ነጋሪት ሚድያ
‹‹ጓዶች እንደ ድርጅት ያጋጠመንን ሽንፈት ለትውልዱና ለሕዝቡ እያከፋፈልን ነው፡፡ እውነቱን መጋፈጥ አለብን፡፡ ሕዝባችን በሚያሸነፍበት ፈንታ የሚሞትበትን ጦርነት ደግሰን እየማገድነው ነው፡፡ በእኛም ልብ ውስጥ ያለው አሸናፊነት ሳይሆን አልሸነፍ ባይነት ነው፡፡ ይህ ደግሞ የሚያዋጣ አይደለም፡፡ አሁን ያለን አማራጭ ሁለት ነው፡፡ አንድም እንደ ድርጅት ያጋጠመንን መራር ጽዋ መቀበል ወይም ደግሞ ሽንፈታችንን ማከፋፈል፡፡ ጓዶች ለክልላችን እና ለሕዝባችን አስበን የገባንበትን ውጊያ ባሁኑ ሰዓት ለእራሳችን ህልውና ማስከበሪያ አድርገን ወጣትና ወንድ አልባ ክልል እየፈጠርን ነው፡፡ የወልቃይት እና የራያ መሬት ላይ ትውልዱን እየቀበርነው ነው፡፡ ስለሆነም ከዚህ በኋላ በፕሮፖጋንዳ የተሸፋፈነ የአልሞት ባይ ተጋዳይ ትግላችንን ጋብ አድርገን ወደ ድርድር በመግባት የጀመርነውን ሕዝብ የመቅበር ተግባር ማቆም ይገባናል፡፡ በዚህ ሐሳቤ መስማማትም ሆነ አለመስማማት ትችላላችሁ፡፡ በበኩሌ ግን የምሞትለትን ሕዝብ ይሄን ያህል ካስገደልኩት ይበቃኛል ብያለሁ፡፡”