>
5:29 pm - Thursday October 10, 3574

"እኛ አፋሮች በፍቅር እንጂ በመሳሪያ የምንበረከክ አይደለንም...!!!" የአፋር ክልል ፕሬዝዳንት ሃጂ አወል አርባ 

“እኛ አፋሮች በፍቅር እንጂ በመሳሪያ የምንበረከክ አይደለንም…!!!”
የአፋር ክልል ፕሬዝዳንት ሃጂ አወል አርባ 

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳደር መልዕክት
ከሁሉም በፊት ሁሌም አንደኛ ሰላም ፣ ለሁለተኛም ሰላም ፣ ለሶስተኛ ጊዜም ስላም በቅድሚያ ሰላም ብለው ሁሌ ሰላምን የሚሰብኩት የአፋር ርዕሰ
መስተዳድር አቶ ሐጂ አወል አርባ በወቅታዊ ነባራዊ ሁኔታን በማስመልከት ባስተላለፉት መልዕት….
” ጦርነት ምርጫችን አይደለም። ወደንና ፈቅደን የገባንበት ጦርነት አይደለም። የህወሓት አመራሮች በፌዴራል መንግስት የነበራቸው የበላይነት ስልጣን ስያጡ ከእኛም ውጭ ሀገር በሌላው ልትመራ አይገባም ብለው በእምቢተኝነት በእብሪት ተሞልተው የራሳቸውን ክልል በእሳት ከአንድደው ለምን አፋር ሰላም ይሆናል በሚል የአፋር ምድር የጦርነት አውድማ እንዲሆን ትግራይን ለስልጣናቸው ስሉ በለኮሱበት እሳት አፋርን ለመፈጀት ከግዛታቸው አልፈው ታዳጊ ህፃናትን አሳልፈው አፋርን የጦርነት ቀጠና ለማድረግ ጁንታው በግድ የእኔ ፅዋ ትቀምሳለህ በማለት ክልላችንን በጉልበት በመውረር ጦርነት ከፍቶብናል።
የአፋር ህዝብ ለህሊናው ለመጣ እንኳን ለህወሓት ህፃናትን ለእሳት ማገዶ ለሚያደርግ ሽብርተኛ ቀርቶ ለውጭ ወራሪ ሀይል የተንበረከከ አይደለም
የተቃጣብንን ወረራ የአፋር ክልላዊ መንግስት እና ህዝብ በአንድ ክንድ እንመክተዋለን ” …
. ህወሃቶች በሪሞት ኮንትሮል እኛን የመምራት እድል ሲያጡ ዛሬ በመሳሪያ ለመምራት ፈለጉ  እኛ አፋሮች በፍቅር እንጂ በመሳሪያ የምንበረከክ አይደለንም። እነሱም ፍቅር አያውቁም እኛም ከመሳሪያ አንፈራምም ለመሳሪያም አንበረከክም።
አንድ ክልል ከእኛ በምንም የማይሻል ክልል እንደ ፌዴራል መንግስት ሁኜ እናንተን እመራለሁ ብሎ ከማሰብ በላይ ሞኝነት የለም።
 ኢትዮጵያ ማለት 9 ክፍሎችና አንድ ሳሎን ያለው ቤት እንደ ማለት ነው። ሳሎን ቤቱ የፌዴራል መንግስት ስሆን 9ኙ ክፍል ደግሞ የክልል መንግስታትና ህዝቦች ናቸው። አንድ ክፍል ከተቃጠለ ሁሉም ክፍሎች ይቃጠላሉ። በሌላ ምሳሌ ደግሞ ኢትዮጵያ ማለት እንደ አንድ ሰው ማለት ነው። ከሰውነታችን አንዱ ጣት ወይም አይናችን ከታመመ እንቅልፍ እንደምነሳን ሁሉ ከኢትዮጵያ የአንድ ክልል ጉዳት የሁላችንም ኢትዮጵያዊያን ጉዳት ነው።
