>

ትንታጔ ጋዜጠኛ መዓዛመሀመድ...!!! (ወንድወሰን ተክሉ)

ትንታጔ ጋዜጠኛ መዓዛመሀመድ…!!!

ወንድወሰን ተክሉ

የትንታጔ ጋዜጠኛ Meaza Mohammed   እና የስራ ባልደረባዋ ወጣቱ ጋዜጠኛ ቴውድሮስ ከ Abbay Media መባረር የሚያሳየን ሁለት መሰረታዊ እውነታዎችን ነው።
፠ አንደኛው እውነት ፦ አፍቃሬ መንግስት ባለመሆን በአንጻሩም ነጻ ገለልተኛና የእውነት መስተጋቢያ መድረክ መስሎን የነበረው አባይ ሚዲያ እንዳሰብነው ነጻ ገለልተኛ ያለመሆኑንና በአንጻሩም ሚዲያው  የመንግስትን የልብ ትርታን እያዳመጠ መንግስትን በሚያስደስት የአሰራር መርህ መሰረት የሚጔዝ አፍቃሬ ብልጽግና መሆኑን ያረጋገጠልን ሲሆን ተቌሙ ቀደም ብሎ የሁለቱን ጋዜጠኞችን እና መሰል የሆኑትን ነጻ ሀሳቦችን ያንሸራሸረበት ምክንያት ነጻና ገለልተኛ መስሎ የአድማጮችን እይታ ለመሳብ ሲል ያደረገው መሆኑን እንረዳለን።
፠ ሁለተኛው እውነታ፦ የአማራዊያን ሀቅና እውነት ምን ያህል ዋጋ እንደሚያስከፍል ያረጋገጠልን ከመሆኑም በላይ ይህ ጸረ አማራዊ መዋቅርና ኔትዎርክ ምን ያህል ትስስራዊ ድሮቹን አስፍቶ የዘረጋ መሆኑንም ጭምር ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል።
ጋዜጠኛ መዓዛ መሀመድ በአዲሱ ዓመት ከአዲስ ስራጋር ለመቅረብ በዝግጅት ላይ እንዳለች አውቃለሁ።  ሙያዊ ነጻነቷን አስጠብቃ በነጻነት በምትሰራበት በዚህ አዲሱ ፕሮግራሟ ከዚህ በፊት ስታቀርብልን ከነበረው አገልግሎት በተሻለ ሁኔታ ይዛልን እንደምትቀርብ እምነት አለኝ።
አስረስ ማረ ዳምጤ   ስለመዓዚ እንደሚከተለው ጽፏል።
ጋዜጠኛ እና መምህርት Meaza Mohammed ባለፉት ሁለት ዓመታት ድፍረትን ጭምር በሚጠይቀው የኢትዮጵያ የጋዜጠኝነት ሙያ ውስጥ ከሻሸመኔ እስከ መተከል፣ ከአጣየ እስከ ከማይካድራ፣ ከዶዶላ እስከ አጋርፋ በሁሉም ማዕዘናት ላበረከትሽው ትልቅ አስተዋፅኦ ምስጋና ይገባሻል። እናትነት፣ ሴትነት እና የቤተሰብ ኃላፊነት ያለውን ጫና ተቋቁመሽ በተለይም ከክልል ውጭ ፍዳን እየተቀበለ ላለው አማራ ድምፅ በመሆን ያበረከትሽውን አስተዋፅኦ አንረሳውም። መጪው ዓመት የበለጠ የምትሰሪበት እንዲሆን እመኛለሁ።
ጋዜጠኛዋ በገጿ ይህን ብላለች – 
ወዳጆቼ…
ላለፉት ሁለት አመታት የተለያዩ ፕሮግራሞችን ሳቀርብበት ከነበረው ዓባይ ሚዲያ  ጋር የነበረን ቆይታ ወደፊት በምገልፀው ምክንያት ተቋርጧል።
በነበረኝ ቆይታ ያበረታታችሁኝ አስተያየት እና ትችታችሁን ያጋራችሁኝ ወዳጆቼ ብርታት ስለሆናችሁኝ አመሰግናለሁ።
በአዲስ አመት በአዲስ እና በተሻለ የሚዲያ አማራጭ እንደምንገናኝ ስገልፅላችሁ ድጋፋችሁ እንደማይለየኝ በማመን ነው።
                 መልካም አዲስ ዓመት!
Filed in: Amharic