>

በእስር ላይ በሚገኙት 3 ጋዜጠኞች ላይ ለአራተኛ ጊዜ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ለፖሊስ ተፈቀደ...!!! ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

በእስር ላይ በሚገኙት 3 ጋዜጠኞች ላይ ለአራተኛ ጊዜ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ለፖሊስ ተፈቀደ…!!!
ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

የአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ፍርድ ቤት፤ በአፋር ክልል አዋሽ ሰባት ኪሎ ከተማ በእስር ላይ በሚገኙ ሶስት ጋዜጠኞች ላይ ለአራተኛ ጊዜ የምርመራ ጊዜ ፈቀደ። ፍርድ ቤቱ የምርመራ ጊዜውን የፈቀደው የአውሎ ሚዲያ ዋና አዘጋጅ በሆነው በቃሉ አላምረው፣ በሚዲያው ላይ በተንታኝነት በሚሳተፈው ፋኑኤል ክንፉ እንዲሁም የ“ኢትዮ ፎረም” ጋዜጠኛ በሆነው አበበ ባዩ ላይ ነው።
የወረዳው ፍርድ ቤት ለዛሬ ነሐሴ 6፤ 2013 ቀጥሮ የነበረው፤ ፖሊስ ባለፈው ችሎት በተፈቀደለት አስር የምርመራ ቀናት ያከናወናቸውን ተግባራት ለመስማት ነበር። ነገር ግን ፖሊስ “ምርመራዬን አላጠናቀቅኩም” በማለቱ ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ አራት የምርመራ ቀናት መፍቀዱን የጋዜጠኞቹ ጠበቃ አቶ ታደለ ገብረመድሀን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳደር” ተናግረዋል።
በዛሬው የችሎት ውሎ ከሶስቱ ጋዜጠኞች ጋር አብሮ ፍርድ ቤት በቀረበው አክቲቪስት ጸጋዘአብ ኪዳኔ ላይም፤ ፖሊስ ተመሳሳይ የምርመራ ቀናት እንደተፈቀደለት ጠበቃው አስረድተዋል። አራቱም ተጠርጣሪዎች በዛሬው ችሎት ለፍርድ ቤቱ የዋስትና ጥያቄ ቢያቀርቡም ውድቅ መደረጉንም ጨምረው ገልጸዋል።
ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2021/4197/
Filed in: Amharic