>

መሻሻል ያለባቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሁኔታ!  (የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ)

መሻሻል ያለባቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሁኔታ! 

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ

 ኢሰመጉ ከተቋቋመበት በ1984 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት 29 ዓመታት ሲያከናውነው የነበረውን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል የቀጠለ ሲሆን፤ ከዚሀ በታች የጠቀሳቸው የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ በአስቸኳይ መሻሻል አለባቸው ብሎ ያምናል፡፡
ኢሰመጉ በሚያደርገው የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል በተለያዩ ጊዜያት በጋዜጠኞች፣ በማህበረሰብ አንቂዎች እና ግለሰቦች ላይ እስራት እየተፈፀመ መሆኑንና ታሳሪዎችም የት እንዳሉ ለማወቅ አለመቻሉን ለመገንዘብ ችሏል፡፡ ይህንንም በተመለከተ ከዚህ ቀደም ባወጣቸው መግለጫዎች ጠቅሶ፤ በመንግስት ሊወሰድ ስለሚገባ እርምጃ አስመልከቶ የመፍትሔ  ኃሳብ ጠቁሟል፡፡ በጉዳዩ ላይ በቀጠለው ክትትሉም እስራት የተፈፀመባቸው ሰዎች ቤተሰቦች ታሳሪዎቹ የት እንዳሉ  ለማወቅ እና ለመጠየቅ እንዳልቻሉ መረጃ አግኝቷዋል፡፡
በህግ ቁጥጥር ስር ያሉት ሰዎች ያሉበት ቦታ አለመታወቁ ኢሰመጉ  ለሚያደርገው የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ከትትል እቅፋት የሆነ ሲሆን፤ የመብታቸው አጠባበቅ ሁኔታም ኢሰመጉን በእጅጉ  ያሳስበዋል፡፡ በህግ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ስልጣን የተሰጠው አካል ሰዎችን ሲይዝና ከያዘም በኋላ ሊያከናውናቸው  ስለሚገቡ ተግባራት እንዲሁም በህግ ቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ከመያዛቸው በፊት እና ከተያዙ በኋላ ሊጠበቁላቸው  ስለሚገቡ መብቶች በኢፌድሪ ሕገ-መንግስት አንቀፅ 19 ስር በግልፅ ተመላክቷል፡፡
በዚህም ሰዎችን ለመያዝ ሥልጣን ተሰጠው አካል እንደዚህ አይነት ተግባራትን ሲያከናውን በህጉ ስር የተቀመጡትን ቅድመ ሁኔታዎች መሟላታቸውን  እንዲሁም የተጣለበትን ግዴታ ስለመወጣቱ ማረጋገጥ ይገባዋል፡፡
ከዚህም ሌላ በኦሮሚያ ክልል ሁሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ጃርቴ ወረዳ  ስጥ የአማራ ብሔር ተወላጆች በሸኔ ታጣቂዎች በአካባቢው መኖር አትችሉም፤ ለቃችሁ ውጡ የተባሉ መሆኑን እና በዚህም በወረዳው በሚገኙ ሀሮሎጎ፣ ጃንጂማረ፣ ሆሮዳዴ፣ አብዲ ዳንዲ እና አሣ ጉዲና ከተባሉ አምስት ቀበሌዎች ሙሉ በሙሉ ያላቸውን እርሻ መሬት እንዲሁም ሌሎች ንብረቶች ለቀው የወጡ መሆኑን፣ በተቀሩት ስድስት የሚሆኑ ቀበሌዎች ያሉ ነዋሪዎችም በእነዚሁ ታጣቂዎች አካባቢውን ለቃችሁ ውጡ ተብለው ማዋከብ እና ጫና እየተደረገባቸዉ እንደሚገኝ ለኢሰመጉ የደረሱ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
በተመሳሳይ በሰንቦ-ጨፌ ቀበሌ ውስጥ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በርካቶች በሸኔ ታጣቂዎች የተገደሉ ሲሆን የተቀሩትም በሻምቡ በኩል አድርገው ወደተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች ለመሄድ ሲሞክሩ ተከልክለው ችግር ላይ እንደሚገኙ የሚጠቁሙ መረጃዎች ለኢሰመጉ ቀርበዋል….
Filed in: Amharic