>

"የወረራው ዋና ባለቤት አማራ ነው፤ ከአማራ ጋር ሒሳባችን እናወራርዳለን...!!!" (የትህነጉ ጀኔራል ከጫካ የተናገረው ነው)

“የወረራው ዋና ባለቤት አማራ ነው፤ ከአማራ ጋር ሒሳባችን እናወራርዳለን…!!!”
የትህነጉ ጀኔራል ከጫካ የተናገረው ነው

 

“ሁሌም ትግላችን ከአማራ ጋር ነው። አብይና ኢሳያስን አስታርቆ፣ አብይን አሳምኖ እንድንወረር ያደረገን አማራ ነው። የወረራው ዋና ባለቤት አማራ ነው። ከአማራ ጋር ሒሳባችን እናወራርዳለን። የግድ መውራረድ አለበት።”
( መድረክ መሪዎቹም በድምፅ ማጉያ “ሒሳብ እናወራርዳለን” እያሉ ከታዳሚው ጋር ይደጋግሙታል።)
ሁሌም ትግላችን ከአማራ ጋር ነው። ወራሪዎቹ አማራና ሻዕቢያ ናቸው። የወረራው ዋና ባለቤት ግን አማራ ነው።
አማራ አብይና ኢሳያስን አስታርቆ፣ አብይን አሳምኖ እንድንወረር አድርጎናል። ከአማራ ጋር ያለን ሒሳብ ገና እናወራርዳለን። የግድ መወራረድም አለበት። ለዚህም መጀገን አለብን፣ መጀገን ግድ ይላል።
ከሻዕቢያ ጋርም ሒሳባችን ማወራረድ አለብን። ሻዕቢያ እንደጀመራት ቤቱ ድረስ ሄደን የነቀላቸው ፋብሪካዎቻችን፣ የወሰደብን ሃብት በሙሉ ሒሳባችን እናወራርዳለን። ትግሬ ገድለህ፣ የትግሬ ንብረት ዘርፈህ በሰላም መተኛት የለም።
አሁን ትግራይ ነጻ ለመውጣት ቀላል ነው። አጭርም ነው። አሳጥሩትም እየተባልን ነው። ነጻ ለመውጣት አሁን በአጭር ጊዜ እናሳካለን ግን ሒሳባችንም ማወራረድ አለብን። መጀገን ያስፈልጋል።
Filed in: Amharic