>

ሰበር ሰሚ ችሎቱ በእነ እስክንድር ነጋ ዶሴ ላይ ለነሐሴ 10 ቀን 2013 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ.... (ጌጥዬ ያለው)

ሰበር ሰሚ ችሎቱ በእነ እስክንድር ነጋ ዶሴ ላይ ለነሐሴ 10 ቀን 2013 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ….
ጌጥዬ ያለው
 

*…. ከዚህ ቀደም ከወራት በፊት በተደረጉ ክርክሮች ከፊሎቹን ካሉበት ወህኒ ቤት ውስጥ ሆነው በፕላዝማ ቴሌቪዥን ቀርበው ተከራክረዋል። ከሰሞኑ እየተደረጉ ባሉ ክርክሮች ደግሞ ፈፅሞ እንዳይቀርቡ ተደርጓል። በዚህም እነ እስክንድር ለችሎቱ ማስረዳት የሚገቧቸውን ጉዳዮች እንዳይናገሩ ታፍነዋል። እማኞች በግልፅ ችሎት ወይም በዝግና ከመጋረጃ ጀርባ እንዲመሰክሩ ይፈርዳል የተባለው ችሎት ራ፤ ራሱን ደብቆ እየፈረደ ይመስላል!
 
የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በእነ እስክንድር ነጋ መዝገብ ላይ ተለዋጭ ቀጠሮ የሰጠው ‘የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ከመጋረጃ ጀርባና በዝግ ችሎት ይቅረቡ ወይስ በግልፅ ችሎት ይሰሙ’ ለሚለው ክርክር ብይን ለመስጠት ነው። ትናንት ነሐሴ 3 ቀን 2013 ዓ.ም. በነበረው ችሎት መዝገቡን አለመመርመሩን ጠቅሶ ለዛሬ ነሐሴ 4 ቀን 2013 ዓ.ም. ማሸጋገሩ ይታወሳል።
ይህንኑ የምስክሮች አሰማም ሂደት በተመለከተ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጸረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት እና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በግልፅ እንዲ መሰክሩ ከዚህ በፊት መፍረዳቸው አይዘነጋም። የዛሬውን ችሎት የመራው ሰበር ሰሚ ችሎትም ጉዳዩ ከዚህ በፊትም የቀረበለት ሲሆን ራሱ ከፍተኛው ፍርድ ቤት እንዲወስን መልሶ ወደ ታችኛው የፍርድ ቤት ርከን መላኩ ይታወሳል። የእስር ፍርድ ቤቱ በበኩሉ በጠቅላይ ፍርድ ቤት አጋጅነት ያቋረጠውን የምስክሮች አሰማም ሂደት ለመቀጠል ለሚቀጥለው ዓመት ማለትም ለጥቅምት 4 ቀን 2014 ዓ.ም. ተለጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
በተለያዩ ጊዜያት በጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተካሄዱ ባሉ ክርክሮች የኅሊና እስረኞች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም እና አስካለ ደምሌ በአካል ቀርበው አያውቁም። ከዚህ ቀደም ከወራት በፊት በተደረጉ ክርክሮች ከፊሎቹን ካሉበት ወህኒ ቤት ውስጥ ሆነው በፕላዝማ ቴሌቪዥን ቀርበው ተከራክረዋል። ከሰሞኑ እየተደረጉ ባሉ ክርክሮች ደግሞ ፈፅሞ እንዳይቀርቡ ተደርጓል። በዚህም እነ እስክንድር ለችሎቱ ማስረዳት የሚገቧቸውን ጉዳዮች እንዳይናገሩ ታፍነዋል። እማኞች በግልፅ ችሎት ወይም በዝግና ከመጋረጃ ጀርባ እንዲመሰክሩ ይፈርዳል የተባለው ችሎት ራ፤ ራሱን ደብቆ እየፈረደ ይመስላል። ምክንያቱም በእነዚህ ችሎቶች ታዳሚያን የሉም፣ ጋዜጠኞች የሉም፣ ራሳቸው ተከሳሾች የሉም፣ ለወትሮው የሚታደሙ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና ሌሎች ግለሰቦችና ድርጅቶች የሉም። ጉዳዩ የደብዳቤ ልውውጥ ሆኗል።
Filed in: Amharic