>

የትግራይ ዲያስፖራ የሳይበር ቡድን ሻጥሮች እና ሴራዎች ተጋለጡ...!!! (ደጀኔ አሰፋ)

የትግራይ ዲያስፖራ የሳይበር ቡድን ሻጥሮች እና ሴራዎች ተጋለጡ…!!!

ደጀኔ አሰፋ

የትግራይ ዲያስፖራ የሳይበር ቡድን (Diaspora Cyber Team) ዛሬ (Sep5 western time)ስብሰባ ነበራቸው። የእኛ ሰዎችም የሳይበር ውይይታቸውን ሰብረው በመግባት ታድመው ወጥተዋል
አጀንዳዎቹ:-
1• አለም አቀፍ ጫናዎችን በድጋሜ በአዲስ መልክ እንዴት እንፍጠር?
2 ትግራይ ውስጥ ቤተሰቦቻችን በርሃብ እያለቁ ነው:: ለዚህስ መፍትሄው ምንድነው?
3 ህወሓት/የትግራይ መንግስት ምን ማድረግ አለበት? የሚሉ ናቸው::
የተስማሙባቸው ነጥቦች:-
1ኛ). ጦርነቱ ትግራይ መሬት ላይ በነበረበት ወቅት ተዘረፍን ፣ ሴቶች ተደፈሩ ፣ በጅምላ ተገደልን … ብለን የአለም አቀፍ መንግስታት ጫና እንዲፈጥሩ አድርገናል:: አሁን ያንን መንገድ መከተል አዋጭ ስላልሆነ 5.2 ሚሊዮን ህዝብ በርሃብ እየተጎዳና እየሞተ እንደሆነ ፣ ወደ ትግራይ እየገባ ያለው የእርዳታ እህልም እጅግ አነስተኛ እንደሆነ ፣ አንድ ሰው የሚመግብ እህል ለአስር ሰው እየተከፋፈለ እንደሆነና እጅግ አስከፊ ርሃብ እንደተከሰተ አድርገን ለአለም እንጩህ:: አጋሮቻችንንም በማንቃት ጫና እንፍጠር::
2ኛ). ይህን ከፈጠርን በሗላ የሱዳን መንግስት ጋር በመነጋገር እና የሱዳን መንግስትም ከድሮው በተሻለ  ተፅኖ እንዲፈጥር  በማድረግ እርዳታዎች  በሱዳን በኩል ሊገቡ የሚችሉበትን አማራጭ እስከቻልነው (to the maximum) መሞከር::
3ኛ). የሱዳን መንግስት አሁን ላይ በሚፈለገው መጠን ኢትዮጵያ ላይ ተፅኖ እየፈጠረ ስላልሆነ በተሻለ አግባብ የሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ የህወሃት ወኪሎች በድጋሜ እንዲወያዩ ማድረግ::
4ኛ) ህወሓት ማርኮ ያስቀመጣቸው ወታደሮች ላይ እርምጃ ይውሰድ / በተጠና አግባብ / then አሁን የትግራይ ሃይልን እያጠቃ ያለው መከላከያ ላይ  መሸማቀቅና ፍርሃት ይፈጠራል ብለዋል።
  
በማጠቃለያቸውም:-
•የፕሮፖጋንዳ ብልጫ በኢትዮጵያውያን የሳይበር ቡድን cyber team እየተወሰደብን ስለሆነ እሱን መቀልበስና አለም ፊቱን ወደ ትግራይ ጉዳይ በድጋሜ እንዲያዞር እናደርጋለን።
•ዘመቻው የሚጀመርበት ጊዜና አጀንዳዎች በቅርብ ይፋ ይደረጋሉ።
•ሃገር ቤት ካሉ አካላት ጋር በመነጋገር ተጨማሪ ሃሳቦች ይመጣሉ ብለዋል።
ትዝብት:-
➢በአብዛኛው ተሰብሳቢ ቤተሰቦቻችን በርሃብ እያለቁ ነው ፣ ሱዳን በሚገባ አልረዳችንም ፣ ወጣቱ እና ህፃናቱ በጦርነት እያለቀ ነው ፣ ህወሓት መፍትሄ ማምጣት አለበት … ወዘተ በማለት ሲያለቃቅሱ ነው የዋሉት::  በብዙዎቹ ላይ ተስፋ መቁረጥ ይታያል:: ብዙ ወቀሳዎች ነበሩበት!!!!
➢”ትግሉ ምድር ላይ ያለው ጦርነት ብቻ ስላይደለ የኢትዮጵያ Cyber team ልንበረታ ይገባል” ብለዋል ውይይቱን ሰብረው የታደሙ ኢትዮጵያውያን::
በመሆኑም እነዚህ ከላይ የተጠቀሱትን ሻጥሮች እና ሴራዎች ከወዲሁ ተደራጅቶ ማጋለጥ ከሁሉም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የሚጠበቅ ብሔራዊ ግዴታ ይሆናል!!!! ኢትዮጵያውያን በሳይበር ብልጫ እየወሰዱ መሆናቸው አበረታች ቢሆንም አሁንም የተቀናጀ የሳይበር ውጊያ እስከመጨረሻው ማካሄድ የግድ ነው!!!! እውነት ያሸንፋል!!!!! ኢትዮጵያ ታሸንፋለች!! via፦ Dejene Assefa
Filed in: Amharic