>

ሚስጥራዊው የጁንታው ናፋቂ ስብስብ በአዲስ አበባ! (አርአያ ተስፋማርያም)

ሚስጥራዊው የጁንታው ናፋቂ ስብስብ በአዲስ አበባ!

አርአያ ተስፋማርያም

1.አብዲፋታህ ሞአሊን የቀድሞ የአብዲኢሌ ምክትልና የጁንታው አባይ ጸሃዬ የቅርብ ሰው
2.አብዲላሁ የሱፍ ዌረር /አብዱላሂ ኢትዮጵያ የአብዲ ኢሌ የጸጥታ ሃላፊ
3. አብዲ ሬይስ የአብዲ ኢሌ የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ
እነዚህ ሶስት ሰዎች ለአንድ አላማ አዲስ አበባ  ላይ ከመሸጉ ወራትን አስቆጥረዋል፡፡ ለውጡ አንጓሎ የተፋቸውን፣ በሙስና እና በብልሹ አሰራር ከስልጣን የተነሱ፣ የድሮ ስርአት ተጠቃሚ የነበሩ እና ለውጥ መምጣቱ ጥቅማቸውን የነካባቸውን በመሰብሰብም ህወሃት ወደ ስልጣን ሲመለስ ሽግግር መንግስት በማቋቋም ስልጣን እንይዛለን ሲሉም ለሰበሰቧቸው  ጭፍሮቻቸው ቃል መግባት ሲጀምሩ ነበር ውስጥ ካለ የራሳቸው ሰው መረጃው መውጣት የጀመረው፡፡
የጁንታው አባይ ጸሃዬ እና የገዳዩ ጌታቸው አሰፋ የቅርብ ሰው አብዲፋታህ ሞአሊን እንዲሁም የሶማሌ ክልል ህዝብን ህፃን አዋቂ ሳይል ከነብር እና ጅብ ጋ ሲያስር የነበረው አብዲላሁ የሱፍ ዌረር /አብዱላሂ ኢትዮጵያ/ በሚስጥራዊ ስብሰባቸው ላይ በድፍረት የሽግግር መንግስት አቋቁመን ሀገር ለመምራት ተዘጋጅተናል ማለታቸውም በሚስጥራዊው ስብሰባ ላይ የተገኘው የመረጃ ምንጭ ይጠቁማል፡፡
እነዚህ ከላይ ስማቸው የሰፈረው ከ ወያኔ ጁንታ ጦር ጀነራሎች ጋር ቅርበት ብቻ ሳይሆን የሶማሌን ህዝብ በጁንታው ሲያስጨፈጭፉ እና ሲያስገድሉ የነበሩ አካላት ለሰሩት ጥፋት መጠየቅ ሲገባቸው ዛሬ ላይ በድፍረት የሽግግር መንግስት እናቋቁማለን በማለት በሶማሌ ክልል የተለያዩ ግጭቶችን ለመቀስቀስ እየሰሩ ነው ያሉት ምንጮች በአዲስ አበባ ከተማ የክልሉን መንግስት የሚቃወም ስብሰባ እናዘጋጃለን በሚል በማህበራዊ ድረገፅ ጥሪ ማድረጋቸውም ታውቋል፡፡
ይህ ሁሉ ሀገር የማፍረስ አንቅስቃሴ ደግሞ የሚሸረበው እና የሚጎነጎነው የፌደራል መንግስቱ መቀመጫ በሆነችው አዲስ አበባ  ከተማ ላይ መሆኑ የፌደራል መንግስቱ እና የከተማ አስተዳደሩ ምን እየሰሩ ነው? የሚል ጥያቄን በክልሉ ነዋሪ እና ፖለቲከኞች ዘንድ እንዲጫር ከማድረጉ ባሻገር በመንግስት መዋቅር ውስጥ ያሉ እዳንድ አካላት በህቡዕ ለነዚህ  ተላላኪዎች ድጋፍ እየሰጡ እና ሁኔታዎችን እያመቻቹ እንደሆነ የሚያመላክቱ መረጃዎች እየወጡ መሆኑ በክልሉ መነጋገሪያ ጉዳይ ሆኗል፡፡
ምንጭ:- (አብዲጀባር ዩሱፍ የላኩልን ጥቆማ)
Filed in: Amharic