>
5:26 pm - Saturday September 17, 7831

እንደ ጦርነቱ ምርጫውም ቀጣይ 7 ወር ያስቆጥር ይሆን...??? ሥርጉተ©ሥላሴ

እንደ  ጦርነቱ ምርጫውም ቀጣይ 7 ወር ያስቆጥር ይሆን…???
ሥርጉተ ሥላሴ

*…. የፀጥታው ሁኔታ አዲስ አበባ ባልቦላው ያለው ከዶር አብይ አህመድ ዘንድ ነው። ዘረፋ ሲያስፈልግ ባንክ አሰብረው ያዘርፋሉ፣ ሽብር ሲፈልጉ አሸባሪ አደራጅተው ይገድላሉ፣ እንዲህ ሲያሰኛቸው ደግሞ ባልቦላውን ይዘጋሉ። የሀጫሉ ነፍስ ለዚህ የኮረጆ ቀን የጦስ ዶሮ ነበር። 
 
ዕለተ አርብ ማዕዶተ ኢትዮጵያ
በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና
በቢሆነኝ የተብራራ ብራ
በሰብለ ሕይወት አዝመራ
ለራህብ የሚራራ።
“ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ።”
(ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯)
አንድ ነገር አሰኩኝ። ዶር ታምራት ነገራ ስለ ወት ብርቱካን ስኬት¡ እና ማሸነፍ¡ ዕንባ ይተናነቀው ነበር። ሲቃ ቢጤ። እኔ ምን እንዳሰብኩ ታውቃላችሁ የዕንባ ማዳረቂያ ሽክ ያለች የእጅ ማህረብ።
ስለ ትናንት ከሆነ ሥርጉተ የፈፀመችው፣ የተቀበለችው መካራ ወዘተረፈ ነው። ስለዚህ ፕሮፖጋንዲስት አያስፈልገንም።
 ስለዛሬ ከሆነ ደግሞ አንድ አባል የሌለው መሥራች ፎርም ሞልተው ያልተመዘገቡበት ከህወሃት ሙራሹ ያለቀ ዕዳ ወደ አዲሱ ዕዳ በካሬታ እዬተጫነ የተገለበጠ ውራጅ አባል ተሸክሞ ለዛ ዕውቅና አሰጥቶ አሸነፈ ውርዴት ነው።
ይህም ብቻ አይደለም ሦስቱ ሰኔወች፣ ሦስቱ ጥቅምቶች ለዚህው የሸፍጥ ኮረጆ ጥርጊያ ነበር። በሰላም ተጠናቀቀ ለማስባል ርሸናው እስሩ ጦርነቱ ለዚህው የገዳ የምርጫ ኳኳቴ። እንደ አንድ በሳል ተንታይ ይህን ገመና ተሸክሞ ብርቱካን አሸነፈች የገማ እንቁላል ጫጩት ሆነ ይሆናል።
ይህም ሆኖ እስከ አሁን ውጤት ለመንገር ምጥ ነው የሆነው። ጋንቤላ ቤንሻንጉል ሲዳማ ምርጫው ቀጥሎ በማግስቱ ነበር። ቁሳቁስ እንኳን በቅጡ ለማስተዳደር ያልቻለ ዕንቅልፍ አቅም “አሸነፈች” ፌዝ፣ ስላቅ ነው።
በዓለም አራተኛ መዲና በዘመነ ዲጂታል ይህን መሰል ዝልግልግ ተግባር ብርቅ ሲሆን ከዕውር ቤት ዓንድ አይና ብርቅ መሆኑ አይደንቀኝም።
ተመክሮ የለም ተሰጥዖም የለም። ማደራጀት የማይክ፣ የፋሽን ውሎ አይደለም። ቢሮ እያደሩ እዬዋሉ የሰከነ ተግባርን ይጠይቃል። ምንም ምንም ነው።
