አቢይ ሕውሐት እና ኦነግ
ከሲናጋ አበበ
በትግራይ በተከሰተው አገር የመበተን ሴራ የትግራይ ሕዝብ በተረጋጋ መንፈስ ኑሮውን እንዲያሸንፍ በማሰብ መንግሥት የተናጠል የተኩስ ማቆም እርምጃ ቢወስድም ሕዝቡ የዚህ ተግባር ተጠቃሚ የሚሆነው ገበሬ ክረምቱ ሳይወጣ እርሻውን እንዳያከነውን ታስቦ ቢሆንም ሕውሐት መላ ትግራይን ወሮ ዳር እስከ ዳር ሕዝቡን ሕጻናትን ሳይቀር ለጦርነት እያሰለጠነና እየማገደ፤ ከውጭ የሚጎርፈውን የእህል እርዳታ እንደመያዣ በመጠቀም አንድ ግለሰብ የእለት ጉርሱን እሱና ቤተሰቦቹ እንዲያገኙ ከፈለጉ ሳይወዱ በግድ በዘመቻው እንዲሳተፍ ይፈርድበታል፡፡ ትግራይን በመላ ከተቆጣጠረ በሁዋላ የዘመቻውን አድማስ በማስፋት ወደ ጎንደር፤ ወሎ እና አፋር በማስፋት ሕዝቡት ለመከራ እየዳረገ ይገኛል፡፡
ወያኔ በወሎ የተለያዩ ወረዳዎች የከፈተውን ዘመቻ ለመመከት በየሰፍራው ከመሀል አገር ጭምር የዘመቱ የጦርነቱን አስከፊነት ከዚህ በታች በሥፍራው ተገኝቶ ከተመለስ አገር ወዳድ የተዘገበው ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቡዋል፡፡
አርቲስት ዱባለ የተባለ ታዋቂ የዘፈን አቀንቃኝ ያገሩ ጉዳይ አንገብግቦት ወደ ወሎ ዘምቶ ጁንታው በወሎ የተለያዩ ወረዳዎች ላይ ዘምቶ ሕዝቡን እያፈናቀለ፤ ቤት እያቃጠለ፤ ንብረት እየዘረፈ መሆኑን መመልከቱን ሲናገር መስማቱ የሚዘገንን ነው፡፡ የሚገርመው ግን ወያኔን ለመመከት ወጣቱ በፈቃደኛነት ሥለጠና ወስዶ ከመንግሥት መሣሪያ ሊሰጠው ባለመቻሉ እጁን አጣጥፎ እንዲቀመጥ መደረጉ በመንግሥት በኩል የሚካሄድ ደባ እንዳለ ጠርጥሮዋል፡፡ የወሎ ሕዝብ ባለው መሣሪያ ሊቁዋቁም ቢሞክርም ከበላይ የመጣ ትእዛዝ ስለሆነ ማፈግፈግ እንዲያደርግ በመወሰኑ ጁንታው በየወረዳው እንደልቡ እንዲፈነጭ ፈቅደውለታል፡፡ ይሕ ሲሆን የአገር መከላከያ ሀይል ተብዬው ከቅርብ ሩቅ ሆኖ በሕዝብ ላይ የሚደርሰውን ጭፍጨፋ ይመለከታል፡፡ ድንበር ተሸግሮ ሕዝብን ለከፋ ችግር ለሚዳርግ አሸባሪ ቡድን አጸፋውን እንዲከፍል ማድረግ ሲገባው የመከላከያ ክፍላችን እጁን አጣጥፎ ከመቀመጥ ባሻገር በማፍገፈግ እሳቤ ትላልቅ መሣሪያዎችን ይዞ እንደመሄድ እንዳሉ ለጠላት ትቶ መሄድ በወታደሩ ዓለም የተለመደ አሠራር አይደለም፡፡ ይሕ የሚያመለክው መንግሥት የተለየ ዓላማ ያነገበ መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡
በወሎ አስቀድሞ ሥልጠና የተደረገላቸው ወጣቶች መሣሪያ የለም ተብለው በእጃቸው በተገኙ ቁሳቁሶች እንዲከላከሉ ተፈርዶባቸዋል፡፡ መንግሥት በዚህ መልኩ የሚንቀሳቀስ ከሆነ በአዲስ አበባና በአማራው ክልል እንደጎርፍ ተነሳስቶ ለመሰልጠን በተመዘገበት ሁኔታ መሣሪያ የሚሰጠው ካልሆነ ስልጠናው የይስሙላ መሆኑን ያመላክታል፡፡
አርቲስት ዱባለ በወሎ የተለያ ሥፍራዎች በመገኘትና በጦርነቱ በመሳተፍ እንደተመለከተው መንግሥት ተስፋ የሚጣልበት እንዳለሆነና ግንበር ቀደም ተጠቂው አማራው እራሱን አደራጅቶ ሕልወናውን ማስጠበቅ ሊይዘው የሚገባ ብቸኛ አማራጭ ነው ሲል በይፋ ለሕዝብ ገልጡዋል፡፡
