>

አሸባሪው ህወሓት በአፋር ህዝብ ላይ ጦርነት ከፈተ ...!!! የአፋር የክልሉ መንግስት መግለጫ

አሸባሪው ህወሓት በአፋር ህዝብ ላይ ጦርነት ከፈተ …!!!

የአፋር የክልሉ መንግስት መግለጫ

የአሸባሪው የህወሓት ታጣቂዎች በአፋር አርብቶ አደር ህዝብ ላይ ጦርነት ከፍተዋል።
አሸባሪው ህወሓት በኢትዮጵያዊነቱ በማይደራደረው የአፋር አርብቶ አደር ህዝብ ላይ ፈንቲ ረሱ ዞን ያሎ ወረዳ በኩል ጦርነቱን መክፈቱ ተገልጿል።
“ሰላማዊ ክልላችንን ለማተራመስ ህወሀት የለኮሰው ጦርነት በአጭሩ እንዲገታ አርብቶ አደር ህዝባችንም አስፈላጊውን ሁሉ ጥረት ማድረግ የሚጠበቅ ሲሆን አካባቢውንም በንቃት ሊጠብቅ ይገባል፤ የተከፈተብንንም ጦርነት መንግስት ከህዝባችን ጋር በመተባበር ይመክታል” ።
“ሚሊሺያችንና አጠቃላይ የፀጥታ ሀይላችን ይህን በህዝባችን ላይ የተሠነዘረውን ጥቃት የመከላከል ስራ በቁርጠኝነት የሚተገብር ይሆናል” ያለው የክልሉ መንግስት፤ “መላው የኢትዮጵያ ህዝብም እንደ አበደ ውሻ እዚያና እዚህ ለመንከስ የእብደት ስራ እየሰራ ያለውን ይህን እኩይ ቡድን በፍጥነት ግብአተ መሬቱ እንዲፈፀም እንደወትሮው ሁሉ እጅ ለእጅ በመያያዝ በጋራ በመታገል እስትንፋሱ እንዲቋረጥ ማድረግ ይጠበቅብናል”
የክልሉ ህዝብ ከፀጥታ ሀይሉች ጎን በመቆም በፈንቲ ረሱ ያሎ ወረዳ በኩል የተከፈተብንን ጦርነት እንዲመክት እና በክልላችን በየትኛውም አካባቢ ያለው ህዝባችንም ደግሞ በንቃት አካባቢውን በመቃኘት ከአካባቢው የፀጥታ ሀይል ጋር በትብብር እንዲሰራ  ጥሪ እናቀርባለን።
አሸባሪው ህወሓት በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ከፈጸመ በሁዋላ በሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ በአማራ እና በአፋር ክልል ልዩ ሀይሎች ተቀጥቅጦ ወደ በረሃ መሸሹ አይዘነጋም።
Filed in: Amharic