>

"አዲስ አበቤ ልዩ ጥቅምንና የዘር ፖለቲካን  መርጧል...!!!" (ይርጋለም ታደሰ)

“አዲስ አበቤ ልዩ ጥቅምንና የዘር ፖለቲካን  መርጧል…!!!”

ይርጋለም ታደሰ
ምርጫ ትራምፕን ይወልዳል ! ዲሞክራሲን እየመረረህም ትውጠዋለህ ! የኛ ስራ ምርጫው አለመጭበርበሩን ማረጋገጥ ብቻ ነው። ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው እንዲሉ ፣ ከዚህ በኋላ በድምፅህ የመረጥካቸው ክብርት ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጨቆኑህ ብለን ልንታገልልህ ይከብደናል። አዲስ አበቤ ልዩ ጥቅምንና የዘር ፖለቲካን በማያሻማ መልኩ መርጧል። እስከዛሬ ያልመረጥከው ከንቲባ በህገወጥ መንገድ የተጫነብህ መስሎን ሳንታክት ታግለንልሃል፣ ከትላንት በስቲያ በድምፅህ ያረጋገጥከው የምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤን ህጋዊነት ነው።
ህዝብን አንንቅም ፣ አናንጓጥጥም ! ምንም ያህል ቢቆጨንም አዲስ አበቤ የዘር ፖለቲካን ከመረጠ ፣ እኛም ይህ ይከበርለት ዘንድ እንጠይቃለን።
ወደ post election analysis መምጣታችን አይቀርም ፣ ኢዜማ ባልደራስ አብሮነት እናት ፓርቲ ወዘተ …. ልዩነታቸው ምን ነበር ? የልዩ ጥቅም ባለቤቱ በሰፊ ልዩነት ሊያሸንፍ እንዴት ቻለ የሚለው ጥያቄ መልስ የሚያሻ ጉዳይ በመሆኑ ሁሉም ፓርቲዎች በሰፊው ሊመክሩበት ይገባል።
ለሁሉም የዘር ፖለቲካን ለመረጠው አዲስ አበቤና ለክብርት ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልካም የፍቅር ዘመንን እንመኛለን። ዲሞክራሲን እየመረረህም ትውጠዋለህ !
Filed in: Amharic