>

ልንሻገር ወደ ፍፃሜው ደርሰናልና ሁሉም ኢትዮጵያዊ ይዘጋጅ!!!! ይዘጋጅ!!!! ይዘጋጅ!!!!! (ደጀኔ አሰፋ)

ልንሻገር ወደ ፍፃሜው ደርሰናልና ሁሉም ኢትዮጵያዊ ይዘጋጅ!!!!

ደጀኔ አሰፋ


የግድባችን ሙሊት መጀመሩን ተከትሎ ግብፅ የምትይዝ የምትጨብጠውን አጥታለች:: የነብስ ግቢ ነብስ ውጭ ዘመቻ እያካሄደች ትገኛለች:: ግብፅ የሶስትዮሽ የትብብር ማዕቀፉን (CFA 2015) በመፈረሟ አሁን ላይ ሰማይ ብትቧጥጥ የሚቀየር ነገር እንደማይኖር አውቃ ተስፋ ከቆረጠች ቆይታለች:: ነገር ግን አሁን እንዲህ እየተራወጠች ያለችው ከጀርባ የአሜሪካ እና የእንግሊዝ እጅ እንዳለበት ግልፅ ነው:: የጁንታውም ጉዳይ በዚሁ መነፅር እንጅ ለብቻው የሚታይ አይደለም::
ምዕራባዊያኑም በኢትዮጵያ ተስፋ ቆርጠዋል:: በተለይ፤ “ከእኔ ወዲያ ማን ጀግና አለ የሚልና የሴት ጓደኛው ሳትነግረው ለሌላ እንደታጨችበት ኮበሌ ጎረምሳ” ፤ አሜሪካ እንዲህ እምቡር እምቡር የምትለው በኢትዮጵያ ምድር ከዚህ ወዲያ በሪሞት ኮንትሮል የሚዘወር መንግስት እንደማይኖር ጠንቅቃ ስላወቀች ነው::
አሜሪካ በዚህ ደረጃ እፍረት ቢስ ሆና እርቃኗን ስትወጣ አየናት:: በሰው ማጀት ካልፈተፈትኩ ስትል አሜሪካ ምን ያህል ወጥ የረገጠች ከጡንቻ በቀር ቅንጣት ጭንቅላትም ሃፍረትም የሌለባት ተራ የሰፈር ጉልቤ መሆኗን በግልፅ ተመለከትን:: ከነዚህ ጋር ነበር ወይ አጋር ሆነን ስንሰራ የኖርነው ያስብላል:: ለነገሩ ጁንታው ኢትዮጵያን ምን ያህል ሲጫወትባት ምን ያህል ክብር አልባ እንዳደረጋት እና ምን ያህል በእጅ አዙር በቅኝ ግዛት ሲያዝገዛት እንደነበር አስተዋልንበት::
ምዕራባዊያኑ በተለይም አሜሪካ….
አንዴ አሸባሪው ጁንታ ወደ ድርድር መጥቶ ዳግም ወደ ስልጣን ካላመጣ ፤ አንዴ የእከሌ ጦር ከዚህ ካልወጣ ሲሉ ፤ አንዴ በህገመንግስታችን ሲመጡ ፤ አንዴ ስለ ስንዴ ሌላ ጊዜ ስለ ጀኖሳይድ ሲያወሩ ፤ አንዴ ግድቡ ያለ ግብፅ ስምምነት ውሃ መሙላት አይቻልም ሲሉ… ምንም ማቆሚያ የሌለው ልቅ ፍላጎታቸውን ስናስተናግድ የራሳችን ነገር የሌለን ብኩን ሃገር አስመሰሉን:: ትላንት ስለ ሃገርና ክልል ዛሬ ስለ ዞን እና ወረዳ ካወሩ ነገ ስለ ቀበሌና መንደር ማውራታቸው አይቀርም:: እጅግ ይቀፋል!!!!! በአጠቃላይ የአሜሪካ የእንግሊዝ እና የአውሮፓ ህብረት ጉዳይ ብዙም የሚያዛልቅ አይደለም:: ኢትዮጵያ ካልፈረሰች አለያም አብይን በግድያ ካላስወገዱ የሚተውን አይመስሉም::
ስለዚህ ዲፕሎማሲውን ከማጠናከር ጎን ለጎን ሌላ አማራጭ መንገድ ካልተዘየደ በቀር ኢትዮጵያን ከማፍረስ አለያም አብይን ከማስገደል የማይመለሱ መሆናቸውን ኢትዮጵያውያን ልናውቅ ይገባል!!! ለዚህ ደግሞ የአብይን ስም በማጠልሸት ለጦር ፍርድ ቤት ከማሰብ ጀምሮ የኢትዮጵያን ችግር ዓለምአቀፋዊ (internationalize) ለማድረግ እና በሰላም አስከባሪ ስም ጣልቃ ገብተው እንደ ሶሪያ ሊያፈርሱን ብዙ ጥረዋል:: ሆኖም እስከዛሬ በፈጣሪ እገዛ ፤ በህዝባችን አንድነት እና በመንግስታችን ቁርጠኝነት ነገሮችን ማኔጅ አድርገን ሁሉንም በድል ተሻግረን ፀንተን ቆመናል!!!!
