ሰለሞን አለምነህ
እነ እስክንድር ነጋን ቂሊንጦ አጉረህ ~ ኦነጋዊያን ቤተ መንግስት ሰብስበህ “ዲሞክራሲ ዲሞክራሲ ” ብትል ስላቅ ነው! ታላቅ ስላቅ!!!
አንተ የምትታገልላትን ታሪክ ጠገብ #ኢትዮጲያ ሳይሆን አፈ-ጮሌው አፍርሶ ሊሰራት ያሰባትን አዲስቷ-ኢትዮጲያ (ምናባዊቷ-ኦሮሚያ) ለመቀበል የተዘጋጀው ህዝብ የታሪክ ተጠያቂ ነው !! አንተ #እስክንድር_ነጋ ሆይ ፦ ታሪክን፣ እውነትን፣ ህዝብን ከምንም በላይ ፈጣሪን ይዘህ የምታተገለው መሪየ ዛሬ ላይ የበሻሻው እና ግብረ አበሮቹ ባለ ጊዜ ሁነው ያሻቸውን እያደረጉ ነው ! ግድ የለም ከፈጣሪ በታች የቀን እንጅ የሰው ጅግና የለውም ።
አንተ በግፍ በቂሊንጦ ያለ #ፍትሕ ታጉረህ ነገር ግን ንፁህ ህሊናህን ይዘህ የሰላም እንቅልፍ ትተኛለህ ። አቦይ ስብሓትን በቃሊቲ ያገኘኸው ዕለት ስለአቦይ ስብሓት ” #ድል_ለዲሞክራሲ ” በሚለው መፅሓፍህ አጫውተኸን እንደተኛው የሰላም እንቅልፍ ! ( እሱንም ስለሀገረ ከማሰብ አቁመህ ከተኛህ ነው ) ! #ተረኞቹ ግን ፈጣሪ ሁሉን ያያል እና ቀን ከሌት የሰሩት ግፍ እና ወንጀል አላስተኛቸው ብሎ ይቅበዘበዛሉ ። ስልጣኔን እንዳላጣ በሚል የደሀን ልጅ እንደ ማገዶ ይማግዳሉ !
ዛሬ ላይ ታንኩም ባንኩም ሳክሱም በእጅህ ሆኖ ባየህ ጊዜ የልብ ልብ ተሰምቶህ በአዳነች አበቤ ፣ በሽመልስ አብዲሳ እና በአሻዲሊ ሀሰን ምኞችህን ብታስፈፅምም ( ይሄን መቼም አትርሳ ትላንት ሕውሓትንም ስንጥላት እንዳንተው ነበረች ) ።
የበሻሻው ፤ ተረኛው ፤ ጦረኛው እና አምባገነኑ አብይ አህመድ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጅ ለፍርድ መቅረብህ አይቀሬ ነው ! አንተ እና ግብረ አበሮቹን ሀገሬ #ኢትዮጲያ መቼ አሽቀንጥራ መጣል እንዳለባት ታውቃለች እስከዚያም እኛ ልጆቿ እንታገልሀላን ! የልብ ልብ አይሰማህ የስራህን ታገኛለህ እና የጊዜ ጉዳይ ነው ! 《ከፈጣሪን ፍርድ እንጠብቃለን》
እነ እስክንድር ነጋን ፍታ !
ድል ለዲሞክራሲ
Attachments area