የሕወሓት ወዳጅ አምባሳደር ኸርማን ኮህን ሸርተት አሉ !
ታምሩ ገዳ
አሸባሪውን ሕወሓት አራት ኪሎ ያስገቡት ኸርማን ኮህን ዛሬስ ምን እያሉ ነው?
*…ህወሓትን ሙሰኛ እና አምባገነን ፣ የቀድሞው የአገሪቷ ገዥ የአሁኑ ሽፍታ ብለው ጠቅሰውታል።
ክልሎች ይህን ኃይል ለመታገል በሚደረገው ዘመቻ ልዩ ኃይላቸውን መላካቸው የሚያስገርም አይደለም ብለዋል። የዚህ ምክንያት ከ1983 ጅምሮ እስከ 2010 ዓ.ም ድረስ ኢትዮጵያን ሲያስተዳድር ሙሰኛ እና አምባገነን ነበር ሲሉ ገልጸውታል።
ኸርማን ኮህን እ.አ.አ ከ1989 እስከ 1991 የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል።
አምባሳደሩ በሕወሓት ፍቅር ያበዱና ከአራት ኪሎ ተባሮም ሲያለቃቅስ በትዊተር አብረውት ሲነፋረቁ ነበር። ሲፎክር ይፎክራሉ። መከላከያ ላይ ጥቃት ሲከፈት ሕወሓትን የሚያሸንፈው የለም ሲሉ ሸፋፋ. አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ለአሜሪካ መንግስት ዛሬም የቀረቡ ብቻ ሳይሆን አንዳንዴ የእነ አንቶኒ ብሊንከንን የጉዋዳ ሀሳብ እሳቸውን በመሰሉ ጉምቱና ዛሬም ተሰሚነት ያላቸው ዲፕሎማቶች ያስነግራሉ። እና እዛ ቤት ለውጥ እየመጣ ይሆን?
ኾኸን በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ ላይ ሚዛናዊ ያልሆኑ ወቀሳን ሲያቀርቡ የቆዩ ሲሆን ከዚህ ቀደም የአማራ ብሔር ላይ በለቀቁት የተሳሳተ መረጃ የጠነከረ ተቃውሞ ሲያገኙ ይቅርታ ማለታቸው ይታወሳል።
በመጨረሻ የወያኔ ወዳጅም ሸርተት አሉ ሐቅ ያንቃል እንዲሉ ለእነ ጌታቸው ረዳ መርዶ ነው። ቻሉት እንጂ ምን ይባላል ።ማነው ቀጣዩ?