ይሄው ዛሬ ደግሞ ግብጽ በአራት የጦር ሀይል አውሮፕላኖች የተጫነ እርዳታ ለሱዳን መላኳን የግብጽ ጦር ሀይል ልሳን በሆነው ፔጅ ገልፃለች። ይህ እርዳታ ግን ለሱዳን አይመስልም:: ምናልባት ለጁንታው የሚላክ ጦር መሳሪያ ወይም ግድቡን እንመታለን ሲሉ ላስተላለፉት ዛቻ ትንሽ ሙከራ ማድረጊያና ማንቧተሪያ ሊሆን ይችላል:: አሜሪካ እየዞረችን በመሆኑ መጠርጠር አይከፋም:: የኢትዮጵያ ችግር ዓለምአቀፋዊ ይዘት እንዲኖረው በማድረግ አሜሪካ ጣልቃ የምትገባበትን ነገር እያመቻቸች ሊሆን ይችላል::
ዞሮ ዞሮ ይህ ወቅት እንደ ወርቅ በእሳት ተፈትነን የምንወጣበት ጊዜ መሆኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል!!!! ዘላለም አለም አቧራችንን እያራገፍን ክብር አልቦ የእከክ ህይወት ከመኖር ይህ የመጣብንን ተግዳሮት እና ፈተና በፅናት ታግለን እና የህይወት መስዋዕት ከፍለን ብናልፍ እንኳን በህይወት የተረፈው ቀሪው ኢትዮጵያዊ እና መጭው ትውልድ ግን ክብር ያለው ኑሮ እንዲኖር እናስችለዋለን!!!!! እስከመቼ የአሜሪካ ዛቻና ማስፈራሪያ ማራገፊያ እንሆናለን??? ለዚያው ሃቅ ይዘን እነሱ ግን ገንዘብ እና ዘመናዊ ጦር ስላላቸው ብቻ እንዲህ ሊያዙን ይቃጣቸዋል?? አረ ይበቃናል!!!! ያማል በጣም!!!!
ኢትዮጵያ በዘመኗ እንዲህ ተፈትና አታውቅም!!!! ፈጣሪ ግን አስቸጋሪ ፈተናዎችን አሳልፎን እዚህ እንዳደረሰን ይህንንም በድል ያሻግረናል!!! ስለዚህ አስፈላጊውን ስነ ልቦናዊ መንፈሳዊ እና ወታደራዊ ዝግጅት እናድረግ!!! ሁላችንም በየእምነታችን እንፀልይ!!! አንድነታችንን የበለጠ እናጠንክር!!! እንዋደድ!!! እንናበብ!!! የተቃውሞ ሰልፎች በውጭም በውስጥ ይደረጉ!!! ህዝባችን ለሁሉም ጥሪ ራሱን ያዘጋጅ!!!!! ሃገሬን ያለ ሁሉ ከመንግስት ጎን ይቁም!!!! ኢትዮጵያን ያለ ሁሉ ከአብይ ጎን ይሰለፍ!!!! ምርጫ ሳይሆን ግዴታ ነው!!!!
ሰራዊታችንም በወልቃይት : ሁመራ እና ራያ ላይ በደንብ ይዘጋጅ!!! ህዝቡም ከመከላከያና ከአማራ ልዩ ኃይል ጎን ይሰለፍ!!!! የሱዳን ኮሪደሮች ላይ አስተማማኝ ዝግጅት ይደረግ!!!! የአፋር ድንበሮች ላይ ጥበቃ ይጠናከር!!!!
መንግስትም የበለጠ ይትጋ!!!! በዲፕሎማሲው የቻለውን ያህል ይሂድበት!!!! የሚያግዙ ምሁራን በየኤምባሲዎች ይግቡና ያግዙ!!!! ሎቢስቶች ይቀጠሩ!!! የተቻለው ሁሉ ቀረ ሳይባል ይሞከር!!! የኢትዮጵያን ክብርና ጥቅም ግን ለሰከንድ አሳልፎ አይስጥ!!! ይጨክን!!! የሚመጣውን ለማስተናገድ አመራሩም ዝግጁ ይሁን!!! ማዕቀብ ቢጣል ጦርነት ቢታወጅብን ሁሉንም ለማስተናገድ ይዘጋጅ!!!! አማራጭ አጋሮችን ለይቶ ጥልቅ መግባባት ላይ ይድረስ!!! ለሁሉም ዓይነት እርምጃ ራሱን ያዘጋጅ!!!! ሊነጋ ሲል ይጨልማል!!!!! መንጋቱ ግን የግድ ነው!!!! የኢትዮጵያ አስደናቂ ድል ሊበሰር በደጅ ነው!!!! አሜሪካ ልትዋረድ ጠላቶቻችን ከስመው ዳግም ላናያቸው ፤ ኢትዮጵያ ግን በድል ልትሻገር ቃል ከሰማይ ወጥቷል!!!! ኢትዮጵያዊ ሁሉ ተነስ!!!! መሻገራችን እሙን ነው!!!!!
Filed in: Amharic