>

ይሄ ተረኝነት ለከት አጥቷል...... አንድ ነገር ሊባል ይገባዋል ... !!! (ገለታው ዘለቀ - የባልደራስ የፅህፈት ቤት  ሃላፊ)

ይሄ ተረኝነት ለከት አጥቷል…… አንድ ነገር ሊባል ይገባዋል … !!!
ገለታው ዘለቀ – የባልደራስ የፅህፈት ቤት  ሃላፊ

*…. የወላይታ የፓርቲዎች ምክር ቤት ኮሚቴዎች ቅሬታ ያቀርባሉ:: እኛ ዘንድ ምርጫ ሳይሆን ዝርፊያ ነው የነበረው አሉኝ:: ከአፋር ዶክትር ኮንቴን አገኘሁ እናንተስ ጋር እንዴት ነበር? አልኩት::  ግልፅ ዝርፊያ ነበር አለኝ :: ሌሎችም ነበሩ :: ሁሉም ያጉረመርማሉ…..:: ያሳዝናል::
በምርጫው እለት ባልደራስ የገጠሙትን ከፍተኛ ቅርታዎች ለምርጫ ቦርድ ለማስገባት ዛሬ ወደ ምርጫ ቦርድ አመራሁ:: ከምርጫ ቦርድ በር ላይ የነበረው ጠባቂ ወዴት ነው? አለኝ:: ቅሬታ ላስገባ ነው አልኩት:: አሁን በሕንፃው ውስጥ አንድም ሰው የለም አለኝ :: እንዴ….? ምርጫ ቦርድ እኮ ቅሬታ አስገቡ… ዛሬ የመጨረሻው ቀን ነው ብሎናል አልኩት:: የእንጨት ዱላውን እየቆረቆረ መግባት አይቻልም ውስጥ አንድም ሰራተኛ የለም አለኝ:: የማልወደው ጭቅጭቅ ውስጥ ከተተኝ:: አንተ ሰው ምርጫ ቦርድ ዛሬ አምጡ አስገቡ ብሎናል እባክህ ልግባ ወይም አይቻልም አላስገባም በልና ፈርም አልኩት:: ጨርሶ አይሰማም:: ተመለስ አለኝ:: በሁዋላ ውስጥ ካሉ የምርጫ ቦርድ ሰራተኞች ጋር ሌሎች ሰዎች ተደዋውለው መጨረሻ ላይ አንድ የምርጫ ቦርድ ሰራተኛ ወጥቶ እንድገባ ሆነ:: በጣም ያሳዘነኝ ይህ ዘበኛ እንዳልገባ የሚከለክልኝ ባልደራስ መሆኔን አውቆ ነው :: በጥበቃው አካባቢ ስመለከት ይህ ነገር ሸቶን ነበር :: ወደ ምርጫ ቦርድ እየሄድኩ መሆኔን ያወቁ እነዚህ ተረኛ  አስተሳሰብ የተጠናወታቸው ሰዎች በአካባቢው ነበሩ::  ከብዙ መጉላላት በሁዋላ ወደ ውስጥ ስገባ ቢሮ ውስጥ ብዙ ሰው አለ :: የወላይታ የፓርቲዎች ምክር ቤት ኮሚቴዎች ቅሬታ ያቀርባሉ:: እኛ ዘንድ ምርጫ ሳይሆን ዝርፊያ ነው የነበረው አሉኝ:: ከአፋር ዶክትር ኮንቴን አገኘሁ እናንተስ ጋር እንዴት ነበር? አልኩት::  ግልፅ ዝርፊያ ነበር አለኝ :: ሌሎችም ነበሩ :: ሁሉም ያጉረመርማሉ…..:: ያሳዝናል::
ይህ ዘበኛ ግን ባልደራስን ለይቶ እንዲመልስ የተቀመጠ ነበር:: ለማናቸውም ለጥበቃው ኃላፊ አመልክቻለሁ ገና ይከሰሳል:: የዚህ የተረኝነት እሳቤ ግን ለከት አጥቷል:: አንድ ሊባል ይገባል ::
Filed in: Amharic