>

የዘር ፍጅት መሀንዲሱ ዶ/ር ዲማ ነገዎ  ስለምርጫና ዴሞክራሲ የሚሰብክባት - ኢትዮጵያ... ¡¡¡ (ጎዳና ያእቆብ)

የዘር ፍጅት መሀንዲሱ ዶ/ር ዲማ ነገዎ  ስለምርጫና ዴሞክራሲ የሚሰብክባት – ኢትዮጵያ… ¡¡¡
ጎዳና ያእቆብ

*…. የትላንትናው ኦነግ መሪ፤ የአርባጉጉና በደኖ መሀንዲስ፤ የቀድሞውን ከ500ሺህ በላይ ይሆናል የሚባለውን ጦር ሰራዊት ” ነፍጠኛ” ብሎ የበተነ ሰው በዓብይ አህመድ ቁልፍ ስልጣን ተሰጥቶት ስለ ምርጫ ማብራሪያ ይሰጣል። አንተ ስለ አገር ህልውና ቀን ከሌት እ..ህ…ህ…ህ
ትላለህ
ዶ/ር ዲማ ነገዎ ለሰራው ወንጀል እስር ቤት መሆን ሲኖርበት በንፁሀን ደም እንደተጨማለቀ ስለዲሞክራሲና የዲሞክራሲ እንዱ መገለጫ ስለሆነው ምርጫ ሲለፍፍ ስትሰማ ፍትህ የሚባል ነገር ከኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት እንደተፋታ ያሳይሀል::
 አያፍርሩም ደግሞ እኮ ስለ ህዋሃት የሀያ ሰባት አመት አብረው ስላዘገሙበት ጉዞ ሊሰብኩህ ስፈልጉ!! ስለ ወንጀላቸው ሳይሆን ወይ ኦሮሞ ስላልሆኑ ወይም ደግሞ ብልፅግና ፓርቲን ስላልተቀላቀሉ እንጂ ህግ ስለጣሱ: ዜጎችን ስለበደሉና ወንጀለኛ ስለሆኑ እንዳልሆነ ግልፅ ይሆንልሀል::
ለነገሩ አብይ አህመድም በመደበኛም ይሁን በኢ-መደበኛ መንገድ የዘረፋችሁትን ይዛችሁ: ከነወንጀላችሁ ብልፅግናን ተቀላቀሉ ብለናቸው ነበር:: እምቢ ማለታቸው እንደፓርቲ ትልቅ የግምገማ ችግር ነው ብሎ ነግሮናልና ግብግቡ የፍትህ አይደለም:: ቢሆንማ ዛሬ ስለፍትህ የሚያወሩት ሁሉ ማሰርና ማረም ፍትህ የሚጠይቀው ነበር::
 የዘረፉትን መመለስ ፍትህ የሚጠይቀው ነበር:: ያ ቢሆን ዲማ ነገዎ ሌክቸር ሰጪ ሌላው ተሳዳጅ ባልሆነ ነበር::
ጦርነት ህግ በሌለበት ሀገርና አንድ ሰው የፈለገውን በሚያደርግበት ሀገር የህግ ማስከበር ዘመቻ የሚል ስላቅ ባልኖረ ነበር:: አብይ አህመድ 4 ኪሎ ተቀምጦ ለመብትና ለነፃነት ሲታገል የኖረው የከተማ ባህታዊ እስክንድር ነጋ በእስር ቤት ባልማቀቀ ነበር:: የኢትዮጵያ ነገር ሁሉ መቼም ግልብጥ ነው:: የሞተላት ቀርቶ የገደላት በምቾት የሚኖርባት ሀገር:: የነዲማ ነገዎ የጉድ ሀገር!!
Filed in: Amharic