እንደሚታየው ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይና የሱ የኦሮሙማ ፖለቲካ አራማጆች ዞሮ ዞሮ አማራው መብቱን ቢያስከብር ለወደፊቱ የነሱን ኦሮሙማ ራዕይ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚቸገሩ በመገመት፤ አማራውን ለመኮላሸት የተጠነሰሰ እርምጃ ለመሆኑ የፖለቲካ ተንታኞች አቁዋም እንደሆነ መረዳት ይቻላል፡፡ አሸባሪው ወያኔ ወሎ ገብቶ ወደ ላሊበላ ሲያቀና እጀግ የተደነቁ የዓለም ቅርስ የሆኑ ንዋዮችን አውላላ ሜዳ ላይ ጥሎ ምስኪን የሆነችውን የላሊበላ አውሮፕላን ማረፊያ ለመጠበቅ የመከላከያ ሀይሉ ተንቀሳቅሶ መረፊያውን ከቦ መቀመጡ ምን ዓይነት ፖለቲካዊ ውሳኔ ነው፡፡ ትልቁን ዳቦ ትቶ ለእንጎቻ እንደመሮጥ ይቆጠራል፡፡ ይህ በመንግሥትና በታዛዡ መከላከያ ሀይል የተሸረበው ደባ አገሪቱን እጅግ ከፍ ያለ ዋጋ የሚያስከፍላት መሆኑ በጉልህ ይታያል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመልካም አንደበቱ ለአገሪቱ ከማንም በላይ ተቆርቁዋሪ መስሎ መታየቱ ከንግግሮቹ በስተጀርባ ግን፤
1ኛ. የኦሮሙማን ምሥረታ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚጥር፤
2ኛ .የስልጣን ጥማቱ ከምንም በላይ ስለሆነ፤ ወንበሩን ላለማጣት ተቀናቃኞቹንና ለኢትዮጵያ አንድነት፤ ለእኩልነት፤ ለፍትህ እና ለዴሞክራሲ ሽንጣቸውን ገትረው ከሚሙዋገቱና ከሚከላከሉ ኃይሎች ጋር አብሮ መራመድ በእጅጉ ይከብደዋል፡፡
በኢትዮጵያ የዘውግ ፖለቲካ አማራው ለኦሮሞው ብቸኛ ተወዳዳሪ፤ ተቀናቃኝ ኃይል በመሆኑ ደካማ ታዛዥና የኦሮሙማን ጽንሰ ሃሳብ አራማጅ እንጂ ሀቀኞችንና ለኢትዮጵያ እና ለሕዝቡዋ በእኩልነት ገናና ኢትዮጵያን ለመፍጠር ለሚቆሙ መወገን ምኞቱም ዓላማውም የላቸውም፡፡
ከጥቂት ቀናት በፊት አሸባሪው ሐይል በከባድ መሣሪያ ተጠቅሞ አቅመ ደካማ አዛውንቶችን፤ሴቶችንና ሐጻናትን በተጠለሉበት ቦታ ላይ አነጣጥሮ በመተኮስ ከ200 በላይ ሰዎች ጨፍጭፎዋል፡፡ የዓለም መገናኛ ብዙሃንም ሆነ የኢትዮጵያ መንግሥት ዝምታን መርጠዋል፡፡ በዚህ አሰቃቂ ድብደባ ከ30 ሺህ ኩንታል በላይ የሚገመት እህል ወድሙም ተዘግቡዋል፡፡ በዚህ አሸባሪ ቡድን ትንኮሳ የተባባሰው ግጭት የሚፈናቀለው የአማራ ሕዝብ ብዛት በየቀኑ እያሻቀበ ይገኛል፡፡ ሠላማዊ ሕዝብ ከየቀን ተግባሩ ተገልሎ ለዘመናት ከዋለባቸው ሠላማዊ ኑሮ እንዲፈናቀል ሆኖ በየመጠለያ ጣቢያዎች እንዲከትምና አገር አልባ እንዲሆን ሲፈረድበት ፤ ሲከፍል የኖረው ዓመታዊ ታክስ ደህንነቱን ሊያስጠበቅለት የተቀጠረው የመከላከያ ኃይል ከአገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በተሰበሰበ ሰንጋና ሙክት በግና ፈየል ጮማውን እየቆረጠ ግፉን ከቅርብ እሩቅ ሆኖ ይመለከታል፡፡
ይብላኝልሽ አገሬ አቢይ የኦሮሙማው ንጉስ ይዞሽ መቀመቅ እየወረደ ስለመሆኑ ማን በነገረሽ ! ጆሮ ያለው ሰምቶ የበኩሉን ለናት አገሩ በሚቻለው አስተዋጽዎ ያድርግ፡፡ ይኸው ነው፡፡