የፀጥታው ሁኔታ አዲስ አበባ ባልቦላው ያለው ከዶር አብይ አህመድ ዘንድ ነው። ዘረፋ ሲያስፈልግ ባንክ አሰብረው ያዘርፋሉ፣ ሽብር ሲፈልጉ አሸባሪ አደራጅተው ይገድላሉ፣ እንዲህ ሲያሰኛቸው ደግሞ ባልቦላውን ይዘጋሉ። የሀጫሉ ነፍስ ለዚህ የኮረጆ ቀን የጦስ ዶሮ ነበር።
ብዙ ጊዜ ፅፌያለሁ እኔ ይህ ሁሉ መፈናቀል፣ ግድያ፣ ጭፍጨፋ፣ ግፍ አብይዝምት ካለተቀናቃኝ ዙፋን ለመድፋት የገዳ ልዕልት መንገዳቸው ጨርቅ እንዲሆን የተሰናዳ የሞገድ ልብወለድ ትራጀዲ ትወና ነው።
እራሱ ወሮ አዳነች አበቤ ም/ ከንቲባ ከመሆናቸው በፊት የተፈፀመው የባልደራስ መሥራቾች እስር ለዚህ ቀን መሰናዶ ነው። ከንቲባዋ በድሎት፣ በምቾት ካለ ጫና የገዳን ወሩራ፣ የገዳን አስምሌሽን፣ የገዳን መስፋፋት እንዲያስፈፅሙ ነው።
ቲም እስክንድር ባይታሠር ሙሉለሙሉ ባልደራስ ያሸንፍ ነበር። ይህ ብቻ አይደለም ዶር ታምራት ከሰይፋ ሾው ጋር ወት ብርቱካን ሚዲቅሳ ጋር የተደረገው ቃለ ምልልስ አዲስ አበቤ ግልብጥ ብሎ ወጥቶ እንዲመርጥ አድርጓል አለ። ወቷ በተወዳደሩ እና ያያት ነበር።
አዲስ አበቤ የወጣው አቶ እስክንድር ነጋ ይወዳደራል ስለተባለ ብቻ ነው። ምስሉ ተለጥፎ ንቅንቅ አላለም ነበር። የተመዘገበው አንድ ሚሊዮን የመሙላት አቅም አልነበረውም።
አዲስ አበቤ ለኢትዮጵያዊነት ክትር አይሻም። ማን ምን እንደሆን ፕሮፖጋንዲስት አይሻም። አዲስ አበቤ ሙያ በልብ ነው። ቲም እስክንድር ባይሠር በተፈጠረበት መክሊቱ ልክ በንፅህና ይጓዝ ስለነበር ድሉ ይታይ ነበር። ግን ሰላዩ ጠቅላይ ሚር ከ97 ጀምሮ ባጠኑት ማስተር ፕላን አሁን ባለበት ሁኔታ ሂደት ይተክዛል።
አዲስ አበቤ ለኢትዮጵያዊነቱ ዘብ አደር ነው። ማገዶም!
አቶ እስክንድር ነጋ ቅባዕው ታይቷል። ዘመን መሰከረ። ግሎባል ታሪክ በኢትዮጵያ ምድር ተሰርቷል። የእሱ ተፅዕኖ ፈጣሪነት በቅናት ላበዱት ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ መስጥረው የያዙት በሽታ ነው።
ሰንሰለቱ ትብትቡ ከኢትዮጵያዊነት ጋር ግብግብ ነው። አዲስ አበቤ ካሸነፈ ሰንሰለቱም፣ ትብትቡም ይፈታል። ከተሸነፈ መከራው የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያዊነት ይሆናል።
እንደ ጉም ሽንት ወደ ኋላ ዬሚጓዘው ዝርክርኩ የገዳ ምርጫ ቦርድ ሽርክትክት ዕድምታው ቀጣይ ነው። ያልቦካ የምርጊት ጭቃ። ኢትዮጵያ ካለ አቅሙ በሚቆለል ኃላፊ ፍዳዋን አዬች። የካህዲው ብዛት ወዘተረፈ ነው። ግን ኢትዮጵያ አምላክ አላት። ቀኑን ጠብቆ ይቀጠቅጠዋል ማህበረ ካህዲን።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
የኢትዮጵያ አምላክ ካህዲን ቅጣልን። እባክህን?
Filed in: Amharic