስከዚያው ድረስ ግን ከሰውነት በታች የሚያስፈርጅ ድርጊታቸውና አነጋገራቸው ያናድዳል፡፡ አዎ፣ “ወይ አታምር ወይ አታፍር” ማለት ይሄኔ ነው፡፡ የፖለቲካ ሽርሙጥና ውስጥ ገብቶ በሥልጣን አራራ የሚሆነውን፣ የሚናገረውንና የሚያደርገውን ከሚያጣ የቆሸሸ ስብዕና ይልቅ የምትልሰውንና የምትቀምሰውን አጥታ ሰውነቷን በመሸጥ የምትተዳደረው የለየላት የቁጭራ ሠፈር ሸርሙጣ በእጅጉ ትበልጣለች – ይህች የተከበረች ሴት ከነዚህ ለገንዘብና ለሥልጣን ሲሉ ኅሊናቸውን በፈቃደኝነት በባለጌዎች ከሚያስደፍሩ ፍናፍንቶች የበለጠ ዋጋ አላት፡፡ እርሷ ወደዚያ “ሥራ” የገባችው አማራጭ አጥታ ነው፡፡ እነዚህ ግን ብዙ አማራጭ እያላቸው ሊቀ ሣጥናኤል አንጎላቸውን እንዲቆጣጠረውና በአምልኮተ ሰይጣን የብልጭልጩ ዓለም የሥጋ ገበያ እንዲከብሩ ስለፈቀዱ ብቻ ነው፡፡ እንዳማሩ መሞት ዕርም በሆነባት ኢትዮጵያ ብዙ ጉድ እያየንና እየሰማን ነው፡፡ እነዘሩ የምትባሉ የአቢይ የፕሮቶኮል ሹሞች እንግዲህ ተንጨርጨሩ፡፡ ትንሽ ጊዜ አለቻችሁ፡፡ በግልጽ የምንተያይበት ወቅት እየመጣ ነውና ያኔ ማን ከሆድ ማን ደግሞ ከአእምሮ እንደሆነ እናያለን፡፡ እስተያው ግን ማንበብህ ይቀራል እንጂ እውነቱን ብቻ እንጽፋለን!!

Filed in: Amharic