በዚህ አለም ላይ በጣም የምንሳሳለትን ህይወታችንን እያጠፉ የክብራችን አለኝታ የሆነችውን ባንድራችንን እያቃጠሉ እኛ ለእናንተ ነፃነትም ነው የምንታገለው ማለት ምን አይነት ሞኝነት ነው? ለዚህ ድርጊታቸው ደግሞ ዋጋ ይከፍላሉ።
 አፋሮች ታንክን የምያህል መሳሪያ በእጅ ሲይዙ የነበሩ ህዝቦች ናቸው እንጂ ዛሬ ላይ የጁንታ ፊሪፋሪዎች የምዳፈሯቸው ህዝቦች አይደሉም። ድንበራችንን ለማስጠበቅ የማንንም እርዳታና ድጋፍ አያስፈልገንም።
 አፋሮች አንድ አባባል አላቸው “ልትሞት ያሰበች አይጥ የድመት አፍንጫ ታሻታለች” ዛሬ ላይ የህወሃት ጁንታ አካሄድም ያንን አባባል ያስታውሰኛል።
 ጦርነት ምርጫ ተደርጎ የሚመረጥ ምርጫ አይደለም።
የጦርነቱ ጉዳቱ ለአጥቂም ለተከላካይም ጭምር ለሁሉም ጉዳት ነው። አፋር ጦርነቱ ምርጫችን አይደለም ማለቱም ልክ ነው። ከራሱ ግዛት አልፎም
የተነኮለም የለውም። መጡብን እንጂ አልሄድንባቸውም። ህወሃት ሰላም የሚወድ አለመሆኑ በአፋር ግዛት የእርሱን ተልዕኮ እና ሰላም ለማደፍረስ ያደረገው ሙከራ የእኔ ቤት ተቃጥለዋል አንተም ልትቃጠል ይገባል ስል ትግራይን እንዳቃጠለ የአፋር ህዝብ የጦርነት ሰለባ ተጎጂ ለማድረግ ያሴሬው እቅድ አጋርነትን ለማገኘት ነበር። አልቀረም በወራራቸው ቦታዎች ንፁሃኑን የአፋር
አርብቶአደሮች ገድለዋል። በርካቶች ከቤት ንብረታቸው እንዲፈናቀሉ
አድርገዋል።
ቢሆንም ህወሃት የፈለገው አልሆነም አልተሳካለትም በእብሪት ከያዛቸው ቦታዎች ምንም የማያውቁ ህፃናት ለጦርነት ሰለባ እያደረገ ተዋርዶ ከአፋር ክልል ግዛት በውርደት ተከናንቦ አላማው ከሽፎበት ወደመጣበት እየፈረጠጠ ይገኛል ።
ህወሃት የአፋርን ግዛትን በጉልበት በመያዝ የመግቢያ መውጪያ መፈንዘጫ መንገድ ለመክፈት ለሴራው ያወጣኛል ያለው እኩዬ አላማ ለስፈፀሚያ ስልቶች ማለትም ጦርነቱን የትግራይ እና የአፋር ለማድረግ የህዝብ ግጭት ለማስነሳት እንዲሁም አፋርን በጎሳ፣ በዞን ከፋፍሎ የአፋር ህዝብ አሰብ ፣ ጁቡቲ አስመልስለሃለሁ በማለት ለአላማው የአፋር ማህበረሰብ ተሳትፎ ለራሱ ማጠቀሚያ ለማድረግ አፋርን ከጎኑ አሳልፎ በአፋር ምድር ልክ እንደትግራይ
ግዛት የሸብር ማስፈፀሚያ ግዛት ለማገኘትና የጥፋት ህሊውና ለማራዘም አልፎም አፋርን በሐሰት በውሽት ላም አለኝ በሰማይ ድሮ ራሱ አሰልፎ የሰጣው
የአሰብ ወደብ አስመልሳለሁ እያለ ከእውነት የራቀ ፕሮፓገንዳ እየነዛ በአቋራጭ የኢትዮ – ጁቡቲ መንገድ ድረስ ወሮ መንገዱን ለመቆጣጠርና ለመዝጋት ያቀደው ሴራ የአፋር ህዝብ ሁለቴ የሚታለል ህዝብ ባለመሆኑ ሴራው ከሽፎበት
ወደመጣበት ሳይወድ በግዱ ከወጣት እስከ ሽማግሌ ታጥቆ አይቀጡ ቅጣት እየቀጣው ሐሳዊ እቅዱን ነቅቶበት ወደመግዛቱ እንዲመለስ ጥሩ መስተንግዶ እያደረገለት እየመለሰው ይገኛል። ልብ ካለው ልቡን ይገዛል!!
Filed in: Amharic