>

ወራሪን ሲቀልብ የኖረ ህዝብ የተራበ ወገኑን መመገብ እንዴት ይሳነዋል...??? (አቻምየለህ ታምሩ)

ወራሪን ሲቀልብ የኖረ ህዝብ የተራበ ወገኑን መመገብ እንዴት ይሳነዋል…???
አቻምየለህ ታምሩ

በማናለብኝነት አማራን አፋርን በመውረር የዘር ፍጅት እያካሄደ ለሚገኝ የፋሽስት ወያኔ  ወራሪ አንበጣ ሠራዊት ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብና ስንቅ ማቅረብ የቻለ ሕዝብ እንዴት የተራበ ወገኑን መመገብ ይሳነዋ?
የፋሽስት ወያኔ  ልሳን የሆነው የትግራይ ቴሌቭዥን ከሰሞኑ በትግርኛና በአማርኛ ቋንቋዎች በሰራቸው ፕሮግራሞች አማራና አፋርን በመውረር የዘር ማጥፋት ጦርነት እያደረገ ለሚገኝ የፋሽስት ወያኔ ወራሪ አንበጣ ሠራዊት የትግራይ ሕዝብ ከፍተኛ መጠን ያለው ስንቅ እያቀረበና ገብዘብ እያዋጣ እንደሆነ ነግሮናል።
የቴሌቭዥን ጣቢያው የትግራይ ሕዝብ አፋርና አማራን በመውረር  የዘር ማጥፋት እያካሄደ ለሚገኘው ወራሪ አንበጣ ሠራዊት ከፍተኛ መጠን ያለው ስንቅ በማቅረብና ገንዘብ በማዋጣት  የዘር ማጥፋት ጦርነቱን እየደገፈ እደሚገኝ ከፍተኛ መጠን ያላቸው የተለያዩ የምግብ አይነቶች ተዘጋጅተው ለመድረቅ በመቀሌ ጎዳናዎች ዳር እስከ ዳር ጢም ብለው ሞልተውና ከባጃጅ ሾፌር እስከ ገበሬ፤ ከነጋዴ እስከ መንግሥት ሰራተኛ  ያዋጣው ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ተከምሮ አሳይቶናል።
ይህንን የትግራይ ሕዝብ አዘጋጀ ያለውን ከፍተኛ መጠን ያለው ስንቅ በመቀሌ መንገዶች ከዳር እስከ ዳር ተሰጥቶና ተደረገ የተባለውን ከፍተኛ መጠን ያለውን የገንዘብ መዋጮ ከምሮ በቴሌቭዥን መስኮት ያሳየን የፋሽስት ወያኔ ቴሌቭዥን ጣቢያ ውሎ ሳያድር ዛሬ ደግሞ አማራና አፋርን በመውረር የዘር ማጥፋት ጦርነት ለሚያካሂደው ወራሪ አንበጣ ሠራዊት ከፍተኛ ስንቅ እያቀረበ እንደሚገኝ የነገረን ሕዝብ በርሃብ እየሞተ እንደሆነ እየነገረን ነው።
አማራና አፋርን በመውረር የዘር ማጥፋት እያደረገ ለሚገኘው የፋሽስት ወያኔ አንበጣ ሠራዊት  ከፍተኛ መጠን ያለው ስንቅ እያቀረበና ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እንዳዋጣ በተደጋጋሚ የተነገረን ሕዝብ እንዴት በምግብ እጦት በርሀብ ሊሞት ይችላል? የትግራይ ሕዝብ ለጠገበውና አማራንና አፋርን በመውረር የዘር ማጥፋት ጦርነት እያካሄደ ለሚገኘው ለፋሽስት ወያኔ ወራሪ አንበጣ ሠራዊት ከፍተኛ መጠን ያለው ስንቅ ማቅረብ ከቻለ ለወራሪው አንበጣ ሠራዊት ካዛጋጀው ከፍተኛ መጠን ያለው ስንቅ ላይ የተወሰነ ቀንሶ በረሀብ እየሞተ እንደሚገኝ ለተነገረን ወገኑ ለምንድን ነው የማይመግበው? ጠግቦ የሚገድልን አንበጣ ሠራዊት መመገብ የቻለ ሕዝብ እንዴት ብሎ ተርቦ የሚሞትን ወገኑን መመገብ ይሳነዋ?
Filed in: Amharic