>
5:29 pm - Wednesday October 11, 6445

ሐቅ ሐቁን እናውራ  ባንዲራዬ... ተባለ'ኮ!?  (የኑስ መሀመድ)

ሐቅ ሐቁን እናውራ  ባንዲራዬ… ተባለ’ኮ!? 
የኑስ መሀመድ

ትህነግ የመገንጠል እቅዷን “ስለባንዲራዋ” በመዝፈን አሀዱ ልትል ነው። ወጣቱ ድምጻዊ ኤፍሬም ኣማረ እና ድምጻዊት ኤዴን ገ/ስላሴ “ባንዲራችን ይሄ ነው” ሲሉ አዲስ ዘፈን አዘጋጅተው ጨርሰዋል። ዜማው የበረኸት ወልዱ ሲሆን ግጥሙ ደሞ የተጋዳላይ ፍስሃ ዘርይሁን መሆኑም ታውቋል። እነዚህ ድምጻውያ ምን ያክል የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍቅር እንደነበራቸው ከናንተ በላይ ምስክር ሊኖር አይችልም።
ትህነግ በትግራይ ክልል ምን ያክል ተጽዕኖ ፈጣሪ ቢሆንም ሙሉውን የትግራይ ማህበረሰብ ግን አይወክሉም። በዛው ልክ እከሌ እከሌ ብለን የምንጠራቸው ሚሊዮን የትግራይ ተወላጆች አሉ ስለሐገራቸው አንድነት ሲጨነቁ ውለው የሚያድሩ። በተግባርም ከሕወሃት ጋር በመጋፈጥ ዋጋ እየከፈሉ ያሉ ጀግና የትግራይ ልጆች አሉ። እነ ኤደን ይሄንን የኮሚኒስት ጨርቅ የኛ ባንዲራ ነው ብለው ሲዘፍኑ እሰይ አበጃችሁ የሚላቸው ትህነግ እንዳለ ሁሉ የኔ ሰንደቃላማ አጼ ዮሐንስ የሰጠኝ የጥንት የጥዋቱ የአባቶቼ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ነው የሚላቸው ትግራዋይም ሞልቷል።
ነፍስ ላለውም ነፍስ ለሌለውም፤ ሕወሃትን መቃወምና የውኃ ሽታ ማድረግ የሐገርን አንድነትና ሉዓላዊነት ለመጠበቅ አንዱ እርምጃ መራመድ መሆኑን ደግሞ ደጋግሞ ማሳወቅ ያስፈልጋል።
Filed in: